የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ሩት 3

3
ሩት እና ቦዔዝ በአውድማው
1አማቷም ናዖሚ አለቻት፦ “ልጄ ሆይ! መልካም ይሆንልሽ ዘንድ የተመቻቸ ኑሮ የምትኖሪበትን ሁናቴ ልፈልግልሽ ይገባል።#ሩት 1፥9። 2አሁንም ስትቃርሚ አብረውሽ የነበሩት ሴቶች የሚያገለግሉት ቦዔዝ ዘመዳችን አይደለምን? እነሆ፥ እርሱ በዛሬ ሌሊት በአውድማው ላይ ገብሱን በመንሽ ይበትናል።#ሩት 2፥1። 3እንግዲህ ሰውነትሽን ታጠቢና ሽቶ ተቀቢ፥ የክት ልብስሽንም ልበሺ፥ ከዚህ በኋላ እርሱ ገብሱን ወደሚወቃበት አውድማ ሂጂ፤ ነገር ግን እስከሚበላና እስከሚጠጣ ድረስ በፊቱ አትታዪ። 4በሚተኛም ጊዜ፥ የሚተኛበትን ስፍራ ተመልከቺ፥ ገብተሽም ከግርጌው በኩል ልብሱን ገልጠሽ በእግሩ አጠገብ ተኚ፤ ምን ማድረግ እንደሚገባሽ እርሱ ራሱ ይነግርሻል።” 5ሩትም፦ “ያልሽውን ሁሉ አደርጋለሁ” አለቻት።
6ስለዚህ ወደ አውድማው ወረደች፥ አማትዋም ያዘዘቻትን ሁሉ አደረገች። 7ቦዔዝም ከበላና ከጠጣ ሰውነቱንም ደስ ካሰኘ በኋላ፥ በእህሉ ክምር አጠገብ ሊተኛ ሄደ፥ ሩትም በቀስታ መጣች፥ እግሩንም ገልጣ ተኛች። 8መንፈቀ ሌሊትም በሆነ ጊዜ ሰውዮው ደነገጠ፥ ዘወርም አለ፥ እነሆም፥ አንዲት ሴት በግርጌው ተኝታ ነበር። 9እርሱም፦ “ማን ነሽ?” አለ። እርሷም፦ “እኔ ባርያህ ሩት ነኝ፥ ዋርሳዬ ነህና ልብስህን በባርያህ ላይ ጣል አለችው።#3፥9 በዚህ ድርጊት፥ ዋርሳዋ በመሆኑ፥ ሩት እንዲያገባት ቦዔዝን ጠየቀችው፥ ዘዳ 23፥1-27 ሕዝ 16፥810ቦዔዝም አላት፦ “ልጄ ሆይ፥ በጌታ የተባረክሽ ሁኚ፥ ባለ ጠጋ ይሁን ወይም ድሀ፥ ወጣቶችን መርጠሽ መሄድ አልፈለግሽምና ከፊተኛው ይልቅ አሁን ባደረግሽው#3፥10 ሩት ከእናትዋ አማት ጋር መቆየትዋ ብቻ ሳይሆን፥ ሩት 2፥11፤ ቦዔዝን በማግባት ቤተሰቡን ጠብቃ ለማቆየት ፈቃደኛ ነበረች። ታማኝነትን አድርገሻል። 11አሁንም፥ ልጄ ሆይ! አትፍሪ፤ በከተማው ያሉ ሰዎች ሁሉ አንቺ ምግባረ መልካም ሴት እንደ ሆንሽ ያውቃሉና ያልሽውን ነገር ሁሉ አደርግልሻለሁ። 12የቅርብ ዘመድ መሆኔ እውነት ነው፥ ነገር ግን ከእኔ ይልቅ ቅርብ የሆነ ሌላ ዘመድ አለ፤#ሩት 4፥1። 13ዛሬ ሌሊት እደሪ፥ ነገም እርሱ ዋርሳ መሆን ቢወድ መልካም ነው፥ ዋርሳ ይሁን፥ ዋርሳ ሊሆን ባይወድ ግን፥ ሕያው ጌታን እኔ ዋርሳ እሆንሻለሁ፥ እስኪ ነጋ ድረስ ተኚ።”#ሩት 1፥16፤ 4፥5።
14እስኪነጋም በእግርጌው ተኛች፥ ቦዔዝም፦ “ሴት ወደ አውድማው እንደ መጣች ማንም እንዳያውቅ” ብሎ ነበርና ማንም ሊያያት በማይችልበት ሰዓት በማለዳ ከመኝታዋ ተነሣች። 15እርሱም፦ “የለበስሽውን ልብስ አምጥተሽ ያዥው” አላት፤ በያዘችም ጊዜ ወደ ኻያ ኪሎ የሚጠጋ ገብስ ሰፍሮላት አሸከማት። እርሱም ወደ ከተማይቱ ሄደ። 16ወደ አማትዋም በመጣች ጊዜ አማቷ፦ “ልጄ ሆይ እንዴት ነሽ?” አለቻት፥ እርሷም ሰውየው ያደረገላትን ሁሉ ነገረቻት። 17“ወደ አማትሽ ባዶ እጅሽን አትሂጂ፥ ብሎ ይህን ኻያ ኪሎ ገብስ ሰጠኝ” አለቻት።#ሩት 1፥21። 18እርሷም፦ “ልጄ ሆይ! ሰውዬው ይህን ነገር ዛሬ እስኪጨርስ ድረስ አያርፍምና፥ ፍጻሜው እስኪታወቅ ድረስ ጠብቂ” አለቻት።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ