ወደ ቲቶ 2
2
ስለ ትክክለኛ የእምነት ትምህርት
1አንተ ግን ከእውነተኛ አስተምሮ ጋር የሚጣጣመውን ነገር አስተምር። 2ሽማግሌዎች በመጠን የሚኖሩ፥ ክብራቸውን የሚጠብቁ፥ ራሳቸውን የሚቈጣጠሩ፥ በእምነትና በፍቅር በመጽናትም በእውነት የጸኑ እንዲሆኑ ምከራቸው፤ 3እንዲሁም በዕድሜ የገፉ ሴቶች በመልካም ጠባያቸው የተቀደሱ፥ የማያሙ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ ያልተገዙ፥ በጎ የሆነውን ነገር የሚያስተምሩ እንዲሆኑ ንገራቸው፤ 4እነርሱም ወጣት ሴቶችን ባሎቻቸውንና ልጆቻቸውን እንዲወድዱ ያስተምሩአቸው፤ 5እንዲሁም በእነርሱ አማካይነት የእግዚአብሔር ቃል እንዳይሰደብ ራሳቸውን የሚቈጣጠሩ፥ ንጹሖች፥ በቤታቸው ውስጥ ሥራቸውን በደንብ የሚያከናውኑ፥ በጎዎች፥ ለባሎቻቸው የሚታዘዙ እንዲሆኑ ይምከሩአቸው። 6ጐልማሶችም እንዲሁ ራሳቸውን እንዲቈጣጠሩ ምከራቸው። 7በነገር ሁሉ የመልካም ሥራ ምሳሌ በመሆን ራስህን አሳይ፤ በትምህርትህም ጽኑ እውነትንና ቅንነትን ግለጥ፤ 8የሚቃወም ሰው ስለ እኛ የሚናገረውን መጥፎ ነገር ሲያጣ እንዲያፍር እውነተኛና የማይነቀፍ ቃልን ተናገር። 9ባርያዎች ለገዛ ጌቶቻቸው እንዲገዙና በነገር ሁሉ ደስ እንዲያሰኙአቸው ንገራቸው፤ እንዲሁም ሳይቃወሙና 10ሳይሰርቁ በጎ ታማኝነትን ሁሉ እያሳዩ ስለ መድኃኒታችን ስለ እግዚአብሔር የሚሆነውን ትምህርት በሁሉ ነገር እንዲያስመሰግኑ ምከራቸው።
11ሰዎችን ሁሉ የሚያድነው የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤ 12ይህም ጸጋ፥ ኀጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን ራሳችንን በመቈጣጠርና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ይመክረናል፤ 13እንዲሁም የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እንድንጠብቅ ያስተምረናል፤ 14መድኃኒታችንም ከኃጢአት ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።
15ይህንንም በሙሉ ሥልጣን ተናገርና ምከር፤ ገሥጽም፤ ማንም አይናቅህ።
Currently Selected:
ወደ ቲቶ 2: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ