የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 13

13
በር​ና​ባ​ስና ሳውል ለስ​ብ​ከተ ወን​ጌል እንደ ተመ​ረጡ
1በአ​ን​ጾ​ኪያ በነ​በ​ረ​ችው ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንም ነቢ​ያ​ትና መም​ህ​ራን ነበሩ፤ እነ​ር​ሱም በር​ና​ባስ፥ ኔጌር#“ኔጌር” ጥቁር ማለት ነው። የተ​ባ​ለው ስም​ዖን፥ የቀ​ሬ​ናው ሉቅ​ዮስ፥ ከአ​ራ​ተ​ኛው ክፍል ገዢ ከሄ​ሮ​ድስ ጋር ያደ​ገው ምናሔ፥ ሳው​ልም ነበሩ። 2የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ሲሠሩ፥ ሲጾ​ሙም#አን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ “ወይ​ጼ​ልዩ” የሚል ይጨ​ም​ራል። መን​ፈስ ቅዱስ፥ “በር​ና​ባ​ስ​ንና ሳው​ልን እኔ ለፈ​ለ​ግ​ኋ​ቸው ሥራ ለዩ​ልኝ” አላ​ቸው። 3ያን​ጊ​ዜም ከጾ​ሙና ከጸ​ለዩ፥ እጃ​ቸ​ው​ንም በራ​ሳ​ቸው ላይ ከጫ​ኑ​ባ​ቸው በኋላ ላኩ​አ​ቸው።
በር​ና​ባ​ስና ሳውል በቆ​ጵ​ሮስ እንደ አስ​ተ​ማሩ
4ከመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስም ተል​ከው ወደ ሴሌ​ው​ቅያ ወረዱ፤ ከዚ​ያም በመ​ር​ከብ ወደ ቆጵ​ሮስ ሄዱ። 5ወደ ሰል​ሚና ሀገ​ርም ገብ​ተው በአ​ይ​ሁድ ምኵ​ራ​ቦች የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አስ​ተ​ማሩ፤ ዮሐ​ን​ስም እየ​አ​ገ​ለ​ገ​ላ​ቸው ከእ​ነ​ርሱ ጋር ነበር። 6በደ​ሴ​ቲ​ቱም ሁሉ ሲዘ​ዋ​ወሩ ጳፉ ወደ​ም​ት​ባል ሀገር ደረሱ፤ በዚ​ያም አንድ አይ​ሁ​ዳዊ የሆነ ሐሰ​ተኛ ነቢ​ይና አስ​ማ​ተኛ ሰው አገኙ፤ ስሙም በር​ያ​ሱስ ይባ​ላል። 7እር​ሱም ብልህ ሰው በሆነ ሰር​ግ​ዮስ ጳው​ሎስ በሚ​ባል አገረ ገዢ ዘንድ ይኖር ነበረ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ሊሰማ ወድዶ በር​ና​ባ​ስ​ንና ሳው​ልን ወደ እርሱ ጠራ​ቸው። 8አስ​ማ​ተ​ኛው ኤል​ማ​ስም የስሙ ትር​ጓሜ እን​ዲህ ነበ​ረና፥ ገዥ​ውን ከማ​መን ሊከ​ለ​ክ​ለው ፈልጎ ተቃ​ወ​ማ​ቸው። 9ጳው​ሎስ በተ​ባ​ለው በሳ​ውል ላይም ቅዱስ መን​ፈስ ሞላ​በት፤ አተ​ኵ​ሮም ተመ​ለ​ከ​ተው። 10እን​ዲ​ህም አለው፥ “ሽን​ገ​ላ​ንና ክፋ​ትን ሁሉ የተ​መ​ላህ፥ የሰ​ይ​ጣን ልጅ፥ የጽ​ድቅ ሁሉ ጠላት ሆይ፥ የቀ​ና​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገድ ማጣ​መ​ም​ህን ትተው ዘንድ እንቢ አል​ህን? 11እነሆ፥ አሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በአ​ንተ ላይ ነው፤ ዕው​ርም ትሆ​ና​ለህ፤ እስከ ጊዜ​ውም ፀሐ​ይን አታ​ይም፤” ወዲ​ያ​ው​ኑም ታወረ፤ ጨለ​ማም ዋጠው፤ የሚ​መ​ራ​ውም ፈለገ። 12አገረ ገዢ​ውም የሆ​ነ​ውን በአየ ጊዜ ተገ​ረመ፤ በጌ​ታ​ችን ትም​ህ​ር​ትም አመነ።
በር​ና​ባ​ስና ጳው​ሎስ በጲ​ስ​ድያ አን​ጾ​ኪያ እንደ አስ​ተ​ማሩ
13ከዚ​ህም በኋላ እነ ጳው​ሎስ ከጳፉ ከተማ ወጥ​ተው ሄዱና የጵ​ን​ፍ​ልያ አው​ራጃ ወደ​ም​ት​ሆን ወደ ጰር​ጌን ገቡ፤ ዮሐ​ንስ ግን ትቶ​አ​ቸው ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሰ። 14እነ​ር​ሱም ከጰ​ር​ጌን አል​ፈው የጲ​ስ​ድያ አው​ራጃ ወደ​ም​ት​ሆን ወደ አን​ጾ​ኪያ ደረሱ፤ በሰ​ን​በት ቀንም ወደ ምኵ​ራብ ገብ​ተው ተቀ​መጡ። 15ኦሪ​ት​ንና ነቢ​ያ​ትን ካነ​በቡ በኋ​ላም የም​ኵ​ራቡ አለ​ቆች፥ “እና​ንተ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ለሕ​ዝብ ሊነ​ገር የሚ​ገ​ባው የም​ክር ቃል እንደ አላ​ችሁ ተና​ገሩ” ብለው ላኩ​ባ​ቸው።
16ጳው​ሎ​ስም ተነ​ሥቶ ዝም እን​ዲሉ አዘ​ዘና እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንት የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎ​ችና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የም​ት​ፈሩ ሁሉ፥ ስሙ። 17#ዘፀ. 1፥7፤ 12፥51። የእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ አም​ላክ አባ​ቶ​ቻ​ች​ንን መረ​ጣ​ቸው፤ ወገ​ኖ​ቹ​ንም በተ​ሰ​ደ​ዱ​በት በም​ድረ ግብፅ ከፍ ከፍ አደ​ረ​ጋ​ቸው፤ ከዚ​ያም ከፍ ባለ ክንዱ አወ​ጣ​ቸው። 18#ዘኍ​. 14፥34፤ ዘዳ. 1፥31። አርባ ዘመ​ንም በም​ድረ በዳ መገ​ባ​ቸው። 19#ዘዳ. 7፥1፤ ኢያ. 14፥1። ሰባ​ቱን የከ​ነ​ዓ​ንን አሕ​ዛብ አጥ​ፍቶ ምድ​ራ​ቸ​ውን አወ​ረ​ሳ​ቸው። 20#መሳ. 2፥16፤ 1ሳሙ. 3፥20። ከዚ​ህም በኋላ አራት መቶ አምሳ ዓመት እስከ ነቢዩ እስከ ሳሙ​ኤል ዘመን ድረስ መሳ​ፍ​ን​ትን ሾመ​ላ​ቸው። 21#1ሳሙ. 8፥5፤ 10፥21። ከዚ​ያም ወዲያ ንጉሥ ያነ​ግ​ሥ​ላ​ቸው ዘንድ ለመኑ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከብ​ን​ያም ነገድ የተ​ወ​ለ​ደ​ውን ሰው የቂ​ስን ልጅ ሳኦ​ልን አርባ ዓመት አነ​ገ​ሠ​ላ​ቸው። 22#1ሳሙ. 13፥14፤ 16፥12፤ መዝ. 88፥20። እር​ሱ​ንም ሻረው፤ ከእ​ር​ሱም በኋላ ዳዊ​ትን አነ​ገ​ሠ​ላ​ቸው፤ ‘የእ​ሴ​ይን ልጅ ዳዊ​ትን ፈቃ​ዴን ሁሉ የሚ​ፈ​ጽም እንደ ልቤም የታ​መነ ሰው ሆኖ አገ​ኘ​ሁት’ ብሎ መሰ​ከ​ረ​ለት። 23እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተስፋ እንደ ሰጣ​ቸው ከዳ​ዊት ዘር ለእ​ስ​ራ​ኤል መድ​ኀ​ኒት አድ​ርጎ ኢየ​ሱ​ስን አመ​ጣ​ላ​ቸው። 24#ማር. 1፥4፤ ሉቃ. 3፥3። እርሱ ከመ​ም​ጣቱ አስ​ቀ​ድሞ ዮሐ​ንስ ለእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ ሁሉ የን​ስሓ ጥም​ቀ​ትን ሰበ​ከ​ላ​ቸው። 25#ማቴ. 3፥11፤ ማር. 1፥7፤ ሉቃ. 3፥16፤ ዮሐ. 1፥20፤27። ዮሐ​ን​ስም መል​እ​ክ​ቱን ሲፈ​ጽም እን​ዲህ አላ​ቸው፦ ‘እኔን ለምን ትጠ​ራ​ጠ​ሩ​ኛ​ላ​ችሁ? እር​ሱን አይ​ደ​ለ​ሁም፤ የጫ​ማ​ውን ማዘ​ቢያ ከእ​ግሩ ልፈታ የማ​ይ​ገ​ባኝ ከእኔ በኋላ እነሆ፥ ይመ​ጣል።’
26“እና​ንተ ከአ​ብ​ር​ሃም ወገን የተ​ወ​ለ​ዳ​ችሁ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የም​ት​ፈሩ፥ ይህ የሕ​ይ​ወት ቃል ለእ​ና​ንተ ተል​ኮ​አል። 27በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ኖ​ሩና አለ​ቆ​ቻ​ቸው ግን እር​ሱን አላ​ወ​ቁም፤ የነ​ቢ​ያት መጻ​ሕ​ፍ​ት​ንም በየ​ሰ​ን​በቱ ሁሉ ሲያ​ነቡ አላ​ስ​ተ​ዋ​ሉ​ትም፤ ነገር ግን ይሙት በቃ ፈረ​ዱ​በት፥ ስለ እርሱ የተ​ጻ​ፈ​ው​ንም ሁሉ ፈጸ​ሙ​በት። 28#ማቴ. 27፥22-23፤ ማር. 15፥13-14፤ ሉቃ. 23፥21-23፤ ዮሐ. 19፥15። ለሞ​ትም የሚ​ያ​በቃ ምንም በደል ባላ​ገ​ኙ​በት ጊዜ እን​ዲ​ገ​ድ​ለው ጲላ​ጦ​ስን ለመ​ኑት። 29#ማቴ. 27፥57-61፤ ማር. 15፥42-47፤ ሉቃ. 23፥50-55፤ ዮሐ. 19፥38-42። ስለ እር​ሱም የተ​ጻ​ፈ​ውን ሁሉ ከፈ​ጸሙ በኋላ ከመ​ስ​ቀል አው​ር​ደው በመ​ቃ​ብር ቀበ​ሩት። 30እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ከሙ​ታን ለይቶ አስ​ነ​ሣው። 31#የሐዋ. 1፥3። ከተ​ነ​ሣም በኋላ ከገ​ሊላ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም አብ​ረ​ውት ለወ​ጡት ብዙ ቀን ተገ​ለ​ጠ​ላ​ቸው። እነ​ር​ሱም በሕ​ዝብ ዘንድ ምስ​ክ​ሮች ሆኑት።
32“እኛም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ያና​ገ​ረ​ላ​ቸ​ውን#አን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ “ለል​ጆ​ቻ​ቸው የሰ​ጣ​ቸ​ውን” የሚል ይጨ​ም​ራል። ተስፋ እን​ነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለን። 33#መዝ. 2፥7። በሁ​ለ​ተ​ኛው መዝ​ሙር፦ ‘አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወለ​ድ​ሁህ’ እን​ዳለ ኢየ​ሱ​ስን አስ​ነ​ሥቶ ተስ​ፋ​ውን ለእኛ ለል​ጆ​ቻ​ቸው ፈጽ​ሞ​አል። 34#ኢሳ. 55፥3። መፍ​ረስ መበ​ስ​በ​ስ​ንም እን​ዳ​ያይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሙ​ታን ለይቶ እን​ዳ​ስ​ነ​ሣው እን​ዲህ አለ፦ ‘የታ​መ​ነ​ውን የዳ​ዊ​ትን ቅዱስ#በግ​ሪኩ ብቻ። ተስፋ እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ። 35#መዝ. 15፥10። በሌላ ስፍ​ራም እን​ዲህ ይላል፦ ‘ጻድ​ቅ​ህን መፍ​ረስ መበ​ስ​በ​ስን ያይ ዘንድ አት​ሰ​ጠ​ውም።’ 36ዳዊት ግን በዘ​መኑ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ አገ​ል​ግ​ሎ​አል፤ እንደ አባ​ቶቹ ሞተ፥ ተቀ​በ​ረም፤ መፍ​ረስ መበ​ስ​በ​ስ​ንም አይ​ቶ​አል። 37#ኢሳ. 42፥6፤ 49፥6። ይህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያስ​ነ​ሣው ግን መፍ​ረስ መበ​ስ​በ​ስን አላ​የም። 38እን​ግ​ዲህ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን፥ በእ​ርሱ ኀጢ​አ​ታ​ችሁ እን​ደ​ሚ​ሰ​ረ​ይ​ላ​ችሁ ተስፋ የሰ​ጣ​ች​ሁን ዕወቁ። 39ከሁ​ሉም ይልቅ በሙሴ ሕግ መጽ​ደቅ የተ​ሳ​ና​ችሁ ናችሁ። በእ​ርሱ ግን ያመነ ሁሉ ይጸ​ድ​ቃል። 40እን​ግ​ዲህ እን​ዲህ የሚ​ለው የነ​ቢ​ያት ቃል እን​ዳ​ይ​ደ​ር​ስ​ባ​ችሁ ተጠ​ን​ቀቁ። 41‘እነሆ፥ እና​ንተ የም​ታ​ቃ​ልሉ፥ እዩ፤ ተደ​ነ​ቁም፤ ያለ​ዚያ ግን ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ፤ ማንም ቢነ​ግ​ራ​ችሁ የማ​ታ​ም​ኑ​ትን ሥራ እኔ በዘ​መ​ና​ችሁ እሠ​ራ​ለ​ሁና።’ ”
42ከም​ኵ​ራ​ብም ከወጡ በኋላ ይህን ነገር በሁ​ለ​ተ​ኛው ሰን​በት እን​ዲ​ነ​ግ​ሩ​አ​ቸው ማለ​ዱ​አ​ቸው። 43ጉባ​ኤ​ውም በተ​ፈታ ጊዜ ከአ​ይ​ሁ​ድና ወደ ይሁ​ዲ​ነት ከተ​መ​ለ​ሱት ከደ​ጋጉ ሰዎች ብዙ​ዎች ጳው​ሎ​ስ​ንና በር​ና​ባ​ስን ተከ​ተ​ሉ​አ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ ይድኑ ዘንድ እያ​ስ​ረዱ ነገ​ሯ​ቸው።
44በሁ​ለ​ተ​ኛው ሰን​በ​ትም የከ​ተ​ማው ሰዎች ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ይሰሙ ዘንድ ተሰ​በ​ሰቡ። 45አይ​ሁ​ድም የተ​ሰ​በ​ሰ​በ​ውን ብዙ ሕዝብ ባዩ ጊዜ ቀኑ​ባ​ቸው፤ እየ​ተ​ሳ​ደ​ቡም ጳው​ሎስ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል ተቃ​ወሙ።
46ጳው​ሎ​ስና በር​ና​ባ​ስም ደፍ​ረው እን​ዲህ ብለው ተና​ገ​ሩ​አ​ቸው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ለእ​ና​ንተ አስ​ቀ​ድሞ ልን​ነ​ግ​ራ​ችሁ ይገ​ባል፤ እንቢ ብት​ሉና ራሳ​ች​ሁን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት የተ​ዘ​ጋጀ ባታ​ደ​ርጉ ግን እነሆ፥ ወደ አሕ​ዛብ እን​መ​ለ​ሳ​ለን። 47እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ እስከ ምድር ዳርቻ ላሉት ሁሉ መድ​ኀ​ኒት ትሆን ዘንድ ለአ​ሕ​ዛብ ብር​ሃን አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ” ብሎ አዝ​ዞ​ና​ልና። 48አሕ​ዛ​ብም ይህን ሰም​ተው ደስ አላ​ቸው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል አከ​በሩ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትም የተ​ዘ​ጋጁ ሁሉ አመኑ። 49የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል በሀ​ገሩ ሁሉ ተዳ​ረሰ። 50አይ​ሁድ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈሩ የከ​በሩ ሴቶ​ች​ንና የከ​ተ​ማ​ውን ሽማ​ግ​ሌ​ዎች አነ​ሳ​ሡ​አ​ቸው፤ በጳ​ው​ሎ​ስና በበ​ር​ና​ባስ ላይም ስደ​ትን አስ​ነሡ፤ ከሀ​ገ​ራ​ቸ​ውም አባ​ረ​ሩ​አ​ቸው። 51#ማቴ. 10፥14፤ ማር. 6፥11፤ ሉቃ. 9፥5፤ 10፥11። እነ​ርሱ ግን የእ​ግ​ራ​ቸ​ውን ትቢያ አራ​ግ​ፈ​ው​ባ​ቸው ወደ ኢቆ​ን​ዮን ሄዱ። 52መን​ፈስ ቅዱ​ስም በደቀ መዛ​ሙ​ርት ላይ ሞላ፤ ደስም አላ​ቸው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ