መጽ​ሐፈ ዕዝራ ካልእ 4

4
ስለ ንጉሥ አሸ​ና​ፊ​ነት የቀ​ረበ ሐተታ
1ንጉሥ ያሸ​ን​ፋል ያለው ሁለ​ተ​ኛ​ውም ይና​ገር ጀመረ። 2“እና​ንተ ሰዎች ሆይ፥ ሰዎች ምድ​ርን የሚ​ያ​ሸ​ን​ፏት፥ ባሕ​ር​ንም፥ በው​ስጧ ያለ​ው​ንም ሁሉ የሚ​ገዙ አይ​ደ​ለ​ምን? 3ንጉ​ሥም ለእ​ነ​ርሱ ጌታ​ቸው ነው፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ነገር ግን ንጉሡ የበ​ለጠ ኀይ​ለኛ ነው” ይላል። ፈጽ​ሞም ይገ​ዛ​ቸ​ዋል፤ እርሱ ያዘ​ዛ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ያደ​ር​ጋሉ። 4ባል​ን​ጀ​ራ​ች​ሁን ግደሉ ቢላ​ቸ​ውም ይገ​ድ​ላሉ ወደ ጦር​ነ​ትም ሂዱ ቢላ​ቸው ይሄ​ዳሉ፤ ተራ​ሮ​ች​ንም ይን​ዳሉ፤ አጥ​ሩ​ንና ግን​ቡ​ንም ያፈ​ር​ሳሉ። 5የን​ጉ​ሡ​ንም ትእ​ዛዝ እንቢ እን​ዳ​ይሉ ይገ​ድ​ላሉ፤ ይገ​ደ​ላ​ሉም፤ ድል ቢያ​ደ​ር​ጉም#ግእዙ “ወለ​እመ ሞዐ ንጉሥ” ይላል። የማ​ረ​ኩ​ትን ምርኮ ሁሉ ለን​ጉሡ ያገ​ባሉ።
6“ያል​ዘ​መ​ቱና ያል​ተ​ዋጉ፥ ምድ​ርን የሚ​ያ​ርሱ እነ​ርሱ ዘር​ተው አዝ​መ​ራ​ቸ​ውን ባገቡ ጊዜ ግብ​ሩን ለን​ጉሡ ይሰ​ጣሉ። ለን​ጉ​ሡም ግብር እን​ዲ​ከ​ፍል አንዱ ሌላ​ውን ያስ​ገ​ድ​ደ​ዋል። 7እርሱ ግን አንድ ብቻ ነው፤ ግደሉ ቢላ​ቸው ይገ​ድ​ላሉ፤ ተዉ ቢላ​ቸ​ውም ይተ​ዋሉ። 8ግረፉ ቢላ​ቸ​ውም ይገ​ር​ፋሉ፤ ገንቡ ቢላ​ቸ​ውም ይገ​ነ​ባሉ፤ አፍ​ርሱ ቢላ​ቸ​ውም ያፈ​ር​ሳሉ። 9ቍረጡ ቢላ​ቸው ይቈ​ር​ጣሉ፤ ትከሉ ቢላ​ቸ​ውም ይተ​ክ​ላሉ። 10ሕዝቡ ሁሉና ሠራ​ዊ​ቱም ላንድ ለእ​ርሱ ይታ​ዘ​ዙ​ለ​ታል፤ ከዚ​ህም ሁሉ ጋራ እርሱ ተቀ​ምጦ በል​ቶና ጠጥቶ ይተ​ኛል። 11ሌላ​ውም ዙሪ​ያ​ውን ይጠ​ብ​ቃል፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ተለ​ይቶ ሄዶ ጉዳ​ዩን ማድ​ረግ የሚ​ችል አን​ድም የለም፤ በማ​ና​ቸ​ውም ነገር እንቢ ይሉት ዘንድ አይ​ች​ሉም። 12እና​ንተ ሰዎች ሆይ፥ ሁሉ እን​ዲህ የሚ​ታ​ዘ​ዝ​ለት ንጉሥ አያ​ሸ​ን​ፍ​ምን?” ከዚ​ህም በኋላ ዝም አለ።
ስለ ሴት አሸ​ና​ፊ​ነት የቀ​ረበ ሐተታ
13ስለ ሴቶ​ችና ስለ እው​ነት የተ​ና​ገ​ረው ሦስ​ተ​ኛ​ውም ይና​ገር ጀመረ፤ እር​ሱም ዘሩ​ባ​ቤል ነው። እር​ሱም እን​ዲህ አለ፦ 14“እና​ንተ ሰዎ​ች​ሆይ፥ ንጉሡ ታላቅ አይ​ደ​ለ​ምን? ሰዎ​ቹስ ብዙ አይ​ደ​ሉ​ምን? ወይ​ንስ ብርቱ አይ​ደ​ለ​ምን? እኒ​ህ​ንስ የሚ​ገ​ዛ​ቸ​ውና የሚ​ያ​ዝ​ዛ​ቸው ማነው? ሴቶች አይ​ደ​ሉ​ምን? 15ሴቶች ምድ​ር​ንና ባሕ​ርን የሚ​ገዙ ንጉ​ሡ​ንና ሕዝ​ቡን ሁሉ ወል​ደ​ዋል። 16ከእ​ነ​ር​ሱም ተወ​ለዱ፤ እነ​ር​ሱም ከእ​ርሱ ወይን የሚ​ገ​ኝ​በት የወ​ይን ተክ​ልን የሚ​ተ​ክሉ ሰዎ​ችን አሳ​ደጉ። 17እነ​ር​ሱም ለሰ​ዎች ልብ​ስን ይሠ​ራሉ፤ ለወ​ን​ዶ​ችም ክብ​ርን ያደ​ር​ጋሉ፤ ወን​ዶ​ችም ያለ ሴት መኖር አይ​ቻ​ላ​ቸ​ውም። 18ሰዎች ምንም እንኳ ብሩ​ንና ወር​ቁን፥ መል​ካ​ሙ​ንም ዕቃ ሁሉ ቢሰ​በ​ስቡ፥ መልኳ ያማ​ረና ደም ግባ​ትዋ የተ​ወ​ደደ አን​ዲት ሴትን ባዩ ጊዜ፥ 19ያን ሁሉ ረስ​ተው እር​ሷን ይመ​ለ​ከ​ታሉ፤ አፏ​ንም ያያሉ፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “አፋ​ቸ​ውን ከፍ​ተው በት​ኩ​ረት ይመ​ለ​ከ​ት​ዋ​ታል” ይላል። ሁሉም ያደ​ን​ቋ​ታል፤ ከወ​ር​ቅና ከብር፥ ካማ​ረ​ውም ዕቃ ሁሉ እር​ሷን ይመ​ር​ጧ​ታል። 20ሰውም ያሳ​ደ​ገ​ውን አባ​ቱ​ንና ሀገ​ሩን ትቶ ሚስ​ቱን ይከ​ተ​ላል። 21ስለ ሚስ​ቱም ነፍ​ሱን ይሰ​ጣል፤ አባ​ትና እና​ቱን፥ ሀገ​ሩ​ንም አያ​ስ​ባ​ቸ​ውም። 22በዚ​ህም ሴቶች እን​ደ​ሚ​ያ​ሸ​ን​ፏ​ችሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ ጥራ​ች​ሁና ደክ​ማ​ች​ሁም ሁሉን አም​ጥ​ታ​ችሁ ለሴ​ቶች የም​ት​ሰ​ጧ​ቸው አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምን? 23ወንድ ጦሩን ይዞ ወጥቶ ይሄ​ዳል፤ ይሰ​ር​ቃል፤ ይዘ​ር​ፋ​ልም፤ በባ​ሕ​ሩና በወ​ንዙ ይጓ​ዛል፤ 24አን​በ​ሳ​ንም እያየ ይሄ​ዳል፤ በጨ​ለ​ማም ይሄ​ዳል። በሰ​ረ​ቀና በነ​ጠቀ፥ በዘ​ረ​ፈም ጊዜ ሁሉን ለሚ​ወ​ዳት ይሰ​ጣል። 25ወንድ ከወ​ለ​ዱት ከእ​ና​ቱና ከአ​ባቱ ይልቅ ሚስ​ቱን ይወ​ዳ​ታል። 26በሴ​ቶች ምክ​ን​ያት ልባ​ቸው የጠፋ፥ ስለ እነ​ር​ሱም የተ​ገ​ዙና ባሮች የሆኑ ብዙ​ዎች ናቸው። 27በሴ​ቶ​ችም ምክ​ን​ያት የሞቱ፥ የተ​ሳ​ሳ​ቱና የበ​ደሉ ብዙ​ዎች ናቸው።
28“አሁ​ንም አታ​ም​ኑ​ኝ​ምን? ንጉሥ በሥ​ል​ጣኑ ታላቅ አይ​ደ​ለ​ምን? ሕዝ​ቡስ ሁሉ ባዩት ጊዜ እር​ሱን መን​ካት የሚ​ፈሩ አይ​ደ​ለ​ምን? 29እነሆ የን​ጉሡ ዕቅ​ብት የክ​ቡር የበ​ር​ጠቁ ልጅ ኤጴ​ሜን በን​ጉሡ ቀኝ ትቀ​መ​ጣ​ለች። 30የን​ጉ​ሡን ዘውድ ከራሱ ላይ አው​ርዳ በራሷ ላይ ትደ​ፋ​ለች፤ ንጉ​ሡ​ንም በግራ እጇ በጥፊ ትመ​ታ​ዋ​ለች። 31ከዚ​ህም ሁሉ ጋራ ንጉሥ አፏን ያያል፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “አፉን ከፍቶ ያያ​ታል” ይላል። ብት​ስቅ ይስ​ቃል፤ ብት​ቈ​ጣም ትና​ገር ዘንድ፥ ቍጣ​ዋም ይበ​ርድ ዘንድ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ይቅ​ርታ ታደ​ር​ግ​ለት ዘንድ” ይላል። ያቈ​ላ​ም​ጣ​ታል። 32እና​ንተ ሰዎች፥ እን​ዲህ የሚ​ያ​ደ​ርጉ ሴቶች አያ​ሸ​ን​ፉ​ምን?”
ስለ እው​ነት አሸ​ና​ፊ​ነት የቀ​ረበ ሐተታ
33ከዚ​ህም በኋላ ንጉ​ሡና መኳ​ን​ንቱ እርስ በር​ሳ​ቸው ተያዩ፤ ከዚ​ህም በኋላ የእ​ው​ነ​ትን ነገር ይና​ገር ጀመረ። 34እን​ዲ​ህም አለ፥ “እና​ንተ ሰዎች ሆይ፥ እው​ነት የሚ​ያ​ሸ​ንፍ አይ​ደ​ለ​ምን?#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሴቶች የሚ​ያ​ሸ​ንፉ አይ​ደ​ለ​ምን” ይላል። ምድ​ርስ ታላቅ ነው፤ ሰማ​ይም ከፍ ያለ ነው፤ ፀሐ​ይም በዙ​ረቱ ፈጣን ነው፤ ባን​ዲት ቀን ሰማ​ይን ዙሮ በቀኙ ወደ ቦታው ይመ​ለ​ሳ​ልና 35እን​ዲህ የሚ​ያ​ደ​ርግ ታላቅ አይ​ደ​ለ​ምን? እው​ነ​ትም ታሸ​ን​ፋ​ለች፤ ከዚ​ህም ሁሉ ትበ​ል​ጣ​ለች። 36ዓለም ሁሉ እው​ነ​ትን ይጠ​ራ​ታል፤ ሰማ​ይም ይባ​ር​ካ​ታል፤ ፍጥ​ረ​ትም ሁሉ ለእ​ርሷ ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣል፤ ይና​ወ​ጣ​ልም፤ ከእ​ው​ነ​ትም ጋር ዐመፃ አይ​ገ​ኝም። 37ወይን በደ​ለኛ ነው፤ ንጉ​ሥም በደ​ለኛ ነው፤ ሴቶ​ችም በደ​ለ​ኞች ናቸው፤ የሰው ልጅም በደ​ለኛ ነው፤ ሥራ​ቸ​ውም ሁሉ በደል ነው፤ ይህ ሁሉ በእ​ው​ነት ዘንድ የለም፤ እነ​ዚ​ህም ሁሉ በበ​ደ​ላ​ቸው ይሞ​ታሉ።
38“እው​ነት ግን ሁል​ጊዜ ታሸ​ን​ፋ​ለች፤ ሕይ​ወ​ትም ናት፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ሙም ፈጽማ ጸንታ ትኖ​ራ​ለች። 39በእ​ርሷ ዘንድ ልዩ​ነ​ትና ለፊት ማዳ​ላት የሉም፤ ነገር ግን እው​ነት በሐ​ሰ​ትና በክፉ ሁሉ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ከሐ​ሰ​ትና ከክፉ ነገር ይልቅ ጽድ​ቅን ታደ​ር​ጋ​ለች” ይላል። አት​ኖ​ርም። ሰዎች ሁሉም ሥራ​ዋን ይወ​ድ​ዳሉ። 40በፍ​ር​ድ​ዋም ዐመፅ የለ​ባ​ትም፤ እር​ስ​ዋም ታሸ​ን​ፋ​ለች፥ መን​ግ​ሥት፥ ገና​ና​ነ​ትና በዓ​ለም ውስጥ ያለ ሥል​ጣን ሁሉ የእ​ር​ስዋ ነው፤ መን​ግ​ሥት#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የእ​ው​ነት አም​ላክ” ይላል። የእ​ርሱ የሆነ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን” ብሎ ዝም አለ።
የዘ​ሩ​ባ​ቤል ሽል​ማት
41ከዚ​ህም በኋላ ሕዝቡ ሁሉ ድም​ፃ​ቸ​ውን ከፍ በማ​ድ​ረግ፥ “እው​ነት ታላቅ ናት! ፈጽ​ማም ታሸ​ን​ፋ​ለች!” አሉ። 42ንጉ​ሡም፥ “የም​ት​ወ​ድ​ደ​ውን ከተ​ጻ​ፈው ሁሉ አብ​ል​ጠህ ለምን፤ እኔም እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ። አንተ ዐዋቂ ሆነ​ሃ​ልና፥ ተለ​ይ​ተ​ህም ከእኔ ጋር ትቀ​መ​ጣ​ለህ፤ የእ​ኔም ዘመድ ትሆ​ና​ለህ” አለው። 43እር​ሱም ንጉ​ሡን እን​ዲህ አለው፥ “በነ​ገ​ሥህ ጊዜ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ትሠ​ራት ዘንድ የተ​ሳ​ል​ኸ​ውን ስእ​ለት ዐስብ። 44ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የተ​ወ​ሰ​ዱ​ትን፥ ቂሮስ ባቢ​ሎ​ንን ለማ​ጥ​ፋት በጀ​መረ ጊዜ ለይቶ ያኖ​ራ​ቸ​ው​ንና ወደ​ዚያ ለመ​መ​ለስ የተ​ሳ​ላ​ቸ​ውን ዕቃ​ዎ​ችን ትመ​ልስ ዘንድ ዐስብ። 45አን​ተም ከለ​ዳ​ው​ያን#ግእዙ “ፋርስ” ይላል። ይሁ​ዳን ባጠ​ፏት ጊዜ ኤዶ​ማ​ው​ያን ያቀ​ጠ​ሏ​ትን ቤተ መቅ​ደስ ትሠራ ዘንድ ተስ​ለ​ሃል። 46አሁ​ንም ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ የም​ማ​ል​ድ​ህና የም​ለ​ም​ንህ ይህ ነው፤ ካን​ተም የም​ፈ​ል​ጋት ታላቅ ነገር ይህች ናት፥ ጌታዬ ለሰ​ማይ አም​ላክ የተ​ሳ​ል​ኸ​ውን ስእ​ለ​ት​ህን ታደ​ርግ ዘንድ እሺ በለኝ፥ ካን​ደ​በ​ትህ የወ​ጣ​ው​ንም አድ​ርግ።”
47ከዚህ በኋ​ላም ንጉሡ ዳር​ዮስ አቅፎ ሳመው፤ እር​ሱ​ንና ይሠ​ሯት ዘንድ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ወ​ጡ​ትን ከእ​ርሱ ጋር ያሉ​ትን ሁሉ ይሹ ዘንድ ወደ ግምጃ ቤት አዛ​ዦ​ችና ወደ አለ​ቆች፥ ወደ መሳ​ፍ​ን​ቱና ወደ መኳ​ን​ንቱ ሁሉ ደብ​ዳ​ቤ​ዎ​ችን ጻፈ​ለት። 48ከእ​ር​ሱም ጋር ከተ​ማ​ዋን ይሠሩ ዘንድ የዋ​ን​ዛ​ውን እን​ጨት ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ዲ​ያ​መጡ በቄሌ-ሶር​ያና#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ፌኒቄ” ን ይጨ​ም​ራል። በሊ​ባ​ኖስ ላሉ መሳ​ፍ​ንት ሁሉ ደብ​ዳ​ቤ​ዎ​ችን ጻፈ።
49ኀይ​ላ​ቸው የሚ​ሆኑ ባል​ን​ጀ​ሮ​ች​ንም ሁሉ ከመ​ገ​ዛ​ታ​ቸው ነጻ ያወ​ጧ​ቸው ዘንድ ከግ​ዛቱ ወደ ይሁዳ ለሚ​ወ​ጡ​ትም አይ​ሁድ ሁሉ ጻፈ። የግ​ምጃ ቤት አዛ​ዦች፥ መሳ​ፍ​ን​ቱና መኳ​ን​ን​ቱም ወደ በራ​ቸው እን​ዳ​ይ​ገቡ ጻፈ። 50ባው​ራ​ጃ​ቸው ላሉ​ትም ግብ​ሩን ይተ​ዉ​ላ​ቸው ዘንድ፥ ኤዶ​ማ​ው​ያ​ንም አጽ​ን​ተው የያ​ዙ​ትን ቦታ​ቸ​ውን ለአ​ይ​ሁድ ይተዉ ዘንድ ጻፈ። 51ሕን​ጻ​ውም እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ ለቤተ መቅ​ደሱ ሥራ የሚ​ሆን በየ​ዓ​መቱ ሃያ መክ​ሊት ወርቅ ይሰ​ጧ​ቸው ዘንድ ጻፈ። 52እንደ ልማ​ዳ​ቸ​ውም በሕጉ ሁል​ጊዜ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ለሚ​ሠ​ዉት የዘ​ወ​ትር መሥ​ዋ​ዕት ዐሥራ ሰባት፥ በየ​ዓ​መ​ቱም ሌላ ዐሥር መክ​ሊት ወርቅ ይሰ​ጧ​ቸው ዘንድ ጻፈ። 53ከተ​ማ​ዋ​ንም ለመ​ሥ​ራት ከባ​ቢ​ሎን ለሚ​መ​ጡት ሁሉ ለእ​ነ​ር​ሱና ለል​ጆ​ቻ​ቸው አገ​ዛ​ዝን ይተ​ው​ላ​ቸው ዘንድ ጻፈ። 54ለሚ​ወጡ ካህ​ና​ትም ሁሉ ምግ​ባ​ቸ​ው​ንና የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በት የአ​ገ​ል​ግ​ሎት ልብ​ሳ​ቸ​ውን ጻፈ​ላ​ቸው። 55ለሌ​ዋ​ው​ያ​ንም፦ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና የቤተ መቅ​ደስ ሥራ እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ ምግ​ባ​ቸ​ውን ይሰ​ጧ​ቸው ዘንድ ጻፈ​ላ​ቸው። 56ለሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉና ከተ​ማ​ዋን ለሚ​ሠሩ ሁሉ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ከተ​ማ​ዋን ለሚ​ጠ​ብቁ” ይላል። ምግ​ባ​ቸ​ውን ይሰ​ጧ​ቸው ዘንድ ጻፈ​ላ​ቸው። 57ቂሮስ ከባ​ቢ​ሎን ያወ​ጣ​ውን ንዋየ ቅድ​ሳ​ቱ​ንም ሁሉ፥ ሁሉ​ንም ቂሮስ እን​ዳ​ዘ​ዘ​ላ​ቸው ያደ​ርጉ ዘንድ፥ እር​ሱም እን​ዲሁ እን​ዲ​ያ​ደ​ር​ጉና ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ዲ​ልኩ አዘ​ዛ​ቸው።
የዘ​ሩ​ባ​ቤል ጸሎት
58ከዚ​ህም በኋላ ወጣቱ በወጣ ጊዜ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አን​ጻር ፊቱን ወደ ሰማይ አቀና፤ የሰ​ማ​ይ​ንም ንጉሥ አመ​ሰ​ገ​ነው። 59እን​ዲ​ህም አለ፥ “ድል መን​ሣት ከአ​ንተ ዘንድ ነው፤ ጥበ​ብም ከአ​ንተ ዘንድ ነው፤ ክብ​ርም ለአ​ንተ ነው፤ እኔም ያንተ ባሪያ ነኝ። 60ጥበ​ብን የሰ​ጠ​ኸኝ አን​ተም ቡሩክ ነህ፤ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ጌታ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።”
61ደብ​ዳ​ቤ​ዎ​ች​ንም ተቀ​ብሎ ወደ ባቢ​ሎን ሄደ፤ ይህ​ንም ለወ​ን​ድ​ሞቹ ሁሉ ነገ​ራ​ቸው። 62ያባ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም አም​ላክ አመ​ሰ​ገኑ፤ ዕረ​ፍ​ትን ሰጥ​ት​ዋ​ቸ​ዋ​ልና፥ ይቅ​ርም ብሏ​ቸ​ዋ​ልና፥ 63ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንና ስሙ የተ​ጠ​ራ​ባት ቤተ መቅ​ደ​ስ​ንም ይሠ​ሩ​አት ዘንድ፤ ለመ​ው​ጣት ፈቅ​ዶ​ላ​ቸ​ዋ​ልና። በመ​ሰ​ን​ቆና በበ​ገ​ናም ደስ እያ​ላ​ቸው ሰባት ቀን ተቀ​መጡ።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ