ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2 8
8
የመቄዶንያ ቤተ ክርስቲያን አስተዋፅኦ
1ወንድሞች ሆይ፥ ለመቄዶንያ አብያተ ክርስቲያናት የተሰጠውን የእግዚአብሔርን ጸጋ እነግራችኋለሁ። 2በብዙ መከራ ከመፈተናቸው የተነሣ ደስታቸው በዝቶአልና፤ በድህነታቸው ጥልቅነትም የለጋስነታቸው ባለጠግነት በዝታለችና። 3እነርሱ ሲቻላቸው፥ ሳይቻላቸውም እንስጥ በማለት ቈራጦች ለመሆናቸው ምስክራቸው እኔ ነኝና። 4#ሮሜ 15፥26። ለቅዱሳን ስለሚሆነው አገልግሎት እንዲተባበሩ ይህን ቸርነት መላልሰው ማለዱን። 5እነርሱ አስቀድመው በፈቃዳቸው፥#“በፈቃዳቸው” የሚለው በግሪኩ የለም። እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ሰውነታቸውን ለእግዚአብሔርም፥ ለእኛም አሳልፈው ሰጥተዋልና እኛ እንደ አሰብነው አይደለም፤ 6#ግእዙ “ወአስተፍሥሐኒ ቲቶ” ይላል።ይህንም የቸርነት ሥራ እንደ ጀመረ ይፈጽምላችሁ ዘንድ ቲቶን ማለድነው። 7በሁሉ ነገር በእምነትና በቃል፥ በዕውቀትም፥ በትጋትም በእናንተ ዘንድ በሆነው ሁሉ እኛን በመውደዳችሁ ፍጹማን እንደ ሆናችሁ፥ እንዲሁም ደግሞ ይህቺን ስጦታ አብዙ።
8በግድ የምላችሁ አይደለም፤ ነገር ግን ከእናንተ ለዚህ ሥራ የሚተጉለት አሉና የፍቅራችሁን እውነተኛነት አሁን መርምሬ ተረዳሁ። 9የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ቸርነቱን ታውቃላችሁ፤ በእርሱ ድህነት እናንተ ባለጸጎች ትሆኑ ዘንድ እርሱ ባለጸጋ ሲሆን፥ ስለ እናንተ ራሱን ድሃ አደረገ። 10በዚህም የሚጠቅማችሁን እመክራችኋለሁ፤ ይህን ከማድረጋችሁ በፊት ፈቅዳችኋልና፤ ከአምና ጀምሮም ይህን ጀምራችኋል። 11አሁንም አድርጉ፤ ፈጽሙም፤ መፍቀድ ከመሻት ነውና፤ ማድረግም ከማግኘት ነውና። 12ፈቃድ ካለም፥ ሰው በሚቻለው መጠን ቢሰጥ ይመሰገናል፤ በማይቻለውም መጠን አይደለም። 13በዚህ ወራት ተካክላችሁ እንድትኖሩ ነው እንጂ ሌላው እንዲያርፍ እናንተን የምናስጨንቅ አይደለም። 14ኑሮአችሁ በሁሉ የተካከለ ይሆን ዘንድ፥ የእናንተ ትርፍ የእነርሱን ጕድለት ይመላልና፥ የእነርሱም ትርፍ የእናንተን ጕድለት ይመላልና። 15#ዘፀ. 16፥18። መጽሐፍ እንዳለ፥ “ብዙ ያለው አላተረፈም፤ ጥቂት ያለውም አላጐደለም።”
ስለ ቲቶና ጓደኞቹ
16 # ግእዙ “ዘወሀበነ ለነ ንጽሐቅ... በከመ ይቤ ቲቶ” ይላል። በቲቶ ልብ ስለ እናንተ ያን መትጋት የሰጠ እግዚአብሔር የተመሰገነ ነው። 17ልመናችንንም#ግእዙ “ሥላጤክሙ” ይላል። ተቀብሎ፥ ጨክኖ ወደ እናንተ ይመጣ ዘንድ ቸኵሏል። 18ስለ ወንጌል ትምህርት አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ያመሰገኑትን ወንድማችንንም ከእርሱ ጋር ልከናል። 19ይህም ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ክብርና የእኛን በጎ ፈቃድ ለማሳየት በምናገለግልባት በዚች ጸጋ ከእኛ ጋር አንድ ይሆን ዘንድ በአብያተ ክርስቲያናት ተሾመ። 20ስለምናገለግለው ስለዚህ ለጋስ ስጦታ ማንም እንዳይነቅፈን እንጠነቀቃለን። 21#ምሳ. 3፥4። በእግዚአብሔር ፊት ብቻ ያይደለ፥ ነገር ግን በሰው ፊትም መልካሙን ነገር እናስባለንና። 22በብዙ የፈተንነውንና በሁሉም ነገር ትጉህ ሆኖ ያገኘነውን አሁንም በእናንተ እጅግ ስለሚታመን ከፊት ይልቅ እጅግ ትጉ የሚሆነውን ወንድማችንን ከእነርሱ ጋር እንልካለን። 23ቲቶም ቢሆን፥ ስለ እናንተ አብሮኝ የሚሠራ ጓደኛዬ ነው፥ ወንድሞቻችንም ቢሆኑ፥ ለእግዚአብሔር ክብር#ግሪኩ “የክርስቶስ ክብር” ይላል። የአብያተ ክርስቲያናት ሐዋርያት ናቸው። 24አሁንም መዋደዳችሁንና እኛም በእናንተ የምንመካበትን ሥራ በአብያተ ክርስቲያናት ፊት በግልጥ አሳዩአቸው።
Currently Selected:
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2 8: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ