የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 20

20
የጳ​ው​ሎስ ጕዞ ወደ መቄ​ዶ​ን​ያና ወደ ግሪክ ሀገር
1ክር​ክ​ሩም ከተ​ፈ​ጸመ በኋላ ጳው​ሎስ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱን ጠራና አጽ​ና​ና​ቸው፤ ተሰ​ና​በ​ታ​ቸ​ውም፤ ወጥ​ቶም ወደ መቄ​ዶ​ንያ ሄደ። 2በዚያ አው​ራ​ጃም አልፎ ሄደ፤ በቃ​ሉም ብዙ አስ​ተ​ማ​ራ​ቸው፤ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ግሪክ ሀገር ሄደ። 3በዚ​ያም ሦስት ወር ተቀ​መጠ፤ ወደ ሶር​ያም በመ​ር​ከብ ለመ​ሄድ ዐስቦ ሳለ አይ​ሁድ ስለ ተማ​ከ​ሩ​በት ወደ መቄ​ዶ​ንያ ሊመ​ለስ ቈረጠ። 4ከእ​ር​ሱም ጋር የቤ​ርያ ሀገር ሰው የሚ​ሆን ሱሲ​ጳ​ጥ​ሮስ፥ የተ​ሰ​ሎ​ን​ቄም ሰዎች አር​ስ​ጥ​ሮ​ኮ​ስና ሲኮ​ን​ዱስ፥ የደ​ር​ቤኑ ሰው ጋይ​ዮ​ስና ጢሞ​ቴ​ዎ​ስም፥ የእ​ስያ ሰዎች የሚ​ሆኑ ቲኪ​ቆ​ስና ጥሮ​ፊ​ሞ​ስም አብ​ረ​ውት ሄዱ። 5እነ​ር​ሱም ቀድ​መ​ውን ሄደው በጢ​ሮ​አስ ቆዩን።
ጳው​ሎስ ጢሮ​አ​ስን ለመ​ጨ​ረሻ ጊዜ እንደ ጐበኘ
6እኛ ግን ከፋ​ሲካ በኋላ ከፊ​ል​ጵ​ስ​ዩስ ተነ​ሥ​ተን በባ​ሕር ላይ ተጕ​ዘን በአ​ም​ስት ቀን ወደ ጢሮ​አስ ደረ​ስን፤ በዚ​ያም ሰባት ቀን ተቀ​መ​ጥን። 7ከሳ​ም​ን​ቱም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን እሑድ ማዕድ ለመ​ባ​ረክ ተሰ​ብ​ስ​በን ሳለን ጳው​ሎስ በማ​ግ​ሥቱ የሚ​ሄድ ነውና ያስ​ተ​ም​ራ​ቸው ጀመረ፤ እስከ መን​ፈቀ ሌሊ​ትም ድረስ ትም​ህ​ር​ቱን አስ​ረ​ዘመ። 8ተሰ​ብ​ስ​በን በነ​በ​ር​ን​በት ሰገ​ነ​ትም ብዙ መብ​ራት ነበር። 9ስሙ አው​ጤ​ክስ የሚ​ባል አንድ ጐል​ማሳ ልጅም በመ​ስ​ኮት በኩል ተቀ​ምጦ ሳለ ከባድ እን​ቅ​ልፍ አን​ቀ​ላ​ፍቶ ነበር፤ ጳው​ሎ​ስም ትም​ህ​ር​ቱን ባስ​ረ​ዘመ ጊዜ ያ ጐል​ማሳ ከእ​ን​ቅ​ልፉ ብዛት የተ​ነሣ ከተ​ኛ​በት ከሦ​ስ​ተ​ኛው ፎቅ ወደ ታች ወደቀ፤ ሬሳ​ው​ንም አነ​ሡት። 10ጳው​ሎ​ስም ወርዶ በላዩ ወደቀ፤ አቅ​ፎም ያዘው፤ እነ​ር​ሱ​ንም፥ “ነፍሱ አለ​ችና አት​ደ​ን​ግጡ” አላ​ቸው። 11ከዚ​ህም በኋላ ወደ ሰገ​ነት ወጣ፤ ማዕ​ዱ​ንም ባርኮ በላ፤ እስ​ኪ​ነ​ጋም ድረስ ብዙ ትም​ህ​ርት አስ​ተ​ማ​ራ​ቸው፤ ከዚያ በኋ​ላም ተነ​ሥቶ ሄደ። 12ብላ​ቴ​ና​ው​ንም ደኅና ሆኖ ወሰ​ዱት፤ እጅ​ግም ደስ አላ​ቸው።
13እኛ ግን በመ​ር​ከብ ሆነን ወደ አሶስ ሄድን፤ ከዚያ ጳው​ሎ​ስን ልን​ቀ​በ​ለው እንሻ ነበ​ርና፤ እን​ደ​ዚሁ በእ​ግር እን​ደ​ሚ​መጣ ነግ​ሮን ነበ​ርና ተቀ​በ​ል​ነው። 14አሶ​ስም ደረ​ስን፤ በመ​ር​ከ​ብም ይዘ​ነው ወደ ሚጢ​ሊኒ ሄድን። 15በማ​ግ​ሥ​ቱም ከዚያ ወጥ​ተን በኪ​ዮስ ፊት ለፊት ደረ​ስን፤ በማ​ግ​ሥ​ቱም ወደ ሳሞስ አለ​ፍን፤ በት​ሮ​ጊ​ሊ​ዮም ተቀ​መ​ጥን፤ ከዚህ ቀን በኋ​ላም ወደ መሊጡ ደረ​ስን። 16ጳው​ሎ​ስም በእ​ስያ እን​ዳ​ይ​ዘ​ገይ በኤ​ፌ​ሶን በኩል ሊሄድ ቈርጦ ነበር፤ የሚ​ቻ​ለ​ውም ቢሆን ለበ​ዓለ ኀምሳ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ለመ​ድ​ረስ ቸኵሎ ነበ​ርና።
17ከመ​ሊ​ጡም የቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንን ቀሳ​ው​ስት ይጠ​ሩ​አ​ቸው ዘንድ ወደ ኤፌ​ሶን ላከ። 18ወደ እር​ሱም በመጡ ጊዜ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ወደ እስያ ከገ​ባ​ሁ​በት ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ጀምሮ በዘ​መኑ ሁሉ ከእ​ና​ንተ ዘንድ እንደ ተቀ​መ​ጥሁ እና​ንተ ታው​ቃ​ላ​ችሁ። 19እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እያ​ገ​ለ​ገ​ልሁ በፍ​ጹም መከ​ራና በል​ቅሶ ከአ​ይ​ሁ​ድም ሴራ የተ​ነሣ በደ​ረ​ሰ​ብኝ ፈተና እየ​ተ​ጋ​ደ​ልሁ፥ 20በጉ​ባ​ኤም ሆነ በቤት ስነ​ግ​ራ​ች​ሁና ሳስ​ተ​ም​ራ​ችሁ ከሚ​ጠ​ቅ​ማ​ችሁ ነገር አን​ዳች ስን​ኳን አላ​ስ​ቀ​ረ​ሁ​ባ​ች​ሁም። 21ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መመ​ለ​ስ​ንና በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ማመ​ንን ለአ​ይ​ሁ​ድና ለአ​ረ​ማ​ው​ያን እየ​መ​ሰ​ከ​ርሁ፤ 22አሁ​ንም እነሆ በመ​ን​ፈስ ታሥሬ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እሄ​ዳ​ለሁ፤ ነገር ግን በዚያ የሚ​ያ​ገ​ኘ​ኝን አላ​ው​ቅም። 23ነገር ግን መን​ፈስ ቅዱስ፦ በየ​ከ​ተ​ማው መከ​ራና እስ​ራት ይጠ​ብ​ቅ​ሃል ብሎ ይመ​ሰ​ክ​ር​ል​ኛል። 24ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የጸ​ጋ​ውን ወን​ጌል እን​ዳ​ስ​ተ​ምር ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የተ​ቀ​በ​ል​ሁ​ትን ሩጫ​ዬን እን​ድ​ጨ​ር​ስና መል​እ​ክ​ቴ​ንም እን​ድ​ፈ​ጽም ነው እንጂ ለሰ​ው​ነቴ ምንም አላ​ስ​ብ​ላ​ትም።#2ጢሞ. 4፥7። 25አሁ​ንም እነሆ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት የሰ​በ​ክ​ሁ​ላ​ችሁ እና​ንተ ሁላ​ችሁ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ፊቴን እን​ደ​ማ​ታ​ዩኝ እኔ ዐው​ቄ​አ​ለሁ። 26እኔ ከሁ​ላ​ች​ሁም ደም ንጹሕ እንደ ሆንሁ እነሆ ዛሬ በዚች ሌሊት እመ​ሰ​ክ​ር​ላ​ች​ኋ​ለሁ። 27ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምክር ሁሉ የሰ​ወ​ር​ኋ​ች​ሁና ያል​ነ​ገ​ር​ኋ​ችሁ የለም። 28አሁ​ንም በገዛ ደሙ የዋ​ጃ​ትን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ትጠ​ብቁ ዘንድ መን​ፈስ ቅዱስ እና​ን​ተን ጳጳ​ሳት አድ​ርጎ ለሾ​መ​ባት ለመ​ን​ጋው ሁሉና ለራ​ሳ​ችሁ ተጠ​ን​ቀቁ። 29ከእኔ በኋላ ለመ​ን​ጋ​ዪቱ የማ​ይ​ራሩ ነጣ​ቂ​ዎች ተኵ​ላ​ዎች እን​ደ​ሚ​መጡ እኔ አው​ቃ​ለሁ። 30ደቀ መዛ​ሙ​ር​ት​ንም ወደ እነ​ርሱ ይመ​ልሱ ዘንድ ጠማማ ትም​ህ​ር​ትን የሚ​ያ​ስ​ተ​ምሩ ሰዎች ከእ​ና​ንተ መካ​ከል ይነ​ሣሉ። 31ስለ​ዚ​ህም ትጉ፤ እኔ ሁላ​ች​ሁ​ንም ሳስ​ተ​ምር ሦስት ዓመት ሙሉ ሌትም ቀንም እን​ባዬ እን​ዳ​ል​ተ​ገታ ዐስቡ። 32አሁ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና ሊያ​ን​ጻ​ችሁ፥ በቅ​ዱ​ሳ​ንም ሁሉ መካ​ከል ርስ​ትን ሊሰ​ጣ​ችሁ ለሚ​ች​ለው ለጸ​ጋው ቃል አደራ ሰጥ​ቻ​ች​ኋ​ለሁ። 33ወር​ቅም ቢሆን፥ ብርም ቢሆን፥ ልብ​ስም ቢሆን ከእ​ና​ንተ ከአ​ንዱ ስንኳ አል​ተ​መ​ኘ​ሁም። 34እነ​ዚ​ህም እጆች ለም​ሻው ነገ​ርና ከእ​ኔም ጋር ላሉት እን​ዳ​ገ​ለ​ገሉ እና​ንተ ታው​ቃ​ላ​ችሁ። 35በድ​ካ​ማ​ች​ንና በሥ​ራ​ችን ነዳ​ያ​ንን እን​ቀ​በ​ላ​ቸው ዘንድ እን​ደ​ሚ​ገ​ባን ይህን አስ​ተ​ም​ሬ​አ​ች​ኋ​ለሁ፤ ‘ከሚ​ቀ​በል ይልቅ የሚ​ሰጥ ብፁዕ ነው’ ያለ​ው​ንም የጌ​ታ​ች​ንን የኢ​የ​ሱ​ስን ቃል ዐስቡ።”
36ይህ​ንም ከአለ በኋላ ተን​በ​ር​ክኮ አብ​ረ​ውት ካሉት ሁሉ ጋር ጸለየ። 37ሁሉም እጅግ አለ​ቀሱ፤ ጳው​ሎ​ስ​ንም አን​ገ​ቱን አቅ​ፈው ሳሙት። 38ይል​ቁ​ንም “ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ፊቴን አታ​ዩ​ትም” ስለ አላ​ቸው እጅግ አዘኑ። እስከ መር​ከ​ብም ድረስ ሸኙት።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ