የዮሐንስ ራእይ 9
9
1አምስተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ ከሰማይም ወደ ምድር ወድቆ የነበረ ኮከብ አየሁ፤ የጥልቁም ጉድጓድ መክፈቻ ተሰጠው። 2#ዘፍ. 19፥28።የጥልቁንም ጉድጓድ ከፈተው፤ ጢስም ከታላቅ ምድጃ እንደሚወጣ ጢስ ሆኖ ከጉድጓዱ ወጣ፤ ፀሐይና አየርም በጉድጓዱ ጢስ ጨለሙ። 3#ዘፀ. 10፥12-15፤ ጥበ. 16፥9።ከጢሱም አንበጣዎች ወደ ምድር ወጡ፤ የምድርም ጊንጦች እንዳላቸው ሥልጣን ዓይነት ሥልጣን ተሰጣቸው። 4#ሕዝ. 9፥4።የእግዚአብሔርም ማኅተም በግምባራቸው ከሌለባቸው ሰዎች በቀር በምድር ያለውን ሣር ቢሆንም ወይም ማናቸውንም የለመለመ ነገር ወይም ማናቸውንም ዛፍ እንዳይጐዱ ተነገራቸው። 5ለአምስትም ወር እንዲያሰቃዩአቸው እንጂ እንዲገድሉአቸው አልተፈቀደላቸውም፤ እነርሱም የሚያደርሱት ሥቃይ ጊንጥ ሰውን ሲነድፍ እንደሚያደርሰው ስቃይ ዓይነት ነው። 6#ኢዮብ 3፥21፤ ኤር. 8፥3።በዚያም ቀኖች ሰዎች ሞትን ይፈልጋሉ፤ አያገኙትምም፤ ሊሞቱም ይመኛሉ፤ ሞትም ከእነርሱ ይሸሻል።
7 #
ኢዩ. 2፥4። አንበጣዎቹም ለጦርነት የተዘጋጁ ፈረሶችን ይመስሉ ነበር፤ በራሳቸውም ላይ የወርቅ የሚመስሉ አክሊሎች ነበሩአቸው፤ ፊታቸውም የሰው ፊት ይመስል ነበረ፤ 8#ኢዩ. 1፥6።የሴቶችን ጠጉር የሚመስል ጠጉር ነበራቸው፤ ጥርሳቸውም እንደ አንበሳ ጥርስ ነበረ፤ 9#ኢዩ. 2፥5።የብረት ጥሩር የሚመስልም ጥሩር ነበራቸው፤ የክንፋቸውም ድምፅ ወደ ጦርነት እንደሚጋልቡ እንደ ብዙ ፈረሶች ሠረገላዎች ድምፅ ነበረ። 10እንደ ጊንጥም ጅራት ያለ ጅራት አላቸው፤ በጅራታቸውም መውጊያ አለ፤ ሰዎችንም ለአምስት ወር ያህል የመጉዳት ሥልጣን አላቸው። 11ንጉሥም ነበራቸው፤ እርሱም የጥልቁ ጉድጓድ መልአክ ነው፤ ስሙም በዕብራይስጥ አባዶን በግሪክም አጶልዮን ነው።
12የፊተኛው “ወዮ” አልፎአል፤ እነሆ ከዚህ በኋላ ገና ሁለት “ወዮ” ይመጣል።
13 #
ዘፀ. 30፥1-3። ስድስተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ካለው በወርቅ ከተሠራው መሠዊያ ቀንዶች ድምፅ ሲወጣ ሰማሁ፤ 14እርሱም መለከት ለያዘው ስድስተኛው መልአክ “በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ የታሰሩትን አራቱን መላእክት ፍታቸው፤” አለው። 15የሰዎችንም ሲሶ እንዲገድሉ ለሰዓቱና ለቀኑ ለወሩም ለዓመቱም ተዘጋጅተው የነበሩ አራቱ መላእክት ተፈቱ። 16የፈረሰኞችም ጭፍራ ቍጥር ሁለት መቶ ሚሊዮን ነበረ፤ ቁጥራቸውን ሰማሁ። 17#ጥበ. 11፥17፤18።ፈረሶቹንና በእነርሱም ላይ የተቀመጡትን እንዲሁ በራእይ አየሁ፤ እሳትና ያክንት ዲንም የሚመስል ጥሩር ነበራቸው፤ የፈረሶቹም ራስ እንደ አንበሳ ራስ ነበረ፤ ከአፋቸውም እሳትና ጢስ ዲንም ወጣ። 18ከአፋቸውም በወጡት በእሳቱና በጢሱ በዲኑም በእነዚህ ሦስት መቅሰፍቶች የሰዎቹ ሲሶ ተገደለ። 19የፈረሶቹ ሥልጣን በአፋቸውና በጅራታቸው ነውና፥ ጅራታቸው እባብን ይመስላል፤ ራስም አላቸው፤ በእርሱም ጉዳትን ያደርሳሉ።
20 #
መዝ. 135፥15-17፤ ኢሳ. 17፥8፤ ዳን. 5፥4። በእነዚህም መቅሠፍቶች ያልተገደሉት የቀሩቱ ሰዎች ስለ እጃቸው ሥራ ንስሓ አልገቡም፤ ለአጋንንትና ማየት ወይም መስማት ወይም መሄድ ለማይችሉ ከወርቅና ከብር ከናስም ከድንጋይም ከእንጨትም ለተሠሩ ለጣዖቶችም መስገድን አልተዉም። 21ስለ መግደላቸውም ቢሆን ወይም ስለ አስማታቸው ወይም ስለ ዝሙታቸው ወይም ስለ ስርቆታቸው ንስሓ አልገቡም።
Currently Selected:
የዮሐንስ ራእይ 9: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ