የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ካልእ 1

1
ዳዊት የሳ​ኦ​ል​ንና የዮ​ና​ታ​ንን ሞት እንደ ሰማ
1እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሳኦል ከሞተ በኋላ ዳዊት አማ​ሌ​ቃ​ው​ያ​ንን ከመ​ግ​ደል ተመ​ለሰ፤ ዳዊ​ትም በሴ​ቄ​ላቅ ሁለት ቀን ተቀ​መጠ። 2በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን፥ እነሆ፥ ከሰ​ፈር ከሳ​ኦል ወገን አንድ ሰው ልብ​ሱን ቀድዶ፥ በራ​ሱም ላይ ትቢያ ነስ​ንሶ መጣ፤ ወደ ዳዊ​ትም በመጣ ጊዜ በም​ድር ላይ ወድቆ ሰገ​ደ​ለት። 3ዳዊ​ትም፥ “ከወ​ዴት መጣህ?” አለው፤ እር​ሱም፥ “ከእ​ስ​ራ​ኤል ሰፈር አም​ልጬ መጣሁ” አለው። 4ዳዊ​ትም፥ “ነገሩ ምን​ድን ነው? እስኪ ንገ​ረኝ” አለው። እር​ሱም መልሶ፥ “ሕዝቡ ከሰ​ልፉ ሸሽ​ቶ​አል፤ ከሕ​ዝ​ቡም ብዙው ወደቁ፤ ሞቱም፤ ሳኦ​ልና ልጁ ዮና​ታ​ንም ደግሞ ሞተ​ዋል” አለው። 5ዳዊ​ትም ወሬ​ውን ያመ​ጣ​ለ​ትን ጐል​ማሳ፥ “ሳኦ​ልና ልጁ ዮና​ታን እንደ ሞቱ እን​ዴት ዐወ​ቅህ?” አለው። 6ወሬ​ውን ያመ​ጣ​ለት ጎል​ማ​ሳም አለ፥ “በጌ​ላ​ቡሄ ተራራ ተዋ​ግ​ተው ወደቁ፤#ዕብ. “በድ​ን​ገት ወደ ጌላ​ቡሄ ተራራ መጣሁ” ይላል። እነ​ሆም፥ ሳኦል በጦሩ ላይ ተኝቶ ነበር፤ ሰረ​ገ​ሎ​ችና ፈረ​ሰ​ኞ​ችም ተከ​ት​ለው ደረ​ሱ​በት። 7ወደ ኋላ​ውም ዘወር አለና እኔን አይቶ ጠራኝ፤ እኔም፦ እነ​ሆኝ አልሁ። 8እር​ሱም፦ አንተ ማን ነህ? አለኝ፤ እኔም አማ​ሌ​ቃዊ ነኝ ብዬ መለ​ስ​ሁ​ለት። 9እር​ሱም፦ ክፉ ጨለማ ይዞ​ኛ​ልና#ዕብ. “ጨን​ቆ​ኛ​ልና” ይላል። ደግሞ እስ​ካ​ሁን ድረስ ነፍሴ ገና ፈጽማ ሕያ​ውት ናትና በላዬ ቆመህ ግደ​ለኝ አለኝ። 10እኔም ከወ​ደቀ በኋላ አለ​መ​ዳ​ኑን አይቼ በላዩ ቆሜ ገደ​ል​ሁት፤ በራ​ሱም ላይ የነ​በ​ረ​ውን ዘውድ፥ በክ​ን​ዱም የነ​በ​ረ​ውን ቢተዋ ወሰ​ድሁ፤ ወደ​ዚ​ህም ወደ ጌታዬ አመ​ጣ​ሁት።”
11ዳዊ​ትም ልብ​ሱን ቀደደ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በሩ ሰዎች ሁሉ ልብ​ሳ​ቸ​ውን ቀደዱ። 12በጦር ወድ​ቀ​ዋ​ልና ለሳ​ኦ​ልና ለልጁ ለዮ​ና​ታን፥ ለይ​ሁ​ዳም ሕዝብ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ወገን እንባ እያ​ፈ​ሰሱ አለ​ቀሱ፤ እስከ ማታም ድረስ ጾሙ። 13ዳዊ​ትም ወሬ​ውን ያመ​ጣ​ለ​ትን ጐል​ማሳ፥ “አንተ ከወ​ዴት ነህ?” አለው፤ እር​ሱም፥ “እኔ የመ​ጻ​ተ​ኛው የአ​ማ​ሌ​ቃ​ዊው ልጅ ነኝ” ብሎ መለ​ሰ​ለት። 14ዳዊ​ትም፥ “ትገ​ድ​ለው ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀ​ባው ላይ እጅ​ህን ስት​ዘ​ረጋ እን​ዴት አል​ፈ​ራ​ህም?” አለው። 15ዳዊ​ትም ከብ​ላ​ቴ​ኖቹ አን​ዱን ጠርቶ፥ “ሂድና ግደ​ለው” አለው፤ ገደ​ለ​ውም። 16ዳዊ​ትም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቀ​ባ​ውን እኔ ገድ​ያ​ለሁ ብሎ አፍህ በላ​ይህ መስ​ክ​ሮ​አ​ልና ደምህ በራ​ስህ ላይ ይሁን” አለው።
ዳዊት ስለ ሳኦ​ልና ስለ ልጁ ዮና​ታን ሞት የተ​ቀ​ኘው ቅኔ
17ዳዊ​ትም ስለ ሳኦ​ልና ስለ ልጁ ዮና​ታን ይህን የኀ​ዘን ቅኔ ተቀኘ፤ 18የይ​ሁ​ዳ​ንም ልጆች ያስ​ተ​ምሩ ዘንድ አዘዘ። እነሆ ይህ በጻ​ድ​ቃን መጽ​ሐፍ ተጽ​ፎ​አል።
19“እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ ለሞ​ቱ​ትና ለተ​ገ​ደ​ሉት ሐው​ልት ትከል፤#ዕብ. “የእ​ስ​ራ​ኤል ክብር በኮ​ረ​ብ​ቶች ላይ ተወ​ግቶ ሞተ” ይላል።
ኀያ​ላን እን​ዴት ወደቁ!
20የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሴቶች ልጆች ደስ እን​ዳ​ይ​ላ​ቸው፥
የቈ​ላ​ፋ​ንም ሴቶች ልጆች እልል እን​ዳ​ይሉ፥
በጌት ውስጥ አታ​ውሩ፤
በአ​ስ​ቀ​ሎ​ናም አደ​ባ​ባይ የም​ስ​ራች አት​በሉ።
21እና​ንተ የጌ​ላ​ቡሄ ተራ​ሮች ሆይ፥
ዝና​ብና ጠል አይ​ው​ረ​ድ​ባ​ችሁ፤
ቍር​ባ​ን​ንም የሚ​ያ​በ​ቅል እርሻ አይ​ሁ​ን​ባ​ችሁ።
የኀ​ያ​ላን ጋሻ በዚያ ወድ​ቆ​አ​ልና፤
የሳ​ኦ​ልም ጋሻ ዘይት አል​ተ​ቀ​ባ​ምና።
22ከሞ​ቱት ደምና ከኀ​ያ​ላን ስብ፥
የዮ​ና​ታን ቀስት ባዶ​ዋን አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም፤
የሳ​ኦ​ልም ሰይፍ ባዶ​ዋን አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም።
23ሳኦ​ልና ዮና​ታን የተ​ወ​ደ​ዱና ያማሩ ነበሩ፤
በሕ​ይ​ወ​ታ​ቸ​ውና በሞ​ታ​ቸው አል​ተ​ለ​ያ​ዩም፤
ከን​ስር ይልቅ ፈጣ​ኖች ነበሩ፤
ከአ​ን​በ​ሳም ይልቅ ብር​ቱ​ዎች ነበሩ።
24የእ​ስ​ራ​ኤል ሴቶች ልጆች ሆይ፥
ቀይ ሐርና ጥሩ ግምጃ ያለ​ብ​ሳ​ችሁ ለነ​በረ፥
በወ​ር​ቀ​ዘ​ቦም ያስ​ጌ​ጣ​ችሁ ለነ​በረ ለሳ​ኦል አል​ቅ​ሱ​ለት።
25ኀያ​ላን በሰ​ልፍ ውስጥ እን​ዴት ወደቁ!
ዮና​ታን ሆይ፥ ሌሎ​ችም የተ​መ​ቱት በኮ​ረ​ብ​ቶ​ችህ ላይ ወደቁ።
26ወን​ድሜ ዮና​ታን ሆይ፥ እኔ ስለ አንተ እጨ​ነ​ቃ​ለሁ፤
አንተ በእኔ ዘንድ እጅግ የተ​ወ​ደ​ድህ ነበ​ርህ፤
ከሴት ፍቅር ይልቅ ፍቅ​ርህ ለእኔ ድንቅ ነበረ።
27ኀያ​ላን እን​ዴት ወደቁ!
የሰ​ል​ፍም ዕቃ​ዎች እን​ዴት ጠፉ!”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ