የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መኃልየ መኃልይ 5

5
1እኅቴ ሙሽራዬ ሆይ፥ ወደ ገነቴ ገባሁ፥
ከርቤዬን ከቅመሜ ጋር ለቀምሁ፥
እንጀራዬን ከማሬ ጋር በላሁ፥
የወይን ጠጄን ከወተቴ ጋር ጠጣሁ።
ባልንጀሮቼ ሆይ፥ ብሉ፥ ጠጡ፥
ወዳጆቼ ሆይ፥ እስክትረኩ ድረስ ጠጡ#5፥1 በፍቅር ስከሩ የሚል ፍቺም ሊኖረው ይችላል።
2እኔ ተኝቻለሁ፥ ልቤ ግን ነቅቶአል፥
የውዴ ድምፅ ነው፥ እርሱም ያንኳኳል፥
እኅቴ፥ ወዳጄ፥ ርግቤ፥ የእኔ እንከን የለሽ፥
ራሴ በጠል፥ ጸጉሬም በሌሊት ነጠብጣብ ርሶአል።
3ቀሚሴን አወለቅሁ፥ እንዴት እለብሰዋለሁ?
እግሬን ታጠብሁ፥ እንዴት አሳድፈዋለሁ?
4ውዴ እጁን በቀዳዳ ሰደደ፥
አንጀቴም ስለ እርሱ ታወከ።
5ለውዴ እከፍትለት ዘንድ ተነሣሁ፥
እጆቼ በደጁ መወርወሪያ#5፥5 የበር መክፈቻ። ላይ ከርቤን አፈሰሱ፥
ጣቶቼ ፈሳሹን ከርቤ አንጠባጠቡ።
6ለውዴ ከፈትሁለት፥
ውዴ ግን ፈቀቅ ብሎ አልፎ ነበር።
ነፍሴ ከመራቁ የተነሣ#5፥6 “ድምፁን ከመስማት የተነሣ” ወይም “ድምፁን ምነው በሰማሁት” የሚል ትርጉምም ሊኖረው ይችላል። ደነገጠች፥
ፈለግሁት፥ አላገኘሁትም፥
ጠራሁት፥ ነገር ግን አልመለሰልኝም።
7ከተማይቱን የሚዞሩት ጠባቂዎች አገኙኝ፥
መቱኝ፥ አቈሰሉኝም፥
ቅጥር ጠባቂዎችም የዓይነ ርግብ መሸፈኛዬን ወሰዱት።
8እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ አስምላችኋለሁ፥
ውዴን ያገኛችሁት እንደሆነ፥
እኔ ከፍቅር የተነሣ መታመሜን ንገሩት።
9አንቺ በሴቶች ዘንድ የተዋብሽ ሆይ፥
ከሌላ ወዳጅ ይልቅ ፍቅረኛሽ ምን አለው?
ይህን የሚያህል የምታስምይን?
ከሌላ ወዳጅ ይልቅ ፍቅረኛሽ ምን አለው?
10ውዴ ብሩህና ቀይ ነው፥
ከእልፍ የተመረጠ ነው።
11ራሱ ምዝምዝ ወርቅ ነው፥
ጸጉሩ የተዝረፈረፈ ነው፥ እንደ ቁራም ጥቁር ነው።
12ዐይኖቹ በውሃ ምንጮች አጠገብ እንዳሉ
በወተት እንደ ታጠቡ በፈሳሽ ውኃ አጠገብ እንደ ተቀመጡ
እንደ ርግቦች ናቸው።
13ጉንጩና ጉንጩ የሽቱ መደብ
እርከን እንዳለበት እንደ ሽቱ አትክልት ናቸው፥
ከንፈሮቹ እንደ አበቦች ናቸው፥
የሚፈስስ ከርቤንም ያንጠበጥባሉ።
14እጆቹ የቢረሌ ፈርጥ ያለበት የወርቅ ቀለበት ናቸው፥
አካሉ በሰንፔር ያጌጠ የዝሆን ጥርስ ነው።
15እግሮቹ በምዝምዝ ወርቅ ላይ የተመሠረቱ
የዕብነ በረድ ምሰሶች ናቸው፥
መልኩ እንደ ሊባኖስ፥ እንደ ዝግባ ዛፍ ምርጥ ነው#5፥15 ኃይልንና ቁመናን ያመለክታል።
16አፉ እጅግ ጣፋጭ ነው፥ እርሱም ፈጽሞ ያማረ ነው፥
እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥
ውዴ ይህ ነው፥ ባልንጀራዬም ይህ ነው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ