መጽሐፈ ጥበብ 1

1
ጥበብ
ጥበብና የሰው ልጅ ዕጣ፥
ትክክለኛ ፍርድን ስለ መሻት
1እናንተ የምድር ገዥዎች ሆይ፥#1ዜ.መ. 29፥17፤ መዝ. 2፥10፤ ኢሳ. 26፥9። ጽድቅን#1፥1 ጽድቅ በመጽሐፈ ጥበብ 8፥7 ከተዘረዘሩት በጎ ልምዶችና ምግባሮች የሚሰፋ ምስጢር አለው። አፍቅሩ፤
ጌታን በመልካምነት አስቡት፥ በቅን ልብም ፈልጉት፤#ሲራ. 1፥25።
2እርሱ በማይፈታተኑት ዘንድ ይገኛልና፤
በሚታመኑት ዘንድ ይገለጣልና።#1ዜ.መ. 28፥9።
3ቀና ያልሆኑ ሐሳቦች ሕዝብን ከእግዚአብሔር ይለያያሉ፤
ኃይሉም ከተፈታተኗት ማስተዋል የጐደላቸውን ታሳፍራቸዋለች።#ኢሳ. 59፥2።
4ጥበብ በአጥፊ ነፍስ፥ ለኃጢአት ባደረ ሥጋም አታድርምና።#ሲራ. 15፥7፤ ሮሜ 7፥14።
5ሰውን የሚያስተምር#1፥5 ትምህርት በዚህና በሌላም ስፍራ ለጥበብ ስያሜ የዋለ ነው። ቅዱስ መንፈስ አታላይነት ይሸሻል፤
ማስተዋል የጎደለውን አስተሳሰብ ይርቃል፤
ትክክለኛነት የጎደለውን አመል ባየ ጊዜም ያፈገፍጋልና።#ኢሳ. 63፥10።
6ጥበብ የሰው ልጅ ወዳጅ የሆነች መንፈስ ናት፤
ክፉ ተናጋሪን ግን ከስድቡ ነጻ አታደርገውም፤
እግዚአብሔር ለውስጣዊ ማንነቱ ምስክር ነውና፥
ልቡን በጥልቀት ይመለከታል፤ የአንደበቱንም ቃል ይሰማል። #ኤር. 17፥10፤ ኤር. 23፥24።
7የጌታ መንፈስ ዓለሙን ስለ ሞላው፤#ጥበ. 12፥1። ሁሉንም ነገር የያዘ የሚባለውን ሁሉ ያውቃልና።#1፥7 እዚህ ላይ የጌታ መንፈስ የሚለው ሐረግ በጰራቅሊጦስ በዓል በሚደረገው ሥርዓተ አምልኮ ላይ መንፈስ ቅዱስ ይወክላል።
8ስለዚህ ክፉ ቃል የሚናገር ከእርሱ አይሰወርም፤ ደም መላሿ ፍትሕም ለፍርድ ስትገለጥ አታልፈውም።#ምሳ. 19፥5።
9የክፉው ምክር ይመረመራል፤
የቃሉም ማስረጃ ለበደሉ መቀጣጫ ከጌታ ፊት ይቀርባል።
10የቀናኢ ጆሮ ሁሉን ነገር ይሰማልና፥#ዘኍ. 14፥27።
የማጉረምረም ድምፅ እንኳን ሳይሰማ አያመልጥም።
11እንግዲያውስ ከረብ የለሽ ማጉረምረም ተጠበቅ፤
ከሐሜትም አንደበትህን ከልክል፤#1፥11 ሐሜት እዚህ ላይ የሚያመለክተው በእግዚአብሔርና በጥበቃው ላይ የሚደረግ የድፍረት ንግግር ነው።
ምክንያቱም በምሥጢር የተነገረ ምላሽ ማሳየቱ፤
ውሸታምም አፍ ነፍስን ለሞት መስጠቱ አይቀርም።
12በተሳሳተ አኗኗራችሁ በራሳችሁ ላይ ሞትን አትጋብዙ፤
በእጃችሁም ሥራ ጥፋትን አታምጡ።
13እግዚአብሔር ሞትን አልፈጠረም፤
ሕያዋንንም በማጥፋት አይደሰትምና።
14እርሱ እንዲኖሩ ሁሉንም ፈጠረ፤
የዓለም ፍጥረታት ጤነኞች ናቸው፤
በእነርሱም ዘንድ የጥፋት መርዝ አልነበረም፤
የሞትም ግዛት በምድር ላይ አልነበረም።
15ትክክለኛነት ዘላለማዊ ነውና።
ሕይወት በክፉዎች ዐይን
16ክፉዎች በቃላቸው፥ በሥራቸውም ሞትን ይጠሩታል፤
ወዳጅ አድርገውት ስለ እርሱ ራሳቸውን ያደክማሉ፤
የእርሱ ናቸውና ከእርሱ ጋር ይዋዋላሉ።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ