የዮሐንስ ራእይ 19
19
1ከዚህ በኋላ በሰማይ የብዙ ሕዝብ ታላቅ ድምፅን የመሰለ ድምፅ ሰማሁ፦ “ሃሌ ሉያ! ማዳንና ክብር ኃይልም የአምላካችን ነው፤” 2#ዘዳ. 32፥43፤ 2ነገ. 9፥7።ፍርዶቹ እውነትና ጽድቅ ናቸውና፤ በዝሙትዋ ምድርን ያበላሸችውን ታላቂቱን አመንዝራ ፈርዶባት፥ የባርያዎቹንም ደም ከእጅዋ ተበቀሎአልና። 3#ኢሳ. 34፥10።ደግመውም እንዲህ አሉ፦ “ሃሌ ሉያ! ጢስዋም ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይወጣል፤” አሉ። 4ሃያ አራቱም ሽማግሌዎችና አራቱ ሕያዋን ፍጡራን በፊታቸው ተደፍተው በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለእግዚአብሔር “አሜን! ሃሌ ሉያ!” እያሉ ሰገዱለት።
የበጉ ሰርግ
5 #
11፥18፤ መዝ. 115፥13። ድምፅም ከዙፋኑ እንዲህ ሲል ወጣ፦
“ባርያዎቹ ሁሉ እርሱንም የምትፈሩት ታናናሾችና ታላላቆች
ሆይ! አምላካችንን አመስግኑ፤” 6የብዙ ሕዝብም ድምፅ፥ የብዙ ውሃዎችም ድምፅ፥ የብርቱም ነጐድጓድም ድምፅ የሚመስል ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤
“ሃሌ ሉያ! ሁሉን የሚገዛ ጌታ አምላካችን ነግሦአልና።
7 #
ማቴ. 22፥9፤ ኤፌ. 5፥27። የበጉ ሰርግ ስለ ደረሰ፤ ሚስቱም ራስዋን ስላዘጋጀች ደስ ይበለን፤ ሐሤትም እናድርግ፤ ክብርንም ለእርሱ እናቅርብ።
8 #
15፥6፤ ኢሳ. 61፥10፤ ማቴ. 22፥11-12። ያጌጠና የተጣራ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ እንድትለብስ ተሰጥቶአታል።”
ቀጭኑ የተልባ እግር የቅዱሳን የጽድቅ ሥራ ነውና።
9 #
ማቴ. 8፥11፤ ሉቃ. 14፥15፤ ማቴ. 22፥2-3። መልአኩም “ወደ በጉ ሰርግ እራት የተጠሩ ብፁዓን ናቸው፤” ብለህ ጻፍ፤ አለኝ። ደግሞም “ይህ የእግዚአብሔር እውነተኛ ቃል ነው፤” አለኝ። 10#22፥8-9።ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ። እርሱም “እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክርነት ከሚጠብቁት ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባርያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤ የኢየሱስ ምስክርነት የትንቢት መንፈስ ነውና፤” አለኝ።
በነጭ ፈረስ ላይ የተቀመጠው ፈረሰኛ
11 #
ኢሳ. 11፥4። ሰማይም ተከፍቶ አየሁ፤ እነሆም ነጭ ፈረስ፤ የተቀመጠበትም የታመነና እውነተኛ ይባላል፤ በጽድቅም ይፈርዳል፤ ይዋጋልም። 12#1፥14-16፤ 2፥18፤ ሉቃ. 10፥22፤ ዳን. 10፥6።ዐይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ናቸው፤ በራሱ ላይም ብዙ ዘውዶች አሉ፤ ከእርሱም በቀር ማንም የማያውቀው የተጻፈ ስም አለው፤ 13#ኢሳ. 63፥1፤ ዮሐ. 1፥1፤ ጥበ. 18፥14-18።በደምም የተረጨ#19፥13 “የተነከረ” የሚሉ ትርጉሞችም አሉ። ልብስ ተጐናጽፎአል፤ ስሙም የእግዚአብሔር ቃል ተብሏል። 14#15፥6፤ 19፥8።በሰማይም ያሉት ሠራዊት ነጭና ጥሩ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ ለብሰው በነጭ ፈረሶች ላይ ተቀምጠው ይከተሉት ነበር። 15#14፥20፤ መዝ. 2፥9፤ ኢሳ. 63፥3፤ ኢዩ. 3፥13፤ ራእ. 14፥20።አሕዛብንም ይመታበት ዘንድ ስለታም ሰይፍ ከአፉ ይወጣል፤ እርሱም በብረት በትር ይገዛቸዋል፤ እርሱም ሁሉን የሚገዛ የእግዚአብሔርን የብርቱ ቁጣውን ወይን መጥመቂያ ይረግጣል። 16#17፥14፤ 2መቃ. 13፥4።በልብሱና በጭኑም ላይ “የነገሥታት ንጉሥና የጌታዎች ጌታ” የሚል ስም ተጽፎአል።
17አንድም መልአክ በፀሐይ ውስጥ ቆሞ አየሁ፤ በሰማይም መካከል ለሚበሩ ወፎች ሁሉ “ወደ ታላቁ የእግዚአብሔር እራት ኑ፥ ተሰብሰቡ፤ 18#ሕዝ. 39፥17-20።የነገሥታትን ሥጋና የሻለቃዎችን ሥጋ የብርቱዎችንም ሥጋ የፈረሶችንም በእነርሱም የተቀመጡትን ሥጋ የጌታዎችንና የባርያዎችንም የታናናሾችንና የታላላቆችንም ሁሉ ሥጋ ትበሉ ዘንድ” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። 19በፈረሱም የተቀመጠውንና ሠራዊቱን ይወጉ ዘንድ አውሬውና የምድር ነገሥታት ከነሠራዊታቸው ተሰብስበው አየሁ። 20#14፥10፤ ራእ. 13፥1-18።አውሬውም ተያዘ፤ በእርሱም ፊት ተአምራትን እያደረገ የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትን ለምስሉም የሰገዱትን ያሳተ ሐሰተኛውም ነቢይ ከእርሱ ጋር ተያዘ፤ ሁለቱም በሕይወት ሳሉ በዲን ወደሚቃጠል ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ። 21የቀሩትም በፈረስ ላይ ከተቀመጠው አፍ በሚወጣው ሰይፍ ተገደሉ፤ ወፎችም ሁሉ ከሥጋቸው ጠገቡ።
Currently Selected:
የዮሐንስ ራእይ 19: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ