የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 1 6

6
በዐ​መ​ፀ​ኞች ዳኝ​ነት መከ​ራ​ከር ስለ​ማ​ይ​ገባ
1 # 1ቆሮ. 10፥23። እን​ግ​ዲህ በሚ​ነ​ቅፉ ሰዎች ዘንድ ልት​ከ​ራ​ከሩ አት​ድ​ፈሩ፤ ከጓ​ደ​ኛው ጋር በዐ​መ​ፀ​ኞች ዘንድ ሊከ​ራ​ከር የሚ​ችል አለን? በደ​ጋ​ጎች ዘንድ አይ​ደ​ለ​ምን? ከባ​ል​ን​ጀ​ራው ጋር ክር​ክር ያለው ቢኖ​ርም በቅ​ዱ​ሳን ዘንድ ይከ​ራ​ከር፤ በሚ​ነ​ቅ​ፉና በዐ​መ​ፀ​ኞች ዘንድ ግን አይ​ደ​ለም።#ምዕ. 6 ቍ. 1 ግእዙ “እን​ግ​ዲህ በሚ​ነ​ቅፉ ሰዎች ልት​ከ​ራ​ከሩ አት​ድ​ፈሩ፤ ከጓ​ደ​ኛው ጋር በዐ​መ​ፀ​ኞች ዘንድ ሊከ​ራ​ከር የሚ​ችል አለን? በደ​ጋ​ጎች ዘንድ አይ​ደ​ለ​ምን” የሚል ዘር በመ​ጨ​መር ከግ​ሪኩ ይለ​ያል። 2ቅዱ​ሳን ሰውን ሁሉ እን​ደ​ሚ​ዳኙ አታ​ው​ቁ​ምን? እና​ንተ ሰውን ሁሉ የም​ት​ዳኙ ከሆ​ና​ችሁ ይህን ትን​ሹን ነገር ልት​ዳኙ አይ​ገ​ባ​ች​ሁ​ምን? 3የዚ​ህ​ንስ ዓለም ዳኝ​ነት ተዉ​ትና በመ​ላ​እ​ክት ስንኳ እን​ድ​ን​ፈ​ርድ አታ​ው​ቁ​ምን? 4ነገር ግን የዚህ ዓለም ክር​ክር ያላ​ቸው ሰዎች ቢኖሩ በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን የተ​ሾሙ የበ​ታች ወን​ድ​ሞች ይስ​ሙ​አ​ቸው። 5ይህ​ንም የም​ላ​ችሁ ስዘ​ል​ፋ​ችሁ ነው፤ እን​ግ​ዲህ ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸሁ ወን​ድ​ማ​ማ​ቾ​ችን ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ጋር ማስ​ታ​ረቅ የሚ​ችል ሽማ​ግሌ የለ​ምን? 6ነገር ግን ወን​ድም ከወ​ን​ድሙ ጋር ይካ​ሰ​ሳል፤ ይህም በማ​ያ​ምኑ ፊት ይደ​ረ​ጋል።
7እን​ግ​ዲህ ፀብና ክር​ክር ካላ​ችሁ፥ ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ጀምሮ ውር​ደት እን​ደ​ሚ​ሆ​ን​ባ​ችሁ ዕወቁ፤ እን​ግ​ዲ​ያማ እን​ዴት አት​ነ​ጠ​ቁም? እን​ዴ​ትስ አት​ገ​ፉም? 8አሁ​ንም ቢሆን፥ እና​ንተ ዐመ​ፀ​ኞ​ችና ቀማ​ኞች ናችሁ፤ እን​ደ​ዚ​ህም ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን ትበ​ድ​ላ​ላ​ችሁ።
መን​ግ​ሥተ ሰማ​ያ​ትን ስለ​ማ​ይ​ወ​ርሱ ሰዎች
9ዐመ​ፀ​ኞች የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት እን​ደ​ማ​ይ​ወ​ርሱ አታ​ው​ቁ​ምን? አያ​ስ​ቱ​አ​ችሁ፤ ሴሰ​ኞች፥ ወይም ጣዖ​ትን የሚ​ያ​መ​ልኩ፥ ወይም አመ​ን​ዝ​ራ​ዎች፥ ወይም ቀላ​ጮች፥ ወይም በወ​ንድ ላይ ዝሙ​ትን የሚ​ሠሩ፥ የሚ​ሠ​ሩ​ባ​ቸ​ውም ቢሆኑ፤ 10ሌቦች፥ ወይም ቀማ​ኞች፥ ወይም ሰካ​ሮች፥ ወይም ተሳ​ዳ​ቢ​ዎች፥ ወይም ነጣ​ቂ​ዎች፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት አይ​ወ​ር​ሱ​አ​ትም። 11እን​ግ​ዲህ እና​ንተ እን​ዲህ ስት​ሆኑ እነ​ማን ናችሁ? ነገር ግን በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም በአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም መን​ፈስ ታጥ​ባ​ች​ኋል፤ ተቀ​ድ​ሳ​ች​ኋል፤ ጸድ​ቃ​ች​ኋ​ልም።
ሰው​ነ​ትን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር ስለ ማድ​ረግ
12በሆ​ነው ሁሉ ላይ ሥል​ጣን አለኝ፤ ግን ሁሉ የሚ​ጠ​ቅ​መኝ አይ​ደ​ለም፤ ሁሉም ይቻ​ለ​ኛል፤ ነገር ግን በእኔ ላይ እን​ዲ​ሠ​ለ​ጥን የማ​ደ​ር​ገው ምንም የለም። 13መብል ለሆድ ነው ፤ ሆድም ለመ​ብል ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ሁለ​ቱ​ንም ይሽ​ራ​ቸ​ዋል፤ ሥጋ​ች​ሁም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው እንጂ ለዝ​ሙት አይ​ደ​ለም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሥ​ጋ​ችሁ ነው። 14ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ከሙ​ታን ያስ​ነ​ሣው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኛ​ንም በከ​ሃ​ሊ​ነቱ ያስ​ነ​ሣ​ናል። 15ሥጋ​ችሁ የክ​ር​ስ​ቶስ አካል እንደ ሆነ አታ​ው​ቁ​ምን? እን​ግ​ዲህ የክ​ር​ስ​ቶ​ስን አካል ወስ​ዳ​ችሁ የአ​መ​ን​ዝራ አካል ታደ​ር​ጉ​ታ​ላ​ች​ሁን? አይ​ገ​ባም። 16#ዘፍ. 2፥24። ከአ​መ​ን​ዝራ ጋር የተ​ገ​ናኘ ከእ​ር​ስዋ ጋር አንድ አካል እን​ዲ​ሆን አታ​ው​ቁ​ምን? መጽ​ሐፍ፥ “ሁለቱ አንድ አካል ይሆ​ናሉ” ብሎ​አ​ልና። 17ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር የተ​ዋ​ሐደ ግን ከእ​ርሱ ጋር አንድ መን​ፈስ ይሆ​ናል። 18ከዝ​ሙት ራቁ፤ ኀጢ​አት የሚ​ሠራ ሰው ሁሉ ከሥ​ጋው ውጭ ይሠ​ራ​ልና፤ ዝሙ​ትን የሚ​ሠራ ግን ራሱ በሥ​ጋው ላይ ኀጢ​አ​ትን ይሠ​ራል። 19#1ቆሮ. 3፥16፤ 2ቆሮ. 6፥16። ሥጋ​ችሁ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለተ​ቀ​በ​ላ​ች​ሁት በእ​ና​ንተ አድሮ ላለ ለመ​ን​ፈስ ቅዱስ ቤተ መቅ​ደስ እንደ ሆነ አታ​ው​ቁ​ምን? ለራ​ሳ​ች​ሁም አይ​ደ​ላ​ች​ሁም። 20በዋጋ ተገ​ዝ​ታ​ች​ኋ​ልና፤ ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በሥ​ጋ​ችሁ አክ​ብ​ሩት።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ