የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ካልእ 6

6
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ከአ​ሚ​ና​ዳብ ቤት ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እንደ መጣች
(1ዜ.መ. 13፥1-1415፥25—16፥6፤43)
1ዳዊ​ትም ደግሞ ከእ​ስ​ራ​ኤል የተ​መ​ረ​ጡ​ትን ሰባ ሺህ#ዕብ. “ሠላሳ ሺህ” ይላል። ያህል ሰው ሰበ​ሰበ። 2ዳዊ​ትና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩት ሕዝብ ሁሉ ከይ​ሁዳ አለ​ቆች ጋር ተነ​ሥ​ተው በኪ​ሩ​ቤል ላይ የተ​ቀ​መጠ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም የተ​ጠ​ራ​ባ​ትን#ዕብ. “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም የተ​ጠ​ራ​ውን ...” ይላል። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ከዚያ ያመጡ ዘንድ ሄዱ። 3የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት በአ​ዲስ ሰረ​ገላ ላይ ጫኑ​አት፥ በኮ​ረ​ብ​ታ​ውም ላይ ከነ​በ​ረው ከአ​ሚ​ና​ዳብ ቤት አመ​ጡ​አት፤ የአ​ሚ​ና​ዳብ ልጆ​ችም ዖዛና ወን​ድ​ሞቹ ታቦቷ ያለ​ች​በ​ትን ሰረ​ገላ ይነዱ ነበር። 4ወን​ድ​ሞ​ቹም በታ​ቦቷ ፊት ይሄዱ ነበር። 5ዳዊ​ትና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ በዜማ መሣ​ሪ​ያ​ዎች በበ​ገ​ናና በመ​ሰ​ንቆ፥ በከ​በ​ሮና በነ​ጋ​ሪት፥ በጸ​ና​ጽ​ልና በዕ​ን​ዚራ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በሙሉ ኀይ​ላ​ቸው ይጫ​ወቱ ነበር።
6ወደ ናኮ​ንም አው​ድማ ደረሱ፤ ዖዛም በሬ​ዎቹ አነ​ቃ​ን​ቀ​ዋት ነበ​ርና ይይ​ዛት ዘንድ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት እጁን ዘረጋ፤ አስ​ተ​ካ​ከ​ላ​ትም። ሲይ​ዛ​ትም በሬው ወጋው።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ዖዛን በሬው ወጋው” አይ​ሉም። 7እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዖዛ ላይ ተቈጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚ​ያው ቀሠ​ፈው። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት አጠ​ገብ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በዚ​ያው ሞተ። 8እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዖዛን ስለ ገደ​ለው ዳዊት አዘነ፤ እስከ ዛሬም ድረስ የዚያ ስፍራ ስም “ዖዛ የሞ​ተ​በት” ተባለ። 9በዚ​ያም ቀን ዳዊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈራና፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ወደ እኔ እን​ዴት ትገ​ባ​ለች?” አለ። 10ዳዊ​ትም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦተ ሕግ ወደ እርሱ ወደ ዳዊት ከተማ ያመ​ጣት ዘንድ አል​ወ​ደ​ደም፤ ዳዊ​ትም በጌት ሰው በአ​ቢ​ዳራ ቤት አገ​ባት። 11የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት በጌት ሰው በአ​ቢ​ዳራ ቤት ሦስት ወር ተቀ​መ​ጠች፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አቢ​ዳ​ራ​ንና ቤቱን ሁሉ ባረከ።
12ለን​ጉሡ ዳዊ​ትም “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ቢ​ዳ​ራን ቤትና የነ​በ​ረ​ውን ሁሉ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ባረከ” ብለው ነገ​ሩት። ዳዊ​ትም ሄዶ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ከአ​ቢ​ዳራ ቤት ወደ ዳዊት ከተማ በደ​ስታ አመ​ጣት። 13ከእ​ር​ሱም ጋር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት የተ​ሸ​ከሙ ሰባት መሰ​ንቆ የሚ​መቱ ክፍ​ሎች ነበሩ። በሬ​ዎ​ች​ንና በጎ​ችን ይሠዉ ነበር። 14ዳዊ​ትም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በገና ይደ​ረ​ድር ነበር፤ ዳዊ​ትም ለዐ​ይን የሚ​ያ​ን​ጸ​ባ​ርቅ የሐር ቀሚስ ለብሶ ነበር። 15ዳዊ​ትና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ሁሉ በእ​ል​ልታ ቀንደ መለ​ከት እየ​ነፉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት አመ​ጡ​አት።
16የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ በደ​ረ​ሰች ጊዜ የሳ​ኦል ልጅ ሜል​ኮል በመ​ስ​ኮት ሆና ተመ​ለ​ከ​ተች፤ ንጉ​ሡም ዳዊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሲዘ​ል​ልና ሲዘ​ምር አየ​ችው፥ በል​ብ​ዋም ናቀ​ችው። 17የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት አም​ጥ​ተው ዳዊት በተ​ከ​ለ​ላት ድን​ኳን ውስጥ በስ​ፍ​ራዋ አኖ​ሩ​አት፤ ዳዊ​ትም የሚ​ቃ​ጠ​ልና የሰ​ላም መሥ​ዋ​ዕ​ትን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አሳ​ረገ። 18ዳዊ​ትም የሚ​ቃ​ጠ​ልና የሰ​ላም መሥ​ዋ​ዕት ማሳ​ረ​ግን ከፈ​ጸመ በኋላ ሕዝ​ቡን በሰ​ራ​ዊት ጌታ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም መረቀ። 19ለሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ለእ​ስ​ራ​ኤል ወገን ከዳን እስከ ቤር​ሳ​ቤህ ለወ​ን​ዱም፥ ለሴ​ቱም ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ አን​ዳ​ንድ እን​ጀራ፥ አን​ዳ​ን​ድም የሥጋ ቍራጭ፥ አን​ዳ​ን​ድም ጽዋዕ ወይን አከ​ፋ​ፈለ። ሕዝ​ቡም ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ ወደ ቤቱ ሄደ።
20ዳዊ​ትም ቤተ ሰቡን ሊመ​ርቅ ተመ​ለሰ። የሳ​ኦል ልጅ ሜል​ኮ​ልም ዳዊ​ትን ለመ​ቀ​በል ወጣ​ችና ሰላ​ምታ ሰጠ​ችው፥ “ከሚ​ዘ​ፍ​ኑት አንዱ እን​ደ​ሚ​ገ​ለጥ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ በአ​ገ​ል​ጋ​ዮቹ ሚስ​ቶች ፊት በመ​ገ​ለጡ ምንኛ የተ​ከ​በረ ነው!” አለች። 21ዳዊ​ትም ሜል​ኮ​ልን፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ዘም​ሬ​አ​ለሁ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አለቃ እሆን ዘንድ ከአ​ባ​ት​ሽና ከቤቱ ሁሉ ይልቅ የመ​ረ​ጠኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​መ​ሰ​ገነ ይሁን፤ ስለ​ዚ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እጫ​ወ​ታ​ለሁ፤ እዘ​ም​ራ​ለ​ሁም፤ 22አሁ​ንም እገ​ለ​ጣ​ለሁ፤ በዐ​ይ​ንሽ ፊትና እን​ዴት ከበ​ርህ ባል​ሽ​ባ​ቸው ሴቶች ልጆች ፊት የተ​ና​ቅሁ እሆ​ና​ለሁ” አላት። 23የሳ​ኦ​ልም ልጅ ሜል​ኮል እስከ ሞተ​ች​በት ቀን ድረስ ልጅ አል​ወ​ለ​ደ​ችም።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ