የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ቀዳ​ማዊ 27

27
ዳዊት በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም መካ​ከል
1ዳዊ​ትም በልቡ፥ “አንድ ቀን በሳ​ኦል እጅ እሞ​ታ​ለሁ፤ ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ምድር ከመ​ሸሸ በቀር የሚ​ሻ​ለኝ የለም፤ ሳኦ​ልም በእ​ስ​ራ​ኤል አው​ራጃ ሁሉ እኔን መሻት ይተ​ዋል፤ እን​ዲ​ሁም ከእጁ እድ​ና​ለሁ” አለ። 2ዳዊ​ትም ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት ስድ​ስቱ መቶ ሰዎች ተነ​ሥ​ተው ወደ ጌት ንጉሥ ወደ አሜህ ልጅ ወደ አን​ኩስ አለፉ። 3ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ከነ​ቤ​ተ​ሰቡ ከአ​ን​ኩስ ጋር በጌት ተቀ​መጡ፤ ከዳ​ዊ​ትም ጋር ኢይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊቱ አኪ​ና​ሆ​ምና የቀ​ር​ሜ​ሎ​ሳ​ዊው የና​ባል ሚስት አቤ​ግያ ሁለቱ ሚስ​ቶቹ ነበሩ። 4ለሳ​ኦ​ልም ዳዊት ወደ ጌት እንደ ኰበ​ለለ ነገ​ሩት፤ ከዚ​ያም በኋላ ደግሞ አል​ፈ​ለ​ገ​ውም።
5ዳዊ​ትም አን​ኩ​ስን፥ “አገ​ል​ጋ​ይህ በዐ​ይ​ንህ ፊት ሞገስ አግ​ኝቼ እንደ ሆነ በዚህ ሀገር ከከ​ተ​ሞ​ችህ በአ​ን​ዲቱ የም​ቀ​መ​ጥ​በት ስፍራ ስጠኝ፤ ስለ ምን እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ ከአ​ንተ ጋር በን​ጉሥ ከተማ እቀ​መ​ጣ​ለሁ?” አለው።። 6በዚ​ያም ቀን አን​ኩስ ሴቄ​ላ​ቅን ሰጠው፤ ስለ​ዚ​ህም ሴቄ​ላቅ እስከ ዛሬ ድረስ ለይ​ሁዳ ንጉሥ ሆነች። 7ዳዊ​ትም በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሀገር የተ​ቀ​መ​ጠ​በት የዘ​መን ቍጥር አራት ወር#ዕብ. “አንድ ዓመት ከአ​ራት ወራት” ይላል። ነበረ።
8ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም ወጥ​ተው በጌ​ሴ​ራ​ው​ያ​ንና#ዕብ. “ጌር​ዛ​ው​ያንን” ይጨ​ም​ራል። በአ​ማ​ሌ​ቃ​ው​ያን ላይ አደጋ ጣሉ፤ እነ​ዚ​ህ​ንም ቅጽር ባላ​ቸው በጌ​ላ​ም​ሱ​ርና በአ​ኔ​ቆ​ን​ጦን እስከ ግብፅ ምድር ድረስ ተቀ​ም​ጠው አገ​ኙ​አ​ቸው። 9ዳዊ​ትም ሀገ​ሪ​ቱን መታ፤ ወን​ድም ሆነ፥ ሴትም ሆነ፥ ማን​ንም በሕ​ይ​ወት አል​ተ​ወም፤ በጎ​ች​ንና ላሞ​ችን፥ አህ​ያ​ዎ​ች​ንና ግመ​ሎ​ችን፥ ልብ​ስ​ንም ማረከ፤ ተመ​ል​ሶም ወደ አን​ኩስ መጣ። 10አን​ኩ​ስም ዳዊ​ትን፥ “ዛሬ በማን ላይ ዘመ​ታ​ችሁ?” አለው፤ ዳዊ​ትም፥ “በይ​ሁዳ ደቡብ፥ በያ​ሴ​ሜጋ ደቡብ፥ በቄ​ኔ​ዛ​ው​ያን ደቡብ ላይ ዘመ​ትን” አለው። 11ዳዊት እን​ዲህ አደ​ረገ፤ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሀገር በሚ​ቀ​መ​ጥ​በት ዘመን ሁሉ ልማዱ ይህ ነበረ ብለው እን​ዳ​ይ​ና​ገ​ሩ​ብን ብሎ ዳዊት ወደ ጌት ያመ​ጣ​ቸው ዘንድ ወን​ድም ሆነ ሴትም ሆነ ማን​ንም በሕ​ይ​ወት አል​ተ​ወም። 12አን​ኩ​ስም፥ “በሕ​ዝቡ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ እጅግ የተ​ጠላ ሆኖ​አል፤ ስለ​ዚ​ህም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ባሪያ ይሆ​ነ​ኛል” ብሎ ዳዊ​ትን አመ​ነው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ