የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ካልእ 3

3
1በሳ​ኦል ቤትና በዳ​ዊት ቤት መካ​ከል ለብዙ ጊዜ ጦር​ነት ሆነ፤ የዳ​ዊት ቤት እየ​በ​ረታ፥ የሳ​ኦል ቤት ግን እየ​ደ​ከመ የሚ​ሄድ ሆነ።
2ለዳ​ዊ​ትም ወን​ዶች ልጆች በኬ​ብ​ሮን ተወ​ለ​ዱ​ለት፤ በኵ​ሩም ከኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊቱ ከአ​ኪ​ና​ሆም የተ​ወ​ለ​ደው አም​ኖን ነበረ። 3ሁለ​ተ​ኛ​ውም ከቀ​ር​ሜ​ሎ​ሳ​ዊቱ ከአ​ቤ​ግያ የተ​ወ​ለ​ደው ዶሎ​ሕያ ነበረ። ሦስ​ተ​ኛ​ውም ከጌ​ድ​ሶር ንጉሥ ከቶ​ል​ሜ​ልም ልጅ ከመ​ዓክ የተ​ወ​ለ​ደው አቤ​ሴ​ሎም ነበረ። 4አራ​ተ​ኛ​ውም የአ​ጊት ልጅ አዶ​ን​ያስ፥#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ዖር​ኒያ” ይላል። አም​ስ​ተ​ኛ​ውም የአ​ቢ​ጣል ልጅ ሰፋ​ጥያ ነበረ። 5ስድ​ስ​ተ​ኛ​ውም የዳ​ዊት ሚስት የዒ​ገል ልጅ ይት​ረ​ኃም ነበረ። ለዳ​ዊት በኬ​ብ​ሮን የተ​ወ​ለ​ዱ​ለት እነ​ዚህ ነበሩ።
አበ​ኔር ወደ ዳዊት እንደ ገባ
6በሳ​ኦል ቤትና በዳ​ዊት ቤት መካ​ከል ጦር​ነት ሆኖ ሳለ አበ​ኔር የሳ​ኦ​ልን ቤት ያበ​ረታ ነበር። 7ለሳ​ኦ​ልም የኢ​ዮ​ሄል ልጅ ሩጻፋ የተ​ባ​ለች ዕቅ​ብት ነበ​ረ​ችው፤ ኢያ​ቡ​ስ​ቴም አበ​ኔ​ርን፥ “ወደ አባቴ ዕቅ​ብት ለምን ገባህ?” አለው። 8አበ​ኔ​ርም ኢያ​ቡ​ስቴ እን​ዲህ ስላ​ለው እጅግ ተቈጣ፤ አበ​ኔ​ርም እን​ዲህ አለው፥ “በውኑ እኔ የውሻ ራስ ነኝን? እኔ ለአ​ባ​ትህ ለሳ​ኦል ቤት ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም፥ ለዘ​መ​ዶ​ቹም ቸር​ነት አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ፤ አን​ተ​ንም ለዳ​ዊት እጅ አሳ​ልፌ አል​ሰ​ጠ​ሁ​ህም፤ አን​ተም ዛሬ ከዚ​ህች ሴት ጋር ስለ ሠራ​ሁት ኀጢ​አት ትከ​ስ​ሰ​ኛ​ለህ። 9እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዳ​ዊት እንደ ማለ​ለት እን​ዲሁ ከእ​ርሱ ጋር ዛሬ ባላ​ደ​ርግ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​በ​ኔር ይህን ያድ​ር​ግ​በት፤ ይህ​ንም ይጨ​ም​ር​በት። 10የዳ​ዊ​ት​ንም ዙፋን በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በይ​ሁዳ ከዳን ጀምሮ እስከ ቤር​ሳ​ቤህ ድረስ ከፍ ያደ​ርግ ዘንድ መን​ግ​ሥ​ትን ከሳ​ኦል ቤት ወሰ​ዳት።” 11ኢያ​ቡ​ስ​ቴም አበ​ኔ​ርን ይፈ​ራው ነበ​ርና ቃልን ይመ​ል​ስ​ለት ዘንድ አል​ቻ​ለም።
12አበ​ኔ​ርም ለዳ​ዊት፥ “ከእኔ ጋር ቃል ኪዳን አድ​ርግ፤ እጄም ከአ​ንተ ጋር ትሆ​ና​ለች፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሁሉ ወደ አንተ እመ​ል​ሰ​ዋ​ለሁ” ብለው በስሙ ይነ​ግ​ሩት ዘንድ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ወዲ​ያ​ውኑ ላከ​ለት። 13ዳዊ​ትም፥ “ይሁን፤ በመ​ል​ካም ፈቃ​ደ​ኛ​ነት ከአ​ንተ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ነገር ግን አንድ ነገር ከአ​ንተ እሻ​ለሁ፤ ፊቴን ለማ​የት በመ​ጣህ ጊዜ፥ የሳ​ኦ​ልን ልጅ ሜል​ኮ​ልን ካላ​መ​ጣ​ህ​ልኝ ፊቴን አታ​ይም” አለው። 14ዳዊ​ትም ወደ ሳኦል ልጅ ወደ ኢያ​ቡ​ስቴ፥ “በመቶ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሸለ​ፈት ያጨ​ኋ​ትን ሚስ​ቴን ሜል​ኮ​ልን መል​ስ​ልኝ” ብሎ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ። 15ኢያ​ቡ​ስ​ቴም ልኮ ከሴ​ሊስ ልጅ ከባ​ልዋ ከፈ​ላ​ጥ​ያል ወሰ​ዳት። 16ባል​ዋም እያ​ለ​ቀሰ ከእ​ር​ስዋ ጋር ሄደ፤ እስከ ብራ​ቂም ድረስ ተከ​ተ​ላት። አበ​ኔ​ርም፥ “ሂድ፤ ተመ​ለስ” አለው፤ እር​ሱም ተመ​ለሰ።
17አበ​ኔ​ርም ለእ​ስ​ራ​ኤል ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፥ “አስ​ቀ​ድሞ ዳዊት በእ​ና​ንተ ላይ ንጉሥ ይሆን ዘንድ ፈል​ጋ​ችሁ ነበር። 18እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ ዳዊት፦ በባ​ሪ​ያዬ በዳ​ዊት እጅ ሕዝ​ቤን እስ​ራ​ኤ​ልን ክፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅና ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ሁሉ እጅ አድ​ና​ለሁ ብሎ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና እን​ግ​ዲህ አሁን አድ​ርጉ´ ብሎ ነገ​ራ​ቸው። 19አበ​ኔ​ርም ደግሞ በብ​ን​ያም ልጆች ጆሮ ተና​ገረ፤ አበ​ኔ​ርም ደግሞ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በብ​ን​ያም ቤት ሁሉ መል​ካም የነ​በ​ረ​ውን ለዳ​ዊት ሊነ​ግ​ረው ወደ ኬብ​ሮን ሄደ። 20አበ​ኔ​ርም ከሃያ ሰዎች ጋር ወደ ዳዊት ወደ ኬብ​ሮን መጣ፤ ዳዊ​ትም ለአ​በ​ኔ​ርና ከእ​ርሱ ጋር ለነ​በ​ሩት ሰዎች ግብዣ አደ​ረ​ገ​ላ​ቸው። 21አበ​ኔ​ርም ዳዊ​ትን፥ “ተነ​ሥቼ ልሂድ፤ ካንተ ጋርም ቃል ኪዳን እን​ዲ​ያ​ደ​ርጉ፥ ነፍ​ስ​ህም እንደ ወደ​ደች ሁሉን እን​ድ​ት​ገዛ እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ ለጌ​ታዬ ለን​ጉሥ ልሰ​ብ​ስብ” አለው። ዳዊ​ትም አበ​ኔ​ርን አሰ​ና​በ​ተው፤ በሰ​ላ​ምም ሄደ።
አበ​ኔር እንደ ተገ​ደለ
22በዚያ ጊዜም የዳ​ዊት ብላ​ቴ​ኖ​ችና ኢዮ​አብ ከዘ​መቻ ታላቅ ምርኮ ይዘው መጡ። አበ​ኔር ግን ዳዊት አሰ​ና​ብ​ቶት በደ​ኅና ሄዶ ነበር እንጂ በኬ​ብ​ሮን አል​ነ​በ​ረም። 23ኢዮ​አ​ብና ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በረ ጭፍራ ሁሉ በመጡ ጊዜ፥ “የኔር ልጅ አበ​ኔር ወደ ንጉሥ መጣ፤ አሰ​ና​በ​ተ​ውም፤ በሰ​ላ​ምም ሄደ” ብለው ሰዎች ለኢ​ዮ​አብ ነገ​ሩት። 24ኢዮ​አ​ብም ወደ ንጉሥ ገብቶ፥ “ይህ ያደ​ረ​ግ​ኸው ነገር ምን​ድን ነው? እነሆ፥ አበ​ኔር መጥ​ቶ​ልህ ነበር፤ በደ​ኅና እን​ዲ​ሄድ ስለ​ምን አሰ​ና​በ​ት​ኸው? 25የኔር ልጅ አበ​ኔር ያታ​ል​ልህ ዘንድ፥ መው​ጫ​ህ​ንና መግ​ቢ​ያ​ህ​ንም ያውቅ ዘንድ ፥ የም​ታ​ደ​ር​ገ​ው​ንም ነገር ሁሉ ያስ​ተ​ውል ዘንድ እንደ መጣ አታ​ው​ቅ​ምን?” አለው። 26ኢዮ​አ​ብም ከዳ​ዊት በወጣ ጊዜ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ከአ​በ​ኔር በኋላ ላከ፤ ከሴ​ይ​ርም ጕድ​ጓድ መለ​ሱት። ዳዊት ግን ይህን አላ​ወ​ቀም።
27አበ​ኔ​ርም ወደ ኬብ​ሮን በተ​መ​ለሰ ጊዜ ኢዮ​አብ በበር ውስጥ በቈ​ይታ ይና​ገ​ረው ዘንድ ወደ አጠ​ገቡ ወሰ​ደው፤ በዚ​ያም ለወ​ን​ድሙ ለአ​ሣ​ሄል ደም ተበ​ቅሎ ወገ​ቡን መታው፤ ሞተም። 28ከዚ​ህም በኋላ ዳዊት ሰማ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ከኔር ልጅ ከአ​በ​ኔር ደም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እኔ ንጹሕ ነኝ፤ መን​ግ​ሥ​ቴም ንጹሕ ነው፤ 29በኢ​ዮ​አብ ራስ ላይና በአ​ባቱ ቤት ሁሉ ላይ ይም​ጣ​በት፤ በኢ​ዮ​አ​ብም ቤት ፈሳሽ ነገር ያለ​በት ወይም ለም​ጻም ወይም አን​ካሳ ወይም በሰ​ይፍ የሚ​ወ​ድቅ ወይም እን​ጀራ የሌ​ለው ሰው አይ​ታጣ።” 30ኢዮ​አ​ብና ወን​ድሙ አቢ​ሳም በሰ​ልፍ በገ​ባ​ዖን ወን​ድ​ማ​ቸ​ውን አሣ​ሄ​ልን ገድሎ ነበ​ርና አበ​ኔ​ርን ይገ​ድ​ሉት ዘንድ ይጠ​ባ​በቁ ነበር።
31ዳዊ​ትም ኢዮ​አ​ብ​ንና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝብ ሁሉ፥ “ልብ​ሳ​ች​ሁን ቅደዱ፤ ማቅም ልበሱ፤ በአ​በ​ኔ​ርም ፊት አል​ቅሱ” አላ​ቸው። ንጉ​ሡም ዳዊት ከቃ​ሬ​ዛው በኋላ ሄደ። 32አበ​ኔ​ር​ንም በኬ​ብ​ሮን ቀበ​ሩት፤ ንጉ​ሡም ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ በመ​ቃ​ብሩ አጠ​ገብ አለ​ቀሰ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ለአ​በ​ኔር አለ​ቀ​ሱ​ለት። 33ንጉ​ሡም ለአ​በ​ኔር አለ​ቀ​ሰ​ለት፤ እን​ዲ​ህም አለ፦
“አበ​ኔር ሰነፍ እን​ደ​ሚ​ሞት ይሞ​ታ​ልን?
34እጆ​ችህ አል​ታ​ሰ​ሩም፤
እግ​ሮ​ች​ህም በሰ​ን​ሰ​ለት አል​ተ​ያ​ዙም፤
ማንም እንደ ሰነፍ አል​ወ​ሰ​ደ​ህም፤
በዐ​መፃ ልጆ​ችም ፊት ወደ​ቅህ።”
ሕዝ​ቡም ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በው አለ​ቀ​ሱ​ለት። 35ሕዝ​ቡም ሁሉ ገና ሳይ​መሽ ዳዊ​ትን እን​ጀራ ይበላ ዘንድ ሊጋ​ብ​ዙት መጡ፤ ዳዊት ግን፥ “ፀሐይ ሳት​ጠ​ልቅ እን​ጀራ ወይም ሌላ ነገር ብቀ​ምስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ያድ​ር​ግ​ብኝ፥ ይህ​ንም ይጨ​ም​ር​ብኝ” ብሎ ማለ። 36ሕዝ​ቡም ሁሉ ይህን ዐወቁ፤ በሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ፊት ንጉሥ ያደ​ረ​ገው ሁሉ ደስ አሰ​ኛ​ቸው።
37በዚ​ያም ቀን ሕዝቡ ሁሉ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ የኔር ልጅ አበ​ኔ​ርን እን​ዲ​ገ​ድ​ሉት ንጉሡ እን​ዳ​ላ​ዘዘ ዐወቁ። 38ንጉ​ሡም ብላ​ቴ​ኖ​ቹን፥ “ዛሬ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ታላቅ መኰ​ንን እንደ ወደቀ አታ​ው​ቁ​ምን? 39እኔም ዛሬ ዘመዱ እንደ ሆንሁ፥ እር​ሱም በን​ጉሡ ዘንድ የተ​ሾመ እንደ ሆነ አታ​ው​ቁ​ምን? እነ​ዚ​ህም ሰዎች የሦ​ር​ህያ ልጆች በር​ት​ተ​ው​ብ​ኛል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክፋት በሠራ ላይ እንደ ክፋቱ ይመ​ል​ስ​በት” አላ​ቸው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ