የዮሐንስ ራእይ 5
5
የተዘጋው መጽሐፍና በጉ
1 #
ሕዝ. 2፥9፤10፤ ኢሳ. 29፥11። በዙፋኑ ላይም በተቀመጠው በቀኝ እጁ ላይ በውስጥና በኋላ የተጻፈበት በሰባትም ማኅተም የተዘጋ መጽሐፍን አየሁ። 2ብርቱም መልአክ “መጽሐፉን መዘርጋትና#5፥2 የብራና ጥቅል “ይዘረጋ” ነበር። ማኅተሞቹንም መፍታት የሚገባው ማን ነው?” ብሎ በታላቅ ድምፅ ሲያውጅ አየሁ። 3በሰማይም ቢሆን በምድርም ላይ ቢሆን ከምድርም በታች ቢሆን መጽሐፉን ሊዘረጋ ወይም ሊመለከተው ማንም አልተቻለውም። 4መጽሐፉን ሊዘረጋ ወይም ሊመለከተው የሚገባው ማንም ስላልተገኘ እጅግ አለቀስሁ። 5#ዘፍ. 49፥9፤ ኢሳ. 11፥1፤10።ከሽማግሌዎቹም አንዱ “አታልቅስ፤ እነሆ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ፥ እርሱም የዳዊት ሥር መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነሥቶአል፤” አለኝ።
6 #
ኢሳ. 53፥7፤ ዘካ. 4፥10። በዙፋኑና በአራቱ ሕያዋን ፍጡራን መካከልም በሽማግሌዎችም መካከል እንደ ታረደ በግ ቆሞ አየሁ፤ ሰባትም ቀንዶችና ሰባት ዐይኖች ነበሩት፤ እነርሱም ወደ ምድር ሁሉ የተላኩ የእግዚአብሔር መናፍስት ናቸው። 7መጥቶም በዙፋን ላይ ከተቀመጠው ቀኝ እጅ መጽሐፉን ወሰደው። 8#መዝ. 140፥2።መጽሐፉንም በወሰደ ጊዜ አራቱ ሕያዋን ፍጡራን ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ፤ እያንዳንዳቸውም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ሳሕን ያዙ።
9-10 #
መዝ. 32፥3፤ 97፥1፤ ኢሳ. 42፥10። #
ዘፀ. 19፥6፤ ራእ. 1፥6። “መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል
ታርደሃልና፤ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ
ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ፥
ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፤
በምድርም ላይ ይነግሣሉ፤”
እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ። 11#ዳን. 7፥10።አየሁም፤ በዙፋኑም በእንስሶቹም በሽማግሌዎቹም ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ ሰማሁ፤ ቁጥራቸውም አእላፋት ጊዜ አእላፋትና ሺህ ጊዜ ሺህ ነበር፤ 12በታላቅም ድምፅ
“የታረደው በግ ኃይልና ባለጠግነት ጥበብም ብርታትም
ገናናነትም ክብርም ውዳሴም ሊቀበል ይገባዋል”
አሉ። 13በሰማይና በምድርም ከምድርም በታች በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ
“ውዳሴ ገናናነት ክብርም ኃይልም ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም
በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው፥ ለበጉም ይሁን፤”
ሲሉ ሰማሁ። 14አራቱም ሕያዋን ፍጡራን “አሜን” አሉ፤ ሽማግሌዎቹም ወድቀው ሰገዱ።
Currently Selected:
የዮሐንስ ራእይ 5: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ