መዝሙረ ዳዊት 82
82
1የአሳፍ መዝሙር።
#
ኢሳ. 3፥13-14። እግዚአብሔር በመለኮታዊ ጉባኤ ቆመ፥
በአማልክትም መካከል ይፈርዳል።
2 #
መዝ. 58፥2። እስከ መቼ ሐሰትን ትፈርዳላችሁ?
እስከ መቼስ ለክፉዎች ታደላላችሁ?
3ለድሆችና ወላጅ ለሞተባቸው ፍረዱ፥
ለችግረኛውና ለምስኪኑ ፍትሕን አድርጉ፥
4 #
ዘዳ. 1፥17። ብቸኛውንና ችግረኛውን አድኑ፥
ከክፉዎችም እጅ አስጥሉአቸው።
5አያውቁም፥ አያስተውሉም፥
በጨለማ ውስጥ ይመላለሳሉ፥
የምድር መሠረቶች ሁሉ ተናወጡ።
6 #
2ጴጥ. 1፥4። እኔ ግን፦ አማልክት ናችሁ፥
ሁላችሁም የልዑል ልጆች ናችሁ አልሁ፥
7ነገር ግን እንደ ሰው ትሞታላችሁ፥
ከአለቆችም እንደ አንዱ ትወድቃላችሁ።
8አቤቱ፥ ተነሥ፥ በምድር ላይ ፍረድ፥
አንተ አሕዛብን ሁሉ ትወርሳለህና።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 82: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መዝሙረ ዳዊት 82
82
1የአሳፍ መዝሙር።
#
ኢሳ. 3፥13-14። እግዚአብሔር በመለኮታዊ ጉባኤ ቆመ፥
በአማልክትም መካከል ይፈርዳል።
2 #
መዝ. 58፥2። እስከ መቼ ሐሰትን ትፈርዳላችሁ?
እስከ መቼስ ለክፉዎች ታደላላችሁ?
3ለድሆችና ወላጅ ለሞተባቸው ፍረዱ፥
ለችግረኛውና ለምስኪኑ ፍትሕን አድርጉ፥
4 #
ዘዳ. 1፥17። ብቸኛውንና ችግረኛውን አድኑ፥
ከክፉዎችም እጅ አስጥሉአቸው።
5አያውቁም፥ አያስተውሉም፥
በጨለማ ውስጥ ይመላለሳሉ፥
የምድር መሠረቶች ሁሉ ተናወጡ።
6 #
2ጴጥ. 1፥4። እኔ ግን፦ አማልክት ናችሁ፥
ሁላችሁም የልዑል ልጆች ናችሁ አልሁ፥
7ነገር ግን እንደ ሰው ትሞታላችሁ፥
ከአለቆችም እንደ አንዱ ትወድቃላችሁ።
8አቤቱ፥ ተነሥ፥ በምድር ላይ ፍረድ፥
አንተ አሕዛብን ሁሉ ትወርሳለህና።