መዝሙረ ዳዊት 8
8
1ለመዘምራን አለቃ በዋሽንት፥ የዳዊት መዝሙር።
2አቤቱ ጌታችን፥ ስምህ በምድር ሁሉ ምን ያህል ገናና ነው፥
ክብርህን በሰማዮች ላይ የምታኖር።
3 #
ማቴ. 21፥16፤ ጥበ. 10፥21። በጠላቶችህ ምክንያት ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ፥
ጠላትንና ቂመኛን ለማጥፋት።
4የጣቶችህን ሥራ ሰማዮችህን ባየሁ ጊዜ፥
ጨረቃንና ከዋክብትን አንተ የሠራሃቸውን፥
5 #
መዝ. 144፥3፤ ኢዮብ 7፥17-18፤ ዕብ. 2፥6-8። ታስበው ዘንድ ሰው ምንድነው?
ትጐበኘውም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድነው?
6 #
ጥበ. 2፥23፤ ሲራ. 17፥1-4። ከመላእክት#8፥6 ከአምላክ ጥቂት አሳነስከው የሚሉ ትርጉሞች አሉ። ሌሎች ትርጉሞች ደግሞ እንደ ዕብ 2፥ 7 መላእክት የሚለውን ትርጒም ይመርጣሉ። እጅግ ጥቂት አሳነስኸው፥
በክብርና በምስጋና ዘውድ ከለልኸው።
7 #
ዘፍ. 1፥26፤ 28፤ ጥበ. 9፥2፤ 1ቆሮ. 15፥27፤ ኤፌ. 1፥22፤ ዕብ. 2፥8። በእጆችህም ሥራ ሁሉ ላይ ሾምኸው፥
ሁሉን ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት፥
8በጎችንም ላሞችንም ሁሉ
ደግሞም የምድረ በዳውን እንስሶች፥
9የሰማይንም ወፎች የባሕርንም ዓሦች፥
በባሕር መንገድ የሚሄደውንም ሁሉ።
10አቤቱ ጌታችን፥ ስምህ በምድር ሁሉ እጅግ ተመሰገነ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 8: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ