ወደ ሮሜ ሰዎች 6
6
ለኃጢአት መሞት በክርስቶስ መኖር
1እንግዲህ ምን እንላለን? ጸጋ እንዲበዛ ኃጢአት በመሥራት እንቀጥል? 2በጭራሽ! ለኃጢአት የሞትን እስካሁን እንዴት በእርሱ እንኖራለን? 3ወይስ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ ለመሆን የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ ለመሆን እንደ ተጠመቅን አታውቁምን? 4#ቈላ. 2፥12።ስለዚህ በአብ ክብር ክርስቶስ ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንኖር፥ በጥምቀት አማካኝነት በሞት ከእርሱ ጋር ተቀብረናል።
5የእርሱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር አንድ ከሆንን እንዲሁም ደግሞ በትንሣኤው ከእርሱ ጋር አንድ እንሆናለን፤ 6ከእንግዲህስ ወዲያ ለኃጢአት ባርያዎች እንዳንሆን የኃጢአት ሰውነት እንዲሻር አሮጌው ማንነታችን ከእርሱ ጋር እንደ ተሰቀለ እናውቃለን። 7የሞተስ ከኃጢአት ነጻ ወጥቶአልና። 8ነገር ግን ከክርስቶስ ጋር ከሞትን ከእርሱ ጋር ደግሞ እንደምንኖር እናምናለን። 9ክርስቶስ ከሙታን ተነሥቷል፥ ዳግመኛም እንደማይሞት እናውቃለንና፤ ሞት ከእንግዲህ እርሱን አይገዛውም። 10በእርሱ ሞቷልና፥ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለኃጢአት ሞቷል፤ መኖርን ግን ለእግዚአብሔር ይኖራል። 11እንዲሁም ደግሞ እናንተ በአንድ በኩል በእርግጥ ለኃጢአት እንደ ሞታችሁ፥ በሌላ በኩል ግን በክርስቶስ ኢየሱስ ለእግዚአብሔር ሕያዋን እንደ ሆናችሁ ራሳችሁን ቁጠሩ።
12ስለዚህ፥ ለምኞቱ ታዛዥ ሊያደርጋችሁ በሚሞተው ሰውነታችሁ ላይ ኃጢአት አይንገሥ። 13የሰውነታችሁን ክፍሎች የክፋት መሣሪያ አድርጋችሁ ለኃጢአት አታቅርቡ፤ ነገር ግን ከሙታን ተለይታችሁ እንደምትኖሩ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ፤ የሰውነታችሁንም ክፍሎች የጽድቅ መሣሪያ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ። 14ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች ስላልሆናችሁ ኃጢአት አይገዛችሁም።
የጽድቅ ባርያዎች
15እንግዲህ ምን ይሁን? ከሕግ በታች ሳይሆን ከጸጋ በታች ስለ ሆንን ኃጢአት መሥራት አለብንን? በጭራሽ! 16እራሳችሁን የመታዘዝ ባርያዎች አድርጋችሁ ለምታቀርቡለት፥ ለምትታዘዙት ለእርሱ ሞትን ለሚያመጣው ለኃጢአት ወይም ጽድቅን ለሚያመጣው ለመታዘዝ ባርያዎች እንደ ሆናችሁ አታውቁምን? 17አስቀድማችሁ የኃጢአት ባርያዎች የነበራችሁ፥ ነገር ግን ለተሰጣችሁለት የትምህርት ዓይነት ከልባችሁ በመታዘዛችሁ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን። 18ከኃጢአትም ነፃ ወጥታችሁ ለጽድቅ ባርያዎች ሆናችኋል። 19ከሥጋችሁ ደካማነት የተነሣ እንደ ሰው አነጋገር እናገራለሁ። የሰውነታችሁን ክፍሎች ሕገ ወጥነትን ለሚያመጣ ለርኩሰትና ለሕገ ወጥነት ባርያዎች አድርጋችሁ እንዳቀረባችሁ፥ ስለዚህ አሁን የሰውነታችሁን ክፍሎች ቅድስና ለሚያመጣ ለጽድቅ ባርያዎች አድርጋችሁ አቅርቡ።
20የኃጢአት ባርያዎች በነበራችሁበት ጊዜ ከጽድቅ ነፃ ነበራችሁ። 21ታዲያ አሁን ከምታፍሩበት ነገር ሌላ ያንጊዜ ምን ፍሬ ነበራችሁ? የእነዚህ ነገሮች መጨረሻ ሞት ነውና። 22አሁን ግን ከኃጢአት ነፃ ወጥታችሁ ለእግዚአብሔርም ባርያዎች ሆናችኋል፥ ፍሬያችሁም ቅድስና ነው፤ መጨረሻውም የዘለዓለም ሕይወት ነው። 23የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፥ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ የዘለዓለም ሕይወት ነው።
Currently Selected:
ወደ ሮሜ ሰዎች 6: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ