የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ቀዳ​ማዊ 30

30
ዳዊት አማ​ሌ​ቃ​ው​ያ​ንን ድል እንደ አደ​ረገ
1እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ዳዊ​ትና ሰዎቹ በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ወደ ሴቄ​ላቅ በገቡ ጊዜ፥ አማ​ሌ​ቃ​ው​ያን በአ​ዜብ በሰ​ቄ​ላ​ቅም ላይ ዘም​ተው ነበር፤ ሴቄ​ላ​ቅ​ንም መት​ተው በእ​ሳት አቃ​ጥ​ለ​ዋት ነበር፥ 2ሴቶ​ቹ​ንና በው​ስ​ጥ​ዋም የነ​በ​ሩ​ትን ሁሉ ከታ​ናሽ እስከ ታላቅ ድረስ ማር​ከው ነበር፤ ሁሉ​ንም ወስ​ደው መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን ሄዱ እንጂ ሴቶ​ች​ንም ሆነ ወን​ዶ​ችን አል​ገ​ደ​ሉም። 3ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም ወደ ከተማ በመጡ ጊዜ፥ እነሆ፥ በእ​ሳት ተቃ​ጥላ፥ ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውም ተማ​ር​ከው አገኙ። 4ዳዊ​ትና ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በሩ ሕዝብ ድም​ፃ​ቸ​ውን ከፍ አድ​ር​ገው ለማ​ል​ቀስ ኀይል እስ​ኪ​ያጡ ድረስ አለ​ቀሱ። 5የዳ​ዊ​ትም ሁለቱ ሚስ​ቶቹ ኢይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊቱ አኪ​ና​ሆ​ምና የቀ​ር​ሜ​ሎ​ሳ​ዊው የና​ባል ሚስት የነ​በ​ረ​ችው አቤ​ግያ ተማ​ር​ከው ነበር። 6ስለ ወን​ዶ​ችና ስለ ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውም የሕ​ዝቡ ሁሉ ልብ አዝኖ ነበ​ርና ሕዝቡ ሊወ​ግ​ሩት ስለ ተና​ገሩ ዳዊት እጅግ ተጨ​ነቀ፤ ዳዊት ግን በአ​ም​ላኩ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራሱን አጽ​ናና።
7ዳዊ​ትም የአ​ቤ​ሜ​ሌ​ክን ልጅ ካህ​ኑን አብ​ያ​ታ​ርን፥ “ኤፉ​ዱን አቅ​ር​ብ​ልኝ” አለው፤ አብ​ያ​ታ​ርም ኤፉ​ዱን ለዳ​ዊት አቀ​ረ​በ​ለት።#“አብ​ያ​ታ​ርም ኤፉ​ዱን ለዳ​ዊት አቀ​ረ​በ​ለት” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። 8ዳዊ​ትም፥ “የእ​ነ​ዚ​ህን ሠራ​ዊት ፍለጋ ልከ​ተ​ልን? አገ​ኛ​ቸ​ዋ​ለ​ሁን?” ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየቀ፤ እር​ሱም፥ “ታገ​ኛ​ቸ​ዋ​ለ​ህና፥ ፈጽ​መ​ህም ምር​ኮ​ኞ​ቹን ታድ​ና​ለ​ህና ፍለ​ጋ​ቸ​ውን ተከ​ተል” ብሎ መለ​ሰ​ለት። 9ዳዊ​ትም ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት ስድ​ስት መቶ ሰዎች ሄዱ፤ እስከ ቦሦር ወንዝ ድረ​ስም መጡ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የቀ​ሩት በዚያ ተቀ​መጡ። 10ዳዊ​ትም ከእ​ር​ሱም ጋር ያሉት አራት መቶ ሰዎች አሳ​ደዱ፤ ሁለቱ መቶ ሰዎች ግን የቦ​ሦር ወን​ዝን መሻ​ገር ደክ​መ​ዋ​ልና በኋላ ቀሩ።
11በበ​ረ​ሃ​ውም ውስጥ አንድ ግብ​ፃዊ አግ​ኝ​ተው ወደ ዳዊት ይዘ​ውት መጡ፤ እን​ጀ​ራም ሰጡ​ትና በላ፤ ውኃም አጠ​ጡት። 12ከበ​ለ​ሱም ጥፍ​ጥፍ ቍራጭ ሰጡ​ትና በላ፤ ነፍ​ሱም ወደ እርሱ ተመ​ለ​ሰች፤ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እን​ጀራ አል​በ​ላም፤ ውኃም አል​ጠ​ጣም ነበ​ርና። 13ዳዊ​ትም፥ “አንተ የማን ነህ? ከወ​ዴት መጣህ?” አለው። ያም ግብ​ፃዊ ብላ​ቴና፥ “እኔ የአ​ማ​ሌ​ቃዊ ባሪያ ነኝ፤ ከሦ​ስት ቀንም በፊት ታምሜ ነበ​ርና ጌታዬ ጥሎኝ ሄደ። 14እኛም በከ​ሊ​ታ​ው​ያን አዜብ፥ በይ​ሁ​ዳም በኩል፥ በካ​ሌ​ብም አዜብ ላይ ዘመ​ትን፥ ሴቄ​ላ​ቅ​ንም በእ​ሳት አቃ​ጠ​ል​ናት” አለው። 15ዳዊ​ትም፥ “ወደ እነ​ዚያ ሠራ​ዊት ልት​መ​ራኝ ትወ​ድ​ዳ​ለ​ህን?” አለው፥ እር​ሱም፥ “እን​ዳ​ት​ገ​ድ​ለኝ፥ ለጌ​ታ​ዬም እጅ አሳ​ል​ፈህ እን​ዳ​ት​ሰ​ጠኝ በአ​ም​ላክ ማል​ልኝ፤ እኔም ወደ እነ​ዚያ ሠራ​ዊት እመ​ራ​ሃ​ለሁ” አለው።
16ወደ እዚ​ያም ባደ​ረ​ሰው ጊዜ፥ እነሆ፥ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንና ከይ​ሁዳ ምድር ከወ​ሰ​ዱት ከብዙ ምርኮ ሁሉ የተ​ነሣ በል​ተው፥ ጠጥ​ተው፥ የበ​ዓ​ልም ቀን አድ​ር​ገው፥ በም​ድር ሁሉ ላይ ተበ​ት​ነው አገ​ኛ​ቸው። 17ዳዊ​ትም ሄዶ የአ​ጥ​ቢያ ኮከብ ከሚ​ወ​ጣ​በት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ዳግ​መ​ኛም በማ​ግ​ሥቱ መታ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም በግ​መል ተቀ​ም​ጠው ከሸ​ሹት አራት መቶ ጐል​ማ​ሶች በቀር አን​ድም ያመ​ለጠ የለም። 18ዳዊ​ትም አማ​ሌ​ቃ​ው​ያን የወ​ሰ​ዱ​ትን ሁሉ አስ​ጣ​ላ​ቸው፤ ሁለ​ቱ​ንም ሚስ​ቶ​ቹን አዳነ። 19ከወ​ን​ዶ​ችና ከሴ​ቶች ልጆች፥ ከወ​ሰ​ዱት ምርኮ ሁሉ፥ ታላ​ቅም ሆነ፥ ታና​ሽም ሆነ፥ ምንም የተ​ወ​ላ​ቸው የለም፤ ዳዊ​ትም ሁሉን አስ​ጣለ። 20ዳዊ​ትም የበ​ጉ​ንና የላ​ሙን መንጋ ሁሉ ወሰደ፤ ምር​ኮ​ው​ንም በፊቱ ነዱ፤ ያንም ምርኮ “የዳ​ዊት ምርኮ” አሉት።
21ዳዊ​ትም ደክ​መው ዳዊ​ትን ይከ​ተ​ሉት ዘንድ ወዳ​ል​ቻሉ፥ በቦ​ሦር ወንዝ ወዳ​ስ​ቀ​ራ​ቸው ወደ ሁለቱ መቶ ሰዎች መጣ፤ እነ​ር​ሱም ዳዊ​ትን ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝብ ሊቀ​በሉ ወጡ፤ ዳዊ​ትም ወደ ሕዝቡ በቀ​ረበ ጊዜ ደኅ​ን​ነ​ቱን ጠየ​ቁት። 22ከዳ​ዊ​ትም ጋር ከሄዱ ሰዎች ክፉ​ዎ​ቹና ዐመ​ፀ​ኞቹ ሁሉ፥ “እነ​ዚህ ከእኛ ጋር አል​መ​ጡ​ምና እየ​ራ​ሳ​ቸው ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንና ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ይዘው ይሂዱ እንጂ ካስ​ጣ​ል​ነው ምርኮ ምንም አን​ሰ​ጣ​ቸ​ውም” አሉ። 23ዳዊ​ትም አለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አሳ​ልፎ ከሰ​ጠን በኋላ እን​ዲህ አታ​ድ​ርጉ፤ እርሱ ጠብ​ቆ​ናል፤ በእ​ኛም ላይ የመ​ጡ​ትን ሠራ​ዊት በእ​ጃ​ችን አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​ናል፤ 24ይህ​ንስ ነገር ማን ይሰ​ማ​ች​ኋል? እና​ንተ ከእ​ነ​ርሱ አት​በ​ል​ጡ​ምና ወደ ጦር​ነት በሄ​ዱት ድርሻ ልክ ጓዝ የጠ​በቁ ሰዎች ድርሻ እን​ዲሁ ነው።” 25ከዚ​ያም ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ይህ ለእ​ስ​ራ​ኤል ሥር​ዐ​ትና ሕግ ሆነ።
26ዳዊ​ትም ወደ ሴቄ​ላቅ በመጣ ጊዜ ለይ​ሁዳ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና ለወ​ዳ​ጆቹ፥ “እነሆ፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠላ​ቶች ምርኮ በረ​ከ​ትን ተቀ​በሉ” ብሎ ከም​ር​ኮው ላከ​ላ​ቸው። 27በቤ​ት​ሶር ለነ​በሩ፥ በራማ አዜ​ብም ለነ​በሩ፥ በጌ​ትም ለነ​በሩ፥ 28በቄ​ኔት ለነ​በሩ፥ በሳ​ፌቅ ለነ​በሩ፥ በቴ​ማት ለነ​በሩ፥ 29በቀ​ር​ሜ​ሎስ ለነ​በሩ፥ በይ​ረ​ሕ​ም​ኤ​ላ​ው​ያ​ንና በቄ​ኔ​ዛ​ው​ያን ከተ​ሞ​ችም ለነ​በሩ፥ 30በኢ​ያ​ሬ​ሞት በቤ​ር​ሳ​ቤህ ለነ​በሩ፥ በኖ​ባማ ለነ​በሩ፥ 31በኬ​ብ​ሮን ለነ​በሩ፥ ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም በተ​መ​ላ​ለ​ሱ​በት ስፍራ ለነ​በሩ ሰዎች ሁሉ ላከ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ