መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 14
14
ዮናታን በፍልስጥኤማውያን ላይ አደጋ እንደ ጣለ
1በነጋም ጊዜ፥ የሳኦል ልጅ ዮናታን ጋሻ ጃግሬውን፥ “ና፤ በዚያ በኩል ወዳለው ወደ ፍልስጥኤማውያን ሰፈር እንለፍ” አለው፤ ለአባቱም አልነገረውም። 2ሳኦልም በመጌዶን ባለው በሮማኑ ዛፍ በታች በኮረብታው ላይ ተቀምጦ ነበር፤ ከእርሱም ጋር የነበረው ሕዝብ ስድስት መቶ የሚያህል ሰው ነበረ። 3የዔሊ ልጅ፥ የፊንሐስ ልጅ፥ የዮካብድ ወንድም፥ የአኪጦብ ልጅ በሴሎ ለእግዚአብሔር ካህን የሆነ፥ ኤፉድም የለበሰ አኪያ አብሮ ነበር፤ ሕዝቡም ዮናታን እንደ ሄደ አላወቁም ነበር። 4ዮናታንም ወደ ፍልስጥኤማውያን ሰፈር ሊሻገርበት በወደደው መተላለፊያ መካከል በወዲህ አንድ ሾጣጣ፥ በወዲህም አንድ ሾጣጣ ድንጋዮች ነበሩ፤ የአንዱም ስም ባዚስ፥ የሁለተኛውም ስም ሴና ነበረ። 5አንደኛዋ መንገድ በማኪማስ አንጻር በመስዕ በኩል የምትመጣ ናት፤ ሁለተኛዋም መንገድ በገባዖን አንጻር በአዜብ በኩል የምትመጣ ነበረች።
6ዮናታንም ጋሻ ጃግሬውን፥ “ና፥ ወደ እነዚህ ቈላፋን ሰፈር እንለፍ፤ በብዙ ወይም በጥቂት ማዳን እግዚአብሔርን አያስቸግረውምና ምናልባት እግዚአብሔር ይረዳን ይሆናል” አለው። 7ጋሻ ጃግሬውም፥ “ልብህ ያሰኘህን ሁሉ አድርግ እነሆ፥ ከአንተ ጋር ነኝ፤ እንደ አንተ ልብ የእኔም ልብ እንዲሁ ነው” አለው። 8ዮናታንም አለው፥ “እነሆ፥ ወደ ሰዎቹ እናልፋለን፤ ወደ እነርሱም እንቀርባለን፤ 9እነርሱም፦ እስክንነግራችሁ ድረስ ርቃችሁ ቈዩ ቢሉን ርቀን እንቆማለን፤ ወደ እነርሱም አንወጣም። 10ነገር ግን ወደ እኛ ውጡ ቢሉን እግዚአብሔር በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶአቸዋልና እንወጣለን፤ ምልክታችንም ይህ ይሆናል።” 11ሁለታቸውም ወደ ፍልስጥኤማውያን ሰፈር ገቡ፤ ፍልስጥኤማውያንም “እነሆ፥ ዕብራውያን ከተሸሸጉበት ጕድጓድ ይወጣሉ” አሉ። 12የሰፈሩም ሰዎች፦ ዮናታንንና ጋሻ ጃግሬውን “ወደ እኛ ውጡ፤ አንድ ነገርንም እንነግራችኋለን” አሉ። ዮናታንም ጋሻ ጃግሬውን “እግዚአብሔር በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጥቶአቸዋልና ተከተለኝ” አለው። 13ዮናታንም በእጁና በእግሩ ወጣ፤ ጋሻ ጃግሬውም ከእርሱ ጋር ነበረ፤ ዮናታንም ፊቱን መልሶ ገደላቸው፤ ጋሻ ጃግሬውም ተከትሎ ገደላቸው። 14የዮናታንና የጋሻ ጃግሬውም በወንጭፍና በዱላ የመጀመሪያ ግድያቸው በአንድ ትልም እርሻ መካከል ሃያ ያህል ሰው ነበረ። 15በሰፈሩና በእርሻውም ድንጋጤ ሆነ፤ በሰፈሩ የተቀመጡ ሕዝብና የሚዋጉትም ሁሉ ተሸበሩ፤ መዋጋትም አልቻሉም፤ ምድሪቱም ተናወጠች፤ ከእግዚአብሔርም ዘንድ ታላቅ ድንጋጤ መጣ።
የፍልስጥኤማውያን ድል መሆን
16በብንያም ገባዖን ያሉ የሳኦል ዘበኞችም ተመለከቱ፤ እነሆም፥ ሠራዊቱ ወዲህና ወዲያ እየተራወጡ ተበታተኑ። 17ሳኦልም ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሕዝብ፥ “እስኪ ተቋጠሩ፤ ከእኛ ዘንድ የሄደ ማን እንደ ሆነ ተመልከቱ” አላቸው። በተቋጠሩም ጊዜ እነሆ፥ ዮናታንና ጋሻ ጃግሬው በዚያ አልተገኙም። 18በዚያም ቀን አኪያ በእስራኤል ልጆች ፊት ኤፉድ ይለብስ ነበርና ሳኦል፥ “ኤፉድን አምጣ” አለው። 19ሳኦልም ከካህኑ ጋር ሲነጋገር በፍልስጥኤማውያን መንደር ግርግርታ እየበዛ ሄደ፤ ሳኦልም ካህኑን፥ “እጅህን መልስ” አለው። 20ሳኦልና ከእርሱም ጋር የነበሩት ሕዝብ ሁሉ ተሰብስበው ወደ ውጊያው መጡ፤ እነሆም፥ የእያንዳንዱ ሰው ሰይፍ በባልንጀራው ላይ ነበረ፤ እጅግም ታላቅ ሽብር ሆነ። 21ቀድሞ ከፍልስጥኤማውያን ጋር የነበሩና ወደ ሠራዊቱ የወጡ አገልጋዮችም ከሳኦልና ከዮናታን ጋር ወደ ነበሩ እስራኤላውያን ለመሆን ተመለሱ። 22በተራራማውም በኤፍሬም ሀገር የተሸሸጉት እስራኤል ሁሉ ፍልስጥኤማውያን እንደ ሸሹ በሰሙ ጊዜ እነርሱ ደግሞ ሊዋጉአቸው ተከተሉአቸው። 23እግዚአብሔርም በዚያ ቀን እስራኤልን አዳነ፤ ውጊያውም በባሞት በኩል አለፈ። ከሳኦልም ጋር የነበሩ ሕዝብ ሁሉ ዐሥር ሺህ የሚያህሉ ሰዎች ነበሩ፤ ውጊያውም በተራራማው በኤፍሬም ከተማ ሁሉ ተበታትኖ ነበር።
ከጦርነት በኋላ የተፈጸሙ ድርጊቶች
24ሳኦልም በዚያ ቀን ትልቅ በደል ፈጸመ፤ “ጠላቶቼን እስክበቀል እስከ ማታ ድረስ መብል የሚበላ ሰው ርጉም ይሁን” ብሎ ሕዝቡን አምሎአቸው ነበርና። ሕዝቡም ሁሉ እህል አልቀመሱም። ሀገሩም ሁሉ ምሳ አልበላም። 25ብዙ ንብ ያለበት የማር ቀፎም በዱሩ ይታይ ነበር። 26ሕዝቡም ማር ወደ አለበት ቀፎ ሄዱ፤ እርስ በርሳቸውም ይነጋገሩ ነበር። እነሆም፥ ሕዝቡ መሐላውን ፈርቶ ነበርና ማንም እጁን አንሥቶ ወደ አፉ አላደረገም። 27ዮናታን ግን አባቱ ሕዝቡን ባማለ ጊዜ አልሰማም ነበር፤ እርሱም በእጁ ያለችውን በትር አንሥቶ ጫፍዋን ወደ ወለላው ነከረ፤ እጁንም ወደ አፉ አደረገ፤ ዐይኑም በራ። 28ከሕዝቡም አንድ ሰው መልሶ፥ “አባትህ፦ ዛሬ መብል የሚበላ ሰው ርጉም ይሁን ብሎ ሕዝቡን መሐላ አምሎአቸዋል” አለው፤ ሕዝቡም ደከሙ። 29ዮናታንም “አባቴ ምድሪቱን አስቸገረ፤ ከዚህ ማር ጥቂት ብቀምስ ዐይኔ እንደ በራ እዩ፤ 30ይልቅስ ሕዝቡ ካገኙት ከጠላቶቻቸው ምርኮ በልተው ቢሆን ኑሮ የፍልስጥኤማውያን መመታት ይበልጥ አልነበረምን?” አለ።
31በዚያም ቀን ፍልስጥኤማውያንን በማኪማስ#ዕብ. “ከማኪማስ እስከ ኤሎን” የሚል ይጨምራል። መቱአቸው፤ ሕዝቡም እጅግ ደከሙ። 32ሕዝቡም ወደ ምርኮ ሄዱ፤ በጎችን፥ በሬዎችንም፥ ጥጆችንም ወስደው እንዳገኙ በምድር ላይ አረዱ፤ ሕዝቡም ከደሙ ጋር በሉ። 33ለሳኦልም፥ “እነሆ፥ ሕዝቡ ከደሙ ጋር በመብላታቸው እግዚአብሔርን በደሉ” ብለው ነገሩት። ሳኦልም በጌቴም “ትልቅ ድንጋይ አንከባልላችሁ አቅርቡልኝ” አላቸው። 34ሳኦልም፥ “በሕዝቡ መካከል እየዞራችሁ፦ እያንዳንዱ ሰው በሬውንና በጉን ወደ እኔ ያቅርብ፥ በዚህም እረዱና ብሉ፤ ከደሙም ጋር በመብላታችሁ እግዚአብሔርን አትበድሉ” በሉአቸው አለ። እያንዳንዱም ሰው ሁሉ በእጁ ያለውን በዚያች ሌሊት አቀረበ፤ በዚያም አረደው። 35ሳኦልም በዚያ ለእግዚአብሔር መሠዊያን ሠራ፤ ይኸውም ሳኦል ለእግዚአብሔር የሠራው የመጀመሪያ መሠዊያ ነው።
36ሳኦልም፥ “ፍልስጥኤማውያንን በሌሊት ተከትለን እንውረድ፤ እስኪነጋም ድረስ እንበዝብዛቸው፤ አንድ ሰው እንኳ አናስቀርላቸው” አለ። እነርሱም፥ “ደስ የሚያሰኝህን ሁሉ አድርግ” አሉት። ካህኑም፥ “ወደ እግዚአብሔር እንቅረብ” አለ። 37ሳኦልም፥ “ልውረድና ፍልስጥኤማውያንን ልከተልን? በእስራኤልስ እጅ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህን?” ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀው። በዚያ ቀን ግን እግዚአብሔር አልመለሰለትም። 38ሳኦልም፥ “እናንተ የእስራኤል አለቆችን ሁሉ ወደዚህ አቅርቡ፤ ዛሬ ይህ ኀጢኣት በማን እንደ ሆነ ዕወቁ፤ ተመልከቱም፤ 39እስራኤልን የሚያድን ሕያው እግዚአብሔርን! ኀጢኣቱ በልጄ በዮናታን ቢሆን ፈጽሞ ይሞታል” አለ። ከሕዝቡም ሁሉ አንድ የመለሰለት ሰው አልነበረም። 40እስራኤልንም ሁሉ፥ “እናንተ አንድ ወገን ትሆናላችሁ፤ እኔና ልጄ ዮናታንም አንድ ወገን እንሆናለን” አለ። ሕዝቡም ሳኦልን፥ “ደስ የሚያሰኝህን አድርግ” አሉት። 41ሳኦልም እግዚአብሔርን፥ “የእስራኤል አምላክ ሆይ፥ ለእኔ ለባሪያህ ዛሬ ያልመለስህልኝ ስለ ምንድን ነው? ይህች በደል በእኔ፥ በልጄ በዮናታንም እንደ ሆነች አቤቱ የእስራኤል አምላክ ሆይ፥ ተናገር። ዕጣው ይህን የሚገልጥ ከሆነ ለሕዝብህ ለእስራኤል እውነትን ግለጥ፥” አለ። ዕጣም በዮናታንና በሳኦል ላይ ወጣ፤ ሕዝቡም ነፃ ወጣ። 42ሳኦልም፥ “በእኔና በዮናታን መካከል ዕጣ አጣጥሉን፤ እግዚአብሔር ዕጣ ያወጣበትም ይሞታል” አላቸው። ሕዝቡም ሳኦልን፥ “እንዲህ ያለ ነገር አይሆንም” አሉት፤ ሳኦልም ሕዝቡን እንቢ አላቸው። በእርሱና በልጁ በዮናታን መካከልም ዕጣ አጣጣሉ። ዕጣውም በልጁ በዮናታን ላይ ወጣ።
43ሳኦልም ዮናታንን፥ “ያደረግኸውን ንገረኝ” አለው፤ ዮናታንም፥ “በእጄ ባለው በበትሬ ጫፍ ጥቂት ማር በርግጥ ቀምሻለሁ፤ እነሆኝ፥ እሞታለሁ” ብሎ ነገረው። 44ሳኦልም፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ያድርግብኝ፤ እንዲህም ይጨምርብኝ፤ ዛሬ ፈጽመህ ትሞታለህ” አለ። 45ሕዝቡም ሳኦልን፥ “በውኑ በእስራኤል ዘንድ ታላቅ መድኀኒት ያደረገ ዮናታን ዛሬ ይሞታልን? ይህ አይሁን፤ ዛሬ ለሕዝቡ ከእግዚአብሔር ጋር አድርጎአልና ሕያው እግዚአብሔርን! ከራሱ ጠጕር አንዲት በምድር ላይ አትወድቅም” አሉት። ሕዝቡም ያን ጊዜ ስለ ዮናታን ጸለዩ፤ እርሱም አልተገደለም። 46ሳኦልም ፍልስጥኤማውያንን ከመከተል ተመለሰ፤ ፍልስጥኤማውያንም ወደ ስፍራቸው ሄዱ።
የሳኦል ዘመነ መንግሥትና ቤተ ሰቡ
47ሳኦልም መንግሥቱን በእስራኤል ላይ አጸና፤ በዙሪያውም ካሉት ከጠላቶቹ ሁሉ ጋር፥ ከሞዓብም፥ ከአሞንም ልጆች፥ ከኤዶምያስም፥ ከቢዖርም፥ ከሱባም ነገሥታት፥ ከፍልስጥኤማውያንም ሁሉ ጋር ይዋጋ ነበር፤ በየሄደበትም ሁሉ ድል ይነሣ ነበር። 48እርሱም ጀግና ነበረ፤ አማሌቃውያንንም መታ፤ እስራኤልንም ከዘራፊዎቹ እጅ አዳነ።
49የሳኦልም ወንዶች ልጆች ዮናታን፥ የሱዊ፥ ሚልኪሳ ነበሩ፤ የሁለቱም ሴቶች ልጆቹ ስም ይህ ነበረ፤ የታላቂቱ ስም ሜሮብ፥ የታናሺቱም ስም ሜልኮል ነበረ። 50የሳኦልም ሚስት ስም የአኪማኦስ ልጅ አኪናሆም ነበረች፤ የሠራዊቱም አለቃ ስም የሳኦል አጎት የኔር ልጅ አቤኔር ነበረ። 51የሳኦልም አባት ቂስ ነበረ፤ የአቤኔርም አባት የአብኤል ልጅ የያሚን ልጅ ኔር ነበረ።
52በሳኦልም ዘመን ሁሉ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ጽኑ ውጊያ ነበረ፤ ሳኦልም ጽኑ ወይም ኀያል ሰው ባየ ጊዜ ወደ እርሱ ይሰበስብ ነበር።
Currently Selected:
መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 14: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ