መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 20
20
ዮናታን ዳዊትን እንደ ረዳው
1ዳዊትም ከአውቴዘራማ ሸሸ፤ ወደ ዮናታንም መጣ፤ እንዲህም አለው፥ “ምን አደረግሁ? ምንስ በደልሁ? ነፍሴንም ይሻት ዘንድ በአባትህ ፊት ጥፋቴና ኀጢአቴ ምንድን ነው?” 2ዮናታንም፥ “ይህንስ ያርቀው፤ አትሞትም፤ እነሆ፥ አባቴ አስቀድሞ ለእኔ ሳይገልጥ ትልቅም ሆነ ትንሽ ነገር ቢሆን አያደርግም፤ አባቴስ ይህን ነገር ለምን ይሰውረኛል? እንዲህ አይደለም” አለው። 3ዳዊትም፥ “እኔ በፊትህ ሞገስን እንዳገኘሁ አባትህ በእውነት ያውቃል፤ እርሱም፦ ዮናታን እንዳይቃወም አይወቅ ይላል፤ ነገር ግን ሕያው እግዚአብሔርን! በሕያው ነፍስህም እምላለሁ፤ እኔ እንዳልሁት በእኔና በሞት መካከል አንድ ርምጃ ያህል ቀርቶአል” ብሎ ማለ። 4ዮናታንም ዳዊትን፥ “ነፍስህ ምን ትፈልጋለች? እኔስ ምን ላድርግልህ?” አለው። 5ዳዊትም ዮናታንን አለው፥ “እነሆ ነገ መባቻ ነው፤ በንጉሥም አጠገብ ለምሳ አልቀመጥም፤ እስከ ማታ ድረስ በውጭ በሜዳ እንድሸሸግ አሰናብተኝ ። 6አባትህም ቢፈልገኝ፦ ለዘመዶቹ ሁሉ በዚያ በቤተ ልሔም የዓመት መሥዋዕት አላቸውና ዳዊት ወደ ከተማው ፈጥኖ ይሄድ ዘንድ አጽንቶ ለምኖኛል በለው። 7እርሱም፦ መልካም ነው ቢል ለእኔ ለባሪያህ ሰላም ይሆናል፤ ቢቈጣ ግን ክፋት ከእርሱ ዘንድ በእኔ ላይ እንደ ተቈረጠች ዕወቅ። 8እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ከባሪያህ ጋር አድርገሃልና ለባሪያህ ቸርነትን አድርግ፤ በደል ግን ቢገኝብኝ አንተ ግደለኝ፤ ለምን ወደ አባትህ ታደርሰኛለህ?” 9ዮናታንም፥ “ይህ ከአንተ ይራቅ፤ ከአባቴ ዘንድ ክፋት በላይህ እንደ ተቈረጠች ያወቅሁ እንደ ሆነ በከተማ ባትኖርም እንኳን ወደ አንተ መጥቼ እነግርሃለሁ” አለው። 10ዳዊትም ዮናታንን፥ “አባትህ ስለ እኔ ክፉ ነገር የነገረህ እንደ ሆነ ማን ይነግረኛል?” አለው። 11ዮናታንም ዳዊትን፥ “ና፤ ወደ ሜዳ እንውጣ” አለው። ሁለቱም ወደ ሜዳ ወጡ።
12ዮናታንም ዳዊትን አለው፥ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ያውቃል፤ እስከ ሦስት ቀን ድረስ በዚህ ጊዜ አባቴን መርምሬ እነሆ፥ በዳዊት ላይ መልካም ቢያስብ፥ እነሆ፥ ወደ ሜዳ ወደ አንተ አልልክም፤ ይህም ምልክት ይሁንህ፤#“ይህም ምልክት ይሁንህ” የሚለው በግእዝ ብቻ። 13አባቴም በአንተ ላይ ክፋት ማድረግ ቢወድድ፥ እኔም ባላስታውቅህ፥ በሰላምም ትሄድ ዘንድ ባላሰናብትህ፥ እግዚአብሔር በዮናታን ይህን ያድርግ፤ ይህንም ይጨምር፤ እግዚአብሔርም ከአባቴ ጋር እንደ ነበረ ከአንተ ጋር ይሁን። 14እኔም በሕይወት ሳለሁ ቸርነትን ታደርግልኛለህ፤ 15ብሞትም ቸርነትህን እስከ ዘለዓለም ከቤቴ አትተው፤ ደግሞም እግዚአብሔር የዳዊትን ጠላቶች ሁሉ እያንዳንዱን ከምድር ፊት ባጠፋቸው ጊዜ የዮናታን ስም በዳዊት ቤት ይገኛል።” 16ዮናታንም፥ “እግዚአብሔር ከዳዊት ጠላቶች እጅ ይፈልገው” ብሎ ከዳዊት ቤት ጋር ቃል ኪዳን አደረገ። 17ዮናታንም ዳዊትን እንደ ነፍሱ ይወድድ ነበርና እንደ ገና ማለለት።
18ዮናታንም አለው፥ “ነገ መባቻ ነው፤ መቀመጫህም ባዶ ሆኖ ይገኛልና ትታሰባለህ። 19ሦስት ቀንም ያህል ቈይ፤ ከዚህም በኋላ በፈለገህ ጊዜ ትመጣና ነገሩ በተደረገበት ቀን በተሸሸግህበት ስፍራ ትቀመጣለህ፤ በኤርገብ ድንጋይም አጠገብ ቈይ። 20እኔም በዓላማ ላይ እወረውራለሁ ብዬ ሦስት ፍላጻዎችን ወደ ዓላማው እወረውራለሁ። 21እነሆም፦ ሂድ ፍላጻዎቹን ፈልግ ብዬ ብላቴናውን እልካለሁ፤ ብላቴናውንም፦ እነሆ፥ ፍላጻው ከአንተ ወደዚህ ነው፤ ይዘኸው ወደ እኔ ና ያልሁት እንደ ሆነ፥ ሕያው እግዚአብሔርን! ለአንተ ሰላም ነውና ምንም ክፉ ነገር የለብህም። 22ብላቴናውን ግን፦ እነሆ፥ ፍላጻው ከአንተ ወዲያ ነው ያልሁት እንደ ሆነ፥ እግዚአብሔር አሰናብቶሃልና መንገድህን ሂድ። 23አንተና እኔም ስለ ተነጋገርነው፥ እነሆ፥ እግዚአብሔር ለዘለዓለም በመካከላችን ምስክር ነው።”
24ዳዊትም በሜዳው ተሸሸገ፤ መባቻም በሆነ ጊዜ ንጉሡ ግብር ለመብላት ተቀመጠ። 25ንጉሡም እንደ ቀድሞው በግንቡ አጠገብ በዙፋኑ ላይ ተቀመጠ፤ ዮናታንም ቆመ፤ አቤኔርም በሳኦል አጠገብ ተቀመጠ፤ የዳዊትም ስፍራ ባዶውን ነበረ። 26ሳኦልም፥ “አንድ ነገር ሆኖ ይሆናል፤ ምንአልባትም ንጹሕ አይደለም ይሆናል፤ በእውነትም ንጹሕ አይደለም” ብሎ አስቦአልና በዚያ ቀን ምንም አልተናገረም። 27ከመባቻም በኋላ በማግሥቱ በሁለተኛው ቀን የዳዊት ስፍራ ባዶውን ነበረ፤ ሳኦልም ልጁን ዮናታንን፥ “የእሴይ ልጅ ትናትና ዛሬ ወደ ግብር ያልመጣ ስለምን ነው?” አለው። 28ዮናታንም ለሳኦል፥ “ዳዊት ወደ ከተማው ወደ ቤተ ልሔም ይሄድ ዘንድ ነግሮኝ ተሰናብቶኛል። 29እርሱም፥ “ዘመዶቼ በከተማ ውስጥ መሥዋዕት አላቸውና፥ ወንድሞቼም ጠርተውኛልና እባክህ! አሰናብተኝ፤ አሁንም በዐይኖችህ ሞገስ አግኝቼ እንደ ሆነ ልሂድና ወንድሞቼን ልይ አለ፤ ስለዚህ ወደ ንጉሥ ማዕድ አልመጣም” ብሎ መለሰለት።
30ሳኦልም በዮናታን ላይ እጅግ ተቈጣ፥ “አንተ የከዳተኞች ሴቶች ልጅ! የእሴይን ልጅ ለአንተ ማፈርያ፥ ለእናትህም ኀፍረተ ሥጋ ማፈርያ እንደ መረጥህ እኔ አላውቅምን? 31የእሴይ ልጅ በምድር ላይ በሕይወት በሚኖርበት ዘመን ሁሉ መንግሥትህ አትጸናም፤ አሁንም ሞት የሚገባው ነውና ያን ብላቴና ያመጡት ዘንድ ላክ” አለው። 32ዮናታንም ለአባቱ ለሳኦል፥ “ስለ ምን ይሞታል? ምንስ አደረገ?” ብሎ መለሰለት። 33ሳኦልም ሊገድለው በዮናታን ላይ ጦሩን አነሣ፤#ዕብ. “ወረወረበት” ይላል። ዮናታንም አባቱ ዳዊትን ይገድለው ዘንድ ያች ክፉ ነገር እንደ ተቈረጠች ዐወቀ። 34አባቱ በእርሱ ላይ ክፉ ነገርን ሊያደርግ ስለ ቈረጠ ዮናታን ስለ ዳዊት አዝኖአልና እጅግ ተቈጥቶ ከማዕዱ ተነሣ፤ በመባቻውም በሁለተኛው ቀን ግብር አልበላም።
35እንዲህም ሆነ በነጋው ዮናታን ከዳዊት ጋር ምልክት ለማድረግ ወደ ተቃጠረበት ቦታ ወደ ሜዳ ወጣ፤ ከእርሱም ጋር ታናሽ ብላቴና ነበረ። 36ብላቴናውንም፥ “ሮጠህ የምወረውራቸውን ፍላጻዎች ፈልግልኝ” አለው። ብላቴናውም በሮጠ ጊዜ ዮናታን ፍላጻውን ወደ ማዶ አሳልፎ ወረወረው። 37ብላቴናውም ዮናታን ፍላጻውን ወደ ወረወረበት ስፍራ በመጣ ጊዜ ዮናታን፥ “ፍላጻው ከአንተ ወዲያ ነው” ብሎ ወደ ብላቴናው ጮኸ። 38ዮናታንም ደግሞ፥ “ቶሎ ፍጠን፤ አትቈይ” ብሎ ወደ ብላቴናው ጮኸ፤ የዮናታንም ብላቴና ፍላጻዎቹን ሰብስቦ ወደ ጌታው መጣ። 39ዮናታንና ዳዊት ብቻ ነገሩን ያውቁ ነበር እንጂ ብላቴናው ምንም አያውቅም ነበር። 40ዮናታንም መሣሪያውን ለብላቴናው ሰጥቶ፥ “ሂድ ወደ ከተማ ግባ” አለው። 41ብላቴናውም በሄደ ጊዜ ዳዊት ከኤርገብ ተነሣ፤ በምድርም ላይ በግንባሩ ተደፋ፤ ሦስት ጊዜም ሰገደ፤ እርስ በእርሳቸውም ተሳሳሙ፤ ለረዥም ሰዓትም ተላቀሱ። 42ዮናታንም ዳዊትን፥ “በሰላም ሂድ፤ እነሆ፥ እኛ ሁለታችን በእኔና በአንተ፥ በዘሬና በዘርህ መካከል እግዚአብሔር ለዘለዓለም ምስክር ይሁን ብለን በእግዚአብሔር ስም ተማምለናል” አለው። ዳዊትም ተነሥቶ ሄደ፤ ዮናታንም ወደ ከተማ ገባ።
Currently Selected:
መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 20: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ