መዝሙረ ዳዊት 67
67
1ለመዘምራን አለቃ፥ በበገናዎች፥ የዳዊት መዝሙር።
2 #
መዝ. 4፥7፤ 31፥17፤ 44፥4፤ 80፥4፤ ዳን. 9፥17። እግዚአብሔር ይማረን ይባርከንም፥
ፊቱንም በላያችን ያብራ፥
3 #
ኤር. 33፥9። መንገድህንም በምድር፥
በአሕዛብ ሁሉ መካከል ማዳንህን እናውቅ ዘንድ።
4አቤቱ፥ አሕዛብ ያመስግኑህ፥
አሕዛብ ሁሉ ያመስግኑህ።
5 #
መዝ. 98፥9። ለአሕዛብ በቅን ትፈርድላቸዋለህና፥
አሕዛብንም በምድር ላይ ትመራለህና
አሕዛብ ደስ ይበላቸው ሐሤትም ያድርጉ።
6አቤቱ፥ አሕዛብ ያመስግኑህ፥
አሕዛብ ሁሉ ያመስግኑህ።
7 #
መዝ. 85፥13፤ ዘሌ. 26፥4፤ ሕዝ. 34፥27፤ ሆሴዕ 2፥23-24። ምድር ፍሬዋን ሰጠች፥
እግዚአብሔር አምላካችንም ይባርከናል።
8እግዚአብሔር ይባርከናል፥
የምድርም ዳርቻ ሁሉ ይፈሩታል።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 67: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
![None](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapistaging.com%2F58%2Fhttps%3A%2F%2Fweb-assets.youversion.com%2Fapp-icons%2Fam.png&w=128&q=75)
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ