የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ቀዳ​ማዊ 5

5
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም መካ​ከል ያደ​ረ​ገ​ችው ተአ​ምር
1ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ወሰ​ዱ​አት፤ ከአ​ቤ​ኔ​ዜ​ርም ወደ አዛ​ጦን ይዘ​ዋት መጡ። 2ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ወስ​ደው ወደ ዳጎን ቤት አገ​ቡ​አት፤ በዳ​ጎ​ንም አጠ​ገብ አኖ​ሩ​አት። 3በነ​ጋ​ውም የአ​ዛ​ጦን ሰዎች ማለዱ፤ ወደ ዳጎ​ንም ቤት ገቡ፤ እነ​ሆም፥ ዳጎን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ፊት በም​ድር ላይ በግ​ን​ባሩ ወድቆ አገ​ኙት፤ ዳጎ​ን​ንም አን​ሥ​ተው በስ​ፍ​ራው አቆ​ሙት።#ግሪክ ሰባ. ሊ. የቍ. 6ን መጀ​መ​ሪያ ክፍል ከዚህ ያስ​ገ​ባል። 4በነ​ጋ​ውም ማለዱ፤ እነ​ሆም፥ ዳጎን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቃል ኪዳን ታቦት ፊት በም​ድር ላይ በግ​ን​ባሩ ወድቆ ነበር፤ የዳ​ጎ​ንም ራስ፥ ሁለቱ እጆ​ቹም ተቈ​ር​ጠው እየ​ራ​ሳ​ቸው በመ​ድ​ረኩ ላይ ወድ​ቀው ነበር፤ ሁለቱ መሀል እጆ​ቹም በወ​ለሉ ላይ ወድ​ቀው ነበር። የዳ​ጎ​ንም ደረት ብቻ​ውን ቀርቶ ነበር። 5ስለ​ዚ​ህም የዳ​ጎን ካህ​ናት፥ ወደ ዳጎን ቤት የሚ​ገ​ቡ​ትም ሁሉ በአ​ዛ​ጦን ያለ​ውን የዳ​ጎ​ንን መድ​ረክ እስከ ዛሬ ድረስ አይ​ረ​ግ​ጡም፤ ይራ​መ​ዱት ነበር እንጂ።
6የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ በአ​ዛ​ጦን ሰዎች ላይ ከበ​ደች፤ ክፉም ነገር አመ​ጣ​ች​ባ​ቸው፤ በእ​ነ​ር​ሱም ላይ በመ​ር​ከ​ቦች ውስጥ ወጣ፤ የአ​ዛ​ጦ​ን​ንና የአ​ው​ራ​ጃ​ዎ​ች​ዋ​ንም ሰዎች የው​ስጥ አካ​ላ​ቸ​ውን በዕ​ባጭ መታ፤ በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም መካ​ከል አይ​ጦች ወጡ፤ በከ​ተ​ማ​ውም ታላቅ መቅ​ሠ​ፍት ሆነ። 7የአ​ዛ​ጦ​ንም ሰዎች እን​ዲህ እንደ ሆነ ባዩ ጊዜ፥ “እጁ በእ​ኛና በአ​ም​ላ​ካ​ችን በዳ​ጎን ላይ ጠን​ክ​ራ​ለ​ችና የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ታቦት ከእኛ ዘንድ አት​ቀ​መጥ” አሉ። 8ልከ​ውም የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን አለ​ቆች ወደ እነ​ርሱ ሰበ​ሰ​ቡና፥ “በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ታቦት ምን እና​ድ​ርግ?” አሉ፤ የጌት ሰዎ​ችም፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ታቦት ወደ እኛ ትዙር” ብለው መለሱ። የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ታቦ​ትም ወደ ጌት ሄደች። 9ከሄ​ደ​ችም በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በከ​ተ​ማ​ዪቱ ላይ መጣች፤ ታላቅ ሁከ​ትም ሆነ፤ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም ሰዎች ታላ​ቁ​ንም ታና​ሹ​ንም መታ፤ የው​ስጥ አካ​ላ​ቸ​ው​ንም በእ​ባጭ መታ​ቸው፤ የጌት ሰዎ​ችም የው​ስጥ አካ​ላ​ቸ​ውን ምስል ሠሩ፥#“የጌት ሰዎ​ችም የው​ስጥ አካ​ላ​ቸ​ውን ምስል ሠሩ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. ብቻ። 10የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት ወደ አስ​ቀ​ሎና ላኩ​አት። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ወደ አስ​ቀ​ሎና በመ​ጣች ጊዜ አስ​ቀ​ሎ​ና​ው​ያን፥ “እኛ​ንና ሕዝ​ባ​ች​ንን ልታ​ስ​ገ​ድ​ሉን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ ታቦት ለምን አመ​ጣ​ች​ሁ​ብን?” ብለው ጮኹ። 11ልከ​ውም የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን አለ​ቆች ሁሉ ሰብ​ስ​በው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ ታቦት ስደ​ዱ​አት፤ እኛ​ንና ሕዝ​ባ​ች​ንን እን​ዳ​ት​ገ​ድል በስ​ፍ​ራዋ ትቀ​መጥ” አሉ። 12የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ወደ​ዚያ በገ​ባች ጊዜ በከ​ተ​ማው ሁሉ ታላቅ ሁከት ሆኖ​አ​ልና። በሕ​ይ​ወ​ትም ያሉ፥ ያል​ሞ​ቱ​ትም ሰዎች በእ​ባጭ ተመቱ፤ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ዋይታ እስከ ሰማይ ወጣ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ