ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 13
13
ስለ ፍቅር
1የሰውን ሁሉ ቋንቋ ባውቅ፥ የመላእክትንም ሁሉ ቋንቋ ባውቅ፥ ነገር ግን ፍቅር ከሌለኝ እንደሚጮህ ነሐስ፥ ወይም እንደሚመታ ከበሮ#ግሪኩ “እንደሚንሿሿው ጸናጽል” ይላል። መሆኔ ነው። 2#ማቴ. 17፥20፤ 21፥21፤ ማር. 11፥23። ትንቢት ብናገር፥ የተሰውረውን ሁሉ፥ ጥበብንም ሁሉ ባውቅ፥ ተራራ እስከ ማፍለስ የሚያደርስ ፍጹም እምነትም ቢኖረኝ ፍቅር ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። 3ገንዘቤን ሁሉ ለምጽዋት ብሰጥ፥ ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል ብሰጥ፥ ነገር ግን ፍቅር ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም።
4ፍቅር ያስታግሣል፤ ፍቅር ያስተዛዝናል፤ ፍቅር አያቀናናም፤ ፍቅር አያስመካም፤ ፍቅር ልቡናን አያስታብይም። 5ብቻዬን ይድላኝ አያሰኝም፤#ግሪኩ “የማይገባውን አያደርግም” ይላል። አያበሳጭም፤ ክፉ ነገርንም አያሳስብም። 6ጽድቅን በመሥራት ደስ ያሰኛል እንጂ፥ ግፍን በመሥራት ደስ አያሰኝም። 7በሁሉ ያቻችላል፤ በሁሉም ያስተማምናል፤ በሁሉም ተስፋ ያስደርጋል፥ በሁሉም ያስታግሣል።
8ፍቅር ለዘወትር አይጥልም፤ ትንቢት የሚናገርም ያልፋል፤ ይሻራልም፤ በልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገርም ያልፋል፤ ይቀራል፤ የሚራቀቅም ያልፋል፤ ይጠፋል።#ምዕ. 13 ከቍ. 4 እስከ 8 ግሪኩ የነገሩን ስም እንደ ሰብአዊ በማድረግ “ፍቅር ይታገሣል ... ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም ትንቢት ቢሆን ግን ይሻራል ልሳኖች ቢሆኑ ይቀራሉ ዕውቀትም ቢሆን ይቀራል” ይላል። 9በየገጹ ጥቂት ጥቂት እናውቃለንና፤ ጥቂት ጥቂት ትንቢትም እንናገራለንና። 10ፍጹም የሆነ ሲመጣ ግን ያ ተከፍሎ የነበረው ይሻራል። 11እኔ ልጅ በነበርሁ ጊዜ እንደ ልጅ እናገር ነበር፤ እንደ ልጅም አስብ ነበር፤ እንደ ልጅም እመክር ነበር፤ በአደግሁ ጊዜ ግን የልጅነትን ጠባይ ሁሉ ሻርሁ። 12አሁን ግን ታወቀኝ፤ በግልጥም ተረዳኝ፤#“ታወቀኝ በግልጥም ተረዳኝ” የሚለው በግሪኩ የለም። በመስታወትም እንደሚያይ ሰው ዛሬ በድንግዝግዝታ እናያለን፤ ያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን፤ አሁን በከፊል፥ ኋላ ግን እንደ ተገለጠልኝ መጠን ሁሉን አውቃለሁ። 13አሁንም እነዚህ ሦስቱ እምነት፥ ተስፋና ፍቅር ጸንተው ይኖራሉ፤ ከሁሉ ግን ፍቅር ይበልጣል።
Currently Selected:
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 13: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ