የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ቀዳ​ማዊ 25

25
የነ​ቢዩ ሳሙ​ኤል ሞት
1ሳሙ​ኤ​ልም ሞተ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በው አለ​ቀ​ሱ​ለት፤ በአ​ር​ማ​ቴ​ምም በቤቱ ቀበ​ሩት። ዳዊ​ትም ተነ​ሥቶ ወደ ማዖን#ዕብ. “ፋራን” ይላል። ምድረ በዳ ወረደ።
ስለ ዳዊ​ትና ናባል
2በማ​ዖ​ንም የተ​ቀ​መጠ አንድ ሰው ነበረ፤ ከብ​ቱም በቀ​ር​ሜ​ሎስ ነበረ፤ እጅ​ግም ታላቅ ሰው ነበረ፤ ለእ​ር​ሱም ሦስት ሺህ በጎ​ችና አንድ ሺህ ፍየ​ሎች ነበ​ሩት፤ በቀ​ር​ሜ​ሎ​ስም በጎ​ቹን ሊሸ​ልት ሄደ። 3የሰ​ው​ዬ​ውም ስም ናባል፥ የሚ​ስ​ቱም ስም አቤ​ግያ ነበረ፤ ሴቲ​ቱም ደግና ብልህ፥ መል​ክ​ዋም እጅግ የተ​ዋበ ነበረ፤ ሰው​ዬው ግን ጨካ​ኝና ንፉግ ነበረ፤ ግብ​ሩም ክፉ ነበረ።#ዕብ. “ከካ​ሌብ ወገን ነበረ” የሚል ይጨ​ም​ራል። 4ዳዊ​ትም በም​ድረ በዳ ሳለ፥ “ናባል በቀ​ር​ሜ​ሎስ በጎ​ቹን ይሸ​ል​ታል” የሚል ወሬ ሰማ። 5ዳዊ​ትም ዐሥር ብላ​ቴ​ኖ​ችን ላከ፤ ለብ​ላ​ቴ​ኖ​ቹም አለ፥ “ወደ ቀር​ሜ​ሎስ ወጥ​ታ​ችሁ ወደ ናባል ሂዱ፤ በስ​ሜም ሰላም በሉት፤ 6እን​ዲ​ህም በሉት፥ “ደኅ​ን​ነ​ትና ሰላም ለአ​ን​ተና ለቤ​ትህ፥ ለአ​ን​ተም ለሆ​ኑት ሁሉ ይሁን። 7አሁ​ንም በጎ​ችህ እን​ደ​ሚ​ሸ​ለቱ ከእኛ ጋር በም​ድረ በዳ ያሉ ሰዎች ነገ​ሩን፤ እኛም አል​ከ​ለ​ከ​ል​ና​ቸ​ውም፤ በቀ​ር​ሜ​ሎ​ስም በነ​በ​ሩ​በት ዘመን ሁሉ ከመ​ን​ጋ​ቸው ይሰ​ጡን ዘንድ አላ​ዘ​ዝ​ና​ቸ​ውም። 8ብላ​ቴ​ኖ​ች​ህን ጠይ​ቃ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ይነ​ግ​ሩ​ሃል፤ አሁ​ንም እን​ግ​ዲህ በመ​ል​ካም ቀን መጥ​ተ​ና​ልና ብላ​ቴ​ኖች በፊ​ትህ ሞገስ ያግኙ፤ በእ​ጅ​ህም ከተ​ገ​ኘው ለል​ጅህ ለዳ​ዊት እባ​ክህ፥ ላክ።”
9የዳ​ዊ​ትም ብላ​ቴ​ኖች መጡ፤ ይህ​ንም የላ​ካ​ቸ​ውን ቃል ሁሉ በዳ​ዊት ስም ለና​ባል ነገ​ሩት፤ 10ናባ​ልም ተነ​ሥቶ ለዳ​ዊት ብላ​ቴ​ኖች መለ​ሰ​ላ​ቸው እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ዳዊት ማን ነው? የእ​ሴ​ይስ ልጅ ማን ነው? እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ከጌ​ቶ​ቻ​ቸው የኰ​በ​ለሉ አገ​ል​ጋ​ዮች ዛሬ ብዙ ናቸው። 11እን​ጀ​ራ​ዬ​ንና የወ​ይን ጠጄን፥ ለሸ​ላ​ቾ​ቼም ያረ​ድ​ሁ​ትን ሥጋ ወስጄ ከወ​ዴት እንደ ሆኑ ለማ​ላ​ው​ቃ​ቸው ሰዎች እሰ​ጣ​ለ​ሁን?” 12የዳ​ዊ​ትም ብላ​ቴ​ኖች ዞረው በመ​ጡ​በት መን​ገድ ተመ​ለሱ፤ መጥ​ተ​ውም ይህን ነገር ሁሉ ለዳ​ዊት ነገ​ሩት። 13ዳዊ​ትም ሰዎ​ቹን፥ “ሁላ​ችሁ ሰይ​ፋ​ች​ሁን ታጠቁ” አላ​ቸው። ሁሉም ሰይ​ፋ​ቸ​ውን ታጠቁ፤ ዳዊ​ትም ሰይ​ፉን ታጠቀ፤ አራት መቶ ሰዎ​ችም ዳዊ​ትን ተከ​ት​ለው ወጡ፤ ሁለት መቶ​ውም በጓ​ዛ​ቸው ዘንድ ተቀ​መጡ።
14ከብ​ላ​ቴ​ኖ​ቹም አንዱ ለና​ባል ሚስት ለአ​ቤ​ግያ እን​ዲህ ብሎ ነገ​ራት፥ “እነሆ፥ ዳዊት በም​ድረ በዳ ሳለ ጌታ​ች​ንን ሰላም ሊሉት መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ እርሱ ግን ፊቱን አዞ​ረ​ባ​ቸው። 15እነ​ዚህ ሰዎች ግን በእኛ ዘንድ እጅግ ደጎች ነበሩ፤ የከ​ለ​ከ​ሉ​ንም የለም፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር በኖ​ር​ን​በት ዘመን ሁሉ በም​ድረ በዳ ሳለን ከመ​ን​ጋው እን​ሰ​ጣ​ቸው ዘንድ ያዘ​ዙን አን​ዳች ነገር የለም። 16ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ሆነን መን​ጋ​ውን በጠ​በ​ቅ​ን​በት ዘመን ሁሉ በም​ድረ በዳ ሌሊ​ትና ቀን አጥር ሆነ​ውን ነበር። 17ስለ​ዚ​ህም በጌ​ታ​ች​ንና በቤቱ ሁላ ክፉ ነገር እን​ዲ​መጣ ተቈ​ር​ጦ​አ​ልና፥ እርሱ ክፉ ሰው ስለ ሆነ ማንም ሊና​ገ​ረው አይ​ች​ል​ምና የም​ታ​ደ​ር​ጊ​ውን ተመ​ል​ከ​ቺና ዕወቂ።”
18አቤ​ግ​ያም ፈጥና፦ ሁለት መቶ እን​ጀራ፥ ሁለት አቁ​ማዳ የወ​ይን ጠጅ፥ አም​ስት የተ​ዘ​ጋጁ በጎች፥ አም​ስ​ትም መስ​ፈ​ሪያ በሶ፥ አንድ ጎሞር ዘቢብ፥ ሁለት መቶም የበ​ለስ ጥፍ​ጥፍ ወሰ​ደች፥ በአ​ህ​ዮ​ችም ላይ አስ​ጫ​ነች። 19ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ዋም፥ “አስ​ቀ​ድ​ማ​ችሁ በፊቴ ሂዱ፤ እነ​ሆም እከ​ተ​ላ​ች​ኋ​ለሁ” አለች። ይህ​ንም ለባ​ልዋ ለና​ባል አል​ነ​ገ​ረ​ች​ውም። 20እር​ስ​ዋም በአ​ህ​ያዋ ላይ ተቀ​ምጣ በተ​ራ​ራው ላይ በተ​ሰ​ወረ ስፍራ በወ​ረ​ደች ጊዜ፥ እነሆ፥ ዳዊ​ትና ሰዎቹ ወደ እር​ስዋ ወር​ደው ተቀ​በ​ሏት፤ እር​ስ​ዋም ተገ​ና​ኘ​ቻ​ቸው። 21ዳዊ​ትም አለ፥ “ለዚህ ሰው ከሆ​ነው ሁሉ አንድ ነገር እን​ዳ​ይ​ጠ​ፋ​በት በእ​ው​ነት ከብ​ቱን ሁሉ በም​ድረ በዳ በከ​ንቱ ጠበ​ቅሁ፤ ከገ​ን​ዘቡ ሁሉ አን​ዳች ይወ​ስ​ዱ​በት ዘንድ ያዘ​ዝ​ነው የለም፤ እር​ሱም በበጎ ፋንታ ክፉ መለ​ሰ​ልኝ። 22ለና​ባ​ልም ከሆ​ነው ሁሉ እስከ ነገ ጥዋት ድረስ አጥር ተጠ​ግቶ የሚ​ሸን አንድ ስንኳ ብን​ተው፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዳ​ዊት ላይ እን​ዲህ ያድ​ርግ፤ እን​ዲ​ህም ይጨ​ምር” ብሎ ነበር።
23አቤ​ግ​ያም ዳዊ​ትን ባየች ጊዜ ከአ​ህ​ያዋ ላይ ፈጥና ወረ​ደች፤ በዳ​ዊ​ትም ፊት በግ​ን​ባ​ርዋ ወደ​ቀች፤ ምድ​ርም ነክታ ሰገ​ደ​ች​ለት። 24በእ​ግ​ሩም ላይ ወደ​ቀች፤ እን​ዲ​ህም አለች፥ “ጌታዬ ሆይ! ይህ ኀጢ​ኣት በእኔ ላይ ይሁን፤ እኔ ባሪ​ያህ በጆ​ሮህ ልና​ገር፥ የባ​ሪ​ያ​ህ​ንም ቃል አድ​ምጥ። 25በዚህ ክፉ ሰው በና​ባል ላይ ጌታዬ ልቡን እን​ዳ​ይ​ጥል እለ​ም​ና​ለሁ፤ እንደ ስሙ እን​ዲሁ እርሱ ነው፤ ስሙ ናባል ነው፤ ስን​ፍ​ናም አድ​ሮ​በ​ታል፤ እኔ ባሪ​ያህ ግን አንተ የላ​ክ​ሃ​ቸ​ውን ብላ​ቴ​ኖ​ች​ህን አላ​የ​ሁም። 26አሁ​ንም ጌታዬ ሆይ! ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! በሕ​ያው ነፍ​ስህ እም​ላ​ለሁ! ወደ ንጹሕ ደም እን​ዳ​ት​ገ​ባና፥ እጅ​ህን እን​ድ​ታ​ድን የከ​ለ​ከ​ለህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ አሁ​ንም ጠላ​ቶ​ች​ህና በጌ​ታዬ ላይ ክፉ የሚሹ ሁሉ እንደ ናባል ይሁኑ። 27አሁ​ንም ባሪ​ያህ ወደ ጌታዬ ያመ​ጣ​ች​ውን ይህን መተ​ያያ ተቀ​በል፤ በጌ​ታ​ዬም ዘንድ ለሚ​ቆሙ ሰዎች ስጣ​ቸው። 28እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለጌ​ታዬ የታ​መነ ቤትን ይሠ​ራ​ለ​ታ​ልና፥ የጌ​ታ​ዬ​ንም ጦር​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይዋ​ጋ​ለ​ታ​ልና የእ​ኔን የባ​ሪ​ያ​ህን ኀጢ​ኣት፥ እባ​ክህ፥ ይቅር በል፤ በዘ​መ​ን​ህም ሁሉ ክፋት አይ​ገ​ኝ​ብ​ህም። 29የሚ​ያ​ሳ​ድ​ድ​ህና ነፍ​ስ​ህን የሚሻ ሰው ቢነሣ፥ የጌ​ታዬ ነፍስ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በሕ​ይ​ወት ማሰ​ሪያ የታ​ሰ​ረች ትሆ​ና​ለች፤ የጠ​ላ​ቶ​ችህ ነፍስ ግን በወ​ን​ጭፍ እን​ደ​ሚ​ወ​ነ​ጨፍ ትሁን። 30እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለጌ​ታዬ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቸር​ነት ሁሉ ያደ​ር​ግ​ል​ሃል፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ አለቃ አድ​ርጎ ይሾ​ም​ሃል፤ 31ይህ ርኵ​ሰ​ትና የልብ በደል፥ በከ​ንቱ ንጹሕ ደም ማፍ​ሰ​ስም ለጌ​ታዬ አይ​ሁ​ኑ​በት፤ የጌ​ታ​ዬም እጁ ትዳን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለጌ​ታዬ በጎ ያድ​ር​ግ​ለት፤ በጎም ታደ​ር​ግ​ላት ዘንድ ባሪ​ያ​ህን አስብ።”
32ዳዊ​ትም አቤ​ግ​ያን አላት፥ “ዛሬ እኔን ለመ​ገ​ና​ኘት አን​ቺን የላከ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን። 33ጠባ​ይሽ የተ​ባ​ረከ ነው። ወደ ደም እን​ዳ​ል​ገባ፥ እጄ​ንም እን​ዳ​ድን ዛሬ የከ​ለ​ከ​ል​ሽኝ አን​ቺም የተ​ባ​ረ​ክሽ ነሽ። 34ነገር ግን ክፉ እን​ዳ​ላ​ደ​ር​ግ​ብሽ የከ​ለ​ከ​ለኝ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! እኔን ለመ​ገ​ና​ኘት ፈጥ​ነሽ ባል​መ​ጣሽ ኖሮ፥ እስ​ኪ​ነጋ ድረስ ለና​ባል አጥር ተጠ​ግቶ የሚ​ሸን አንድ ስንኳ ባል​ቀ​ረ​ውም ብዬ ነበር።” 35ዳዊ​ትም ያመ​ጣ​ች​ውን ከእ​ጅዋ ተቀ​ብሎ፥ “በሰ​ላም ወደ ቤትሽ ሂጂ፤ እነሆ፥ ቃል​ሽን እንደ ሰማሁ፥ ፊት​ሽ​ንም እን​ዳ​ከ​በ​ርሁ ተመ​ል​ከቺ” አላት።
36አቤ​ግ​ያም ወደ ናባል መጣች፤ እነ​ሆም፥ በቤቱ እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ ያደ​ርግ ነበር፤ ናባ​ልም እጅግ ሰክሮ ነበ​ርና ልቡ ደስ ብሎት ነበር፤ ስለ​ዚ​ህም እስ​ኪ​ነጋ ድረስ ታናሽ ነገር ወይም ታላቅ ነገር አል​ነ​ገ​ረ​ች​ውም ነበር። 37በነ​ጋ​ውም የወ​ይኑ ስካር ከና​ባል ባለፈ ጊዜ ሚስቱ ይህን ነገር ነገ​ረ​ችው፤ ልቡም በው​ስጡ ሞተ፤ እንደ ድን​ጋ​ይም ሆነ፤ 38ከዐ​ሥር ቀንም በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ናባ​ልን ቀሠ​ፈው፤ እር​ሱም ሞተ።
39ዳዊ​ትም ናባል እንደ ሞተ በሰማ ጊዜ፥ “ከና​ባል እጅ የስ​ድ​ቤን ፍርድ የፈ​ረ​ደ​ልኝ፥ ባሪ​ያ​ው​ንም ከክ​ፉ​ዎች እጅ የጠ​በቀ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የና​ባ​ልን ክፋት በራሱ ላይ መለሰ” አለ። ዳዊ​ትም ያገ​ባት ዘንድ አቤ​ግ​ያን እን​ዲ​ያ​ነ​ጋ​ግ​ሩ​ለት ላከ። 40የዳ​ዊ​ትም ብላ​ቴ​ኖች ወደ ቀር​ሜ​ሎስ ወደ አቤ​ግያ መጡ፥ “ዳዊ​ትም ሚስት ትሆ​ኚው ዘንድ ወደ አንቺ ልኮ​ናል” ብለው ነገ​ሩ​አት። 41ተነ​ሥ​ታም በግ​ን​ባ​ርዋ በም​ድር ወድቃ ሰገ​ደ​ችና፥ “እነሆ፥ እኔ ገረ​ድህ የጌ​ታ​ዬን ሎሌ​ዎች እግር አጥብ ዘንድ አገ​ል​ጋይ ነኝ” አለች። 42አቤ​ግ​ያም ፈጥና ተነ​ሣች፤ በአ​ህ​ያም ላይ ተቀ​መ​ጠች፤ አም​ስ​ቱም ገረ​ዶ​ችዋ ተከ​ተ​ሉ​አት፤ የዳ​ዊ​ት​ንም መል​እ​ክ​ተ​ኞች ተከ​ትላ ሄደች፤ ሚስ​ትም ሆነ​ችው።
43ዳዊ​ትም ደግሞ ከኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል አኪ​ና​ሆ​ምን ወሰደ፤ ሁለ​ቱም ሚስ​ቶቹ ሆኑ​ለት። 44ሳኦል ግን የዳ​ዊ​ትን ሚስት ልጁን ሜል​ኮ​ልን ሀገሩ ሮማ#ዕብ. “ጋሊም” ይላል። ለነ​በ​ረው ለያ​ሚስ ልጅ ለፈ​ልጢ ሰጣት።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ