ወደ ሮሜ ሰዎች 4
4
የአብርሃም ምሳሌነት
1እንግዲህ በሥጋ አባታችን የሆነ አብርሃም ምን አገኘ እንላለን? 2አብርሃም በሥራ ጸድቆ ቢሆን የሚመካበት አለውና፤ በእግዚአብሔር ፊት ግን መመካት አይችልም። 3#ዘፍ. 15፥6፤ ገላ. 3፥6።መጽሐፉስ ምን አለና? “አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ፤ ጽድቅም ሆኖ ተቆጠረለት።” 4እንግዲህ ለሚሠራ ሰው፥ ደመወዝ እንደ ክፍያ ነው እንጂ እንደ ጸጋ አይቆጠርለትም፤ 5ለማይሠራ፥ ነገር ግን ኃጢአተኛውን በሚያጸድቅ ለሚያምን፥ እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቆጠርለታል። 6ደግሞም ዳዊት እንኳ፥ እግዚአብሔር ያለ ሥራ፥ ጽድቅን ስለሚቆጥርለት ሰው፥ ስለ መባረኩ ሲናገር፤
7 #
መዝ. 32፥1፤2። “መተላለፋቸው ይቅር የተባለላቸው፥ ኃጢአታቸውም የተከደነላቸው የተባረኩ ናቸው፤
8ጌታ ኃጢአቱን የማይቆጥርበት ሰው የተባረከ ነው።”
9እንግዲህ ይህ መባረክ በመገረዝ መጣን? ወይስ ደግሞ ባለመገረዝ? አብርሃም እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት እንላለንና። 10እንዴት ታዲያ ተቆጠረለት? ተገርዞ ሳለ ነውን? ወይስ ሳይገረዝ? ሳይገረዝ ነበር እንጂ፤ ከተገረዘ በኋላ አይደለም። 11#ዘፍ. 17፥10።ሳይገረዝም በእምነቱ ባገኘው የጽድቅ ማኅተም፥ መገረዝን እንደ ምልክት ተቀበለ፤ ሳይገረዙ ለሚያምኑ ሁሉ፥ ለእነርሱም ጽድቅ ሆኖ እንዲቆጠርላቸው አባት ነውና፤ 12ለተገረዙትም አባት ነው፤ ለተገረዙት ብቻ ሳይሆን፥ ነገር ግን አባታችን አብርሃም ከመገረዙ በፊት የነበረውን የእምነቱን ፈለግ ለሚከተሉ ጭምር ነው።
የተሰጠውን ተስፋ በእምነት በኩል ስለመረዳት
13 #
ዘፍ. 17፥4-6፤ 22፥17፤18፤ ገላ. 3፥29። ዓለምን እንዲወርስ ለአብርሃምና ለዘሩ የተሰጠው የተስፋ ቃል በእምነት ጽድቅ ነው እንጂ በሕግ አይደለም። 14#ገላ. 3፥18።ከሕግ የሆኑትስ ወራሾች ከሆኑ እምነት ከንቱ ሆኖአል፤ የተስፋውም ቃል ተሽሮአል፤ 15ሕጉ መቅሠፍትን ያስከትላልና፤ ነገር ግን ሕግ በሌለበት መተላለፍ#4፥15 ሕግንና ሥርዓትን መጣስ ማለት ነው። የለም።
16 #
ገላ. 3፥7። ስለዚህ በእምነት የሆነው፥ ተስፋው በእምነት እንዲያርፍና ለዘሩ ሁሉ እንዲሆን ነው፥ ይህም ሕግ ፈፃሚዎች ብቻ ሳይሆኑ የአብርሃምን እምነት የሚጋሩትንም ጭምር ነው፥ እርሱ የሁላችንም አባት ነውና፥ 17#ዘፍ. 17፥5።“የብዙ ሕዝቦች አባት አድርጌሃለሁ” ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ የሞተውን ሕያው በሚያደርግ የሌለውንም እንዳለ አድርጎ በሚጠራ ባመነበት አምላክ ፊት ነው። 18#ዘፍ. 15፥5።“ዘርህም እንዲሁ ይሆናል” ተብሎ እንደ ተነገረው፥ ተስፋ በሌለበት የብዙ ሕዝቦች አባት እንደሚሆን በተስፋ አመነ። 19#ዘፍ. 17፥17።መቶ ዓመት ሆኖት ሳለ ምውት የሆነውን የራሱን አካልና የሳራ ማኅፀን ምውት መሆን አስቦ በእምነት አልደከመም፤ 20ለእግዚአብሔርም ክብር እየሰጠ፥ በእምነት በረታ እንጂ፤ እግዚአብሔር የሰጠውን ተስፋ አልተጠራጠረም። 21የሰጠውንም ተስፋ እንደሚፈጽም ጽኑ እምነት ነበረው። 22በዚህም ምክንያት “ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት።” 23ነገር ግን “ተቆጠረለት” የሚለው ቃል የተጻፈው በእርሱ ምክንያት ብቻ አይደለም፤ 24ለእኛም ጭምር ነው፤ ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሣው ለምናምን ለእኛም እንዲቆጠርልን ነው። 25#ኢሳ. 53፥4፤5።ስለ ኃጢአታችን ለሞት ተላልፎ ተሰጠ፤ ለጽድቃችንም ተነሣ።
Currently Selected:
ወደ ሮሜ ሰዎች 4: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ