የሐዋርያት ሥራ 15
15
ስለ ቢጽ ሐሳውያን
1 #
ዘሌ. 12፥3፤ የሐዋ. 10፥1-43። ከይሁዳ ሀገርም የወረዱ ሰዎች፥ “እንደ ሙሴ ሕግ ካልተገዘራችሁ ልትድኑ አትችሉም” እያሉ ወንድሞችን ያስተምሩ ነበር። 2ሕዝቡም እጅግ ታወኩ፤ ጳውሎስንና በርናባስንም ተከራከሩአቸው፤ ስለዚህ ነገርም ጳውሎስንና በርናባስን፥ ጓደኞቻቸውንም በኢየሩሳሌም ወደ አሉት ወደ ሐዋርያትና ቀሳውስት ሊልኳቸው ተማከሩ። 3ከቤተ ክርስቲያንም በተላኩ ጊዜ ወደ ሰማርያና ወደ ፊንቄ ደርሰው አሕዛብ ወደ ሃይማኖት እንደ ተመለሱ ነገሩቸአቸው፤ ወንድሞችንም ሁሉ እጅግ ደስ አሰኙአቸው። 4ወደ ኢየሩሳሌም በደረሱ ጊዜም ምእመናንና ሐዋርያት፥ ቀሳውስትም ተቀበሉአቸው፤ እግዚአብሔርም በአሕዛብ መካከል ያደረገላቸውን ነገሩአቸው። 5ነገር ግን ካመኑት ከፈሪሳውያን ወገን አንዳንዶች ተነሥተው፥ “ትገዝሩአቸው ዘንድና የሙሴን ሕግ እንዲጠብቁ ታዝዙአቸው ዘንድ ይገባል” አሉ።
የመጀመሪያዪቱ የሐዋርያት ጉባኤ
6ሐዋርያትና ቀሳውስትም ስለዚህ ነገር የሚያደርጉትን ያዩ ዘንድ ተሰበሰቡ። 7ብዙ ክርክርም ከተከራከሩ በኋላ ጴጥሮስ ተነሥቶ እንዲህ አላቸው፥ “ወንድሞች ሆይ፥ ስሙ፤ ለአሕዛብ ከአፌ የወንጌሉን ቃል እንዳሰማቸውና እንዲያምኑ እግዚአብሔር አስቀድሞ እንደ መረጠኝ እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ። 8#2፥5፤ 10፥44። ልብን የሚያውቅ እግዚአብሔርም ለእኛ እንደ ሰጠን መንፈስ ቅዱስን በመስጠት መሰከረላቸው። 9ልባቸውንም በእምነት አንጽቶ ከእኛ አልለያቸውም። 10አሁንም እግዚአብሔርን አትፈታተኑት፤ እኛም አባቶቻችንም ልንሸከመው ያልቻልነውን ቀንበር በደቀ መዛሙርት ጫንቃ ላይ ለምን ትጭናላችሁ? 11ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እንድን ዘንድ እንታመናለን፤ እነርሱም እንደ እኛ ይድናሉ።”
12ያንጊዜም ሕዝቡ ሁሉ ጸጥ ብለው እግዚአብሔር በአሕዛብ ዘንድ ያደረገላቸውን ተአምራትና ድንቅ ሥራ ሁሉ ሲናገሩ ጳውሎስንና በርናባስን አዳመጡአቸው።
ስለ ያዕቆብ ንግግር
13እነርሱም ጸጥ ባሉ ጊዜ ያዕቆብ መልሶ እንዲህ አለ፥ “ወንድሞች ሆይ፥ ስሙኝ። 14ስምዖንም፥ እግዚአብሔር አስቀድሞ አሕዛብን ይቅር እንዳላቸውና ከውስጣቸውም ለስሙ ሕዝብን እንደ መረጠ ተናግሮአል። 15በዚህም መጽሐፍ እንዲህ ብሎ እንደ ተናገረ የነቢያት ቃል ይስማማል። 16ከዚህም በኋላ የወደቀችውን የዳዊትን ቤት መልሼ እሠራታለሁ፤ ፍራሽዋንም አድሳለሁ፤ 17የቀሩት ሰዎችና ስሜም የተጠራባቸው አሕዛብ ሁሉ እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ፥ ይላል ይህን የሚያደርግ እግዚአብሔር፤ 18#አሞ. 9፥11-12። ከጥንት ጀምሮ ሥራው ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ የታወቀ ነው።
19“አሁንም ወደ እግዚአብሔር በተመለሱ አሕዛብ ላይ ሥርዐት አታክብዱ እላችኋለሁ። 20#ዘፀ. 34፥15-17፤ ዘሌ. 17፥10-16፤ 18፥6-23። ነገር ግን ለጣዖት ከሚሠዋው፥ ከዝሙት፥ ሞቶ የተገኘውንና ደም ከመብላት እንዲርቁ፥ ለራሳቸው የሚጠሉትንም በወንድሞቻቸው ላይ እንዳያደርጉ እዘዙአቸው። 21ሙሴም ከጥንት ጀምሮ በየከተማዉ የሚሰብክላቸው ትምህርት ነበር፤ በየምኵራቡም በየሰንበቱ ያነብቡት ነበር።”
ስለ ሐዋርያት ጉባኤ መልእክት
22ከዚህም በኋላ ሐዋርያትና ቀሳውስት ሕዝቡም ሁሉ ከጳውሎስና ከበርናባስ ጋር ወደ አንጾኪያ የሚልኳቸውን ሰዎች ይመርጡ ዘንድ ተስማሙ፤ ከባልንጀሮቻቸው መካከልም የተማሩትን ሰዎች በርናባስ የተባለ ይሁዳንና ሲላስን መረጡ። 23እንዲህ የምትል መልእክትም በእጃቸው ጻፉ፤ “ከሐዋርያትና ከቀሳውስት ከወንድሞችም በአንጾኪያ፥ በሶርያና በኪልቅያ ለሚኖሩ፥ ከአሕዛብ ላመኑ ወንድሞቻችን ትድረስ፤ ሰላም ለእናንተ ይሁን፥ ደስ ይበላችሁ። 24ያላዘዝናቸው ሰዎች ከእኛ ወጥተው፦ ‘ትገዘሩ ዘንድና የኦሪትንም ሕግ ትጠብቁ ዘንድ ይገባችኋል’ ብለው በነገር እንደ አወኩአችሁና ልባችሁን እንደ አናወጡት ሰምተናል። 25ሁላችን ከተሰበሰብን በኋላ በአንድ ቃል በየን፤ አንድ ሆነንም ከወንድሞቻችን ከጳውሎስና ከበርናባስ ጋር ወደ እናንተ የምንልካቸውን ሰዎች መረጥን። 26እነርሱም ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰውነታቸውን አሳልፈው የሰጡ ሰዎች ናቸው። 27ይሁዳንና ሲላስን ልከናቸዋልና እነርሱ በቃላቸው ይህን ያስረዱአችኋል። 28ሥርዐት እንዳናከብድ ሌላም ሸክም እንዳንጨምር መንፈስ ቅዱስ ከእኛ ጋር ነውና፤ ነገር ግን ይህን በግድ ትተዉ ዘንድ እናዝዛችኋለን። 29ለአማልክት የተሠዋውን፥ ሞቶ የተገኘውን፥ ደምንም አትብሉ፤ ከዝሙትም ራቁ፤ በራሳችሁ የምትጠሉትንም በወንድሞቻችሁ ላይ አታድርጉ፥ ከእነዚህ ሥራዎችም ሰውነታችሁን ብትጠብቁ በሰላም ትኖራላችሁ፤ ደኅና ሁኑ።”
30እነርሱም ተልከው ወደ አንጾኪያ ወረዱ፤ ሕዝቡንም ሰብስበው የተላከውን ደብዳቤ ሰጡአቸው። 31እነርሱም አንብበው እጅግ ደስ አላቸው፥ ተጽናኑም። 32ይሁዳና ሲላስም መምህራን ነበሩና አስተማሩአቸው፤ ወንድሞችንም በብዙ ቃል አጽናኑአቸው። 33በእነርሱም ዘንድ አያሌ ቀን ከተቀመጡ በኋላ ወንድሞቻቸውን ተሰናብተው በሰላም ወደ ሐዋርያት ተመለሱ። 34ሲላስ ግን በዚያ ሊቈይ ወደደ። 35ጳውሎስና በርናባስም በአንጾኪያ ቈዩ፤ ከሌሎች ብዙ ሰዎች ጋርም የእግዚአብሔርን ቃል ሰበኩ፤ አስተማሩም።
ጳውሎስና በርናባስ እንደ ተለያዩ
36ከጥቂት ቀን በኋላም ጳውሎስ በርናባስን፦“እንግዲህስ እንመለስና የእግዚአብሔርን ቃል ባስተማርንባቸው ሀገሮች ያሉትን ወንድሞች እንጐብኛቸው፤ እንዴት እንዳሉም እንወቅ” አለው። 37በርናባስም ማርቆስ የተባለውን ዮሐንስን ከእነርሱ ጋር ይዞት ሊሄድ ወደደ። 38#የሐዋ. 13፥13። ጳውሎስ ግን ከእነርሱ ጋር ሊወስደው አልፈቀደም፤ እነርሱ በጵንፍልያ ሳሉ ትቶአቸው ሄዶአልና፤ አብሮአቸውም ለሥራ አልመጣም ነበርና። 39ስለዚህም ተኰራርፈው እርስ በርሳቸው ተለያዩ፤ በርናባስም ማርቆስን ይዞ በመርከብ ወደ ቆጵሮስ ሄደ። 40ጳውሎስ ግን ሲላስን መረጠ፤ ወንድሞችም ለእግዚአብሔር ጸጋ አደራ ከሰጡት በኋላ ሄደ። 41በሶርያና በኪልቅያም እየዞረ አብያተ ክርስቲያናትን አጽናና።
Currently Selected:
የሐዋርያት ሥራ 15: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ