የሐዋርያት ሥራ 28
28
ጳውሎስ በመላጥያ ደሴት
1ከዚህም በኋላ በደኅና በደረስን ጊዜ ደሴቲቱ መላጥያ እንደምትባል ዐወቅን። 2በዚያ የሚኖሩት አረማውያንም አዘኑልን፤ መልካም ነገርንም አደረጉልን፤ ከቍሩም ጽናትና ከዝናሙ ብዛት የተነሣ እሳት አንድደው እንድንሞቅ ሁላችንንም ሰበሰቡን። 3ጳውሎስም ብዙ ጭራሮ ሰብስቦ በእሳቱ ላይ ጨመረው፤ እፉኝትም ከእሳቱ ወላፈን የተነሣ ወጥታ ጳውሎስን እጁን ነደፈችው። 4አረማውያንም እፉኝቱ በጳውሎስ እጅ ላይ ተንጠልጥላ ባዩ ጊዜ እርስ በርሳቸው፥ “ይህ ሰው ነፍሰ ገዳይ ይመስላል፤ ከባሕር እንኳ በደኅና ቢወጣም በሕይወት ይኖር ዘንድ የእግዚአብሔር ፍርድ አልተወውም” አሉ። 5ጳውሎስ ግን እጁን አራግፎ እፉኝቱን በእሳት ውስጥ ጣላት፤ ጕዳትም አላገኘውም። 6እነርሱ ግን ወዲያውኑ የሚያብጥ ወይም ሞቶ የሚወድቅ መስሎአቸው ነበር። እያዩትም ብዙ ሰዓት ቆሙ፤ አንዳችም እንደ አልጐዳው በአዩ ጊዜም፥ “ይህስ አምላክ ነው” ብለው ቃላቸውን ለወጡ።
7በዚያ ቦታም አጠገብ ስሙን ፑፕልዮስ የሚሉት የደሴቲቱ አለቃ መሬት ነበር፤ እርሱም ሦስት ቀን ሙሉ በደስታ በቤቱ ተቀብሎ አስተናገደን። 8የፑፕልዮስም አባት በንዳድና በተቅማጥ ታሞ ተኝቶ ይኖር ነበር፤ ጳውሎስም እርሱ ወዳለበት ገብቶ ጸለየለት፤ እጁንም በላዩ ጭኖ ፈወሰው። 9ያደረገውንም ይህን ተአምር ባዩ ጊዜ በዚያች ደሴት ያሉትን ድውያን ሁሉ አመጡለት፤ ፈወሳቸውም። 10እጅግ ታላቅ ክብርም አከበሩን፤ ከእነርሱም ዘንድ ለመሄድ በተነሣን ጊዜ የሚያስፈልገንን ስንቅ ሰጡን።
ከመላጥያ ወደ ሮም ስለ መጓዛቸው
11ከሦስት ወር በኋላም በዚያች ደሴት ወደ ከረመችው ወደ እስክንድርያ መርከብ ወጣን፤ በዚያች መርከብ ላይም የዲዮስቆሮስ ምልክት ነበረባት፤ ይኸውም “የመርከበኞች አምላክ”#“የመርከበኞች አምላክ” የሚለው በግሪኩ የለም። የሚሉት ነው። 12ከዚያም ሄደን ወደ ሰራኩስ ደረስን፤ በዚያም ሦስት ቀን ተቀመጥን። 13ከዚያም ሄደን ሬቅዩን ወደምትባል ሀገር ደረስን፤ በማግሥቱም ወጣን፤ ከአንድ ቀንም በኋላ ከጐንዋ ነፋስ በነፈሰ ጊዜ በሁለተኛው ቀን ወደ ፑቲዮሉስ#አንዳንድ የግእዝ ዘርዕ “ፑቲዮሉስ እንተ ሀገረ ኢጣልያ” ይላል። ደረስን። 14በዚያም ወንድሞችን አግኝተን ተቀበሉን፤ በእነርሱ ዘንድም ሰባት ቀን እንድንቀመጥ ለመኑን፤ ከዚያም በኋላ ሄደን ወደ ሮሜ ደረስን። 15በዚያም ያሉት ወንድሞች ስለ እኛ በሰሙ ጊዜ፤ አፍዩስ ፋሩስ እስከሚባለው ገበያና እስከ ሦስተኛው ማረፊያ ድረስ ወጥተው ተቀበሉን፤ ጳውሎስም ባያቸው ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገነ፤ ልቡም ተጽናና። 16ወደ ሮሜም በገባን ጊዜ የመቶ አለቃው እስረኞችን ለሠራዊቱ አለቃ አስረከበ፤ ጳውሎስ ግን ከሚጠብቀው አንድ ወታደር ጋር ለብቻው ይቀመጥ ዘንድ ፈቀደለት።
ጳውሎስ ከአይሁድ ሊቃውንት ጋር ስለ መነጋገሩ
17ከሦስት ቀንም በኋላ ጳውሎስ የአይሁድን ታላላቅ ሰዎች ሰበሰባቸው፤ በተሰበሰቡም ጊዜ እንዲህ አላቸው፥ “ወንድሞቻችን ሆይ፥ እኔ በሕዝቡም ላይ ቢሆን፥ በአባቶቻችንም ሕግ ላይ ቢሆን ያደረግሁት ክፉ ነገር የለም፤ ነገር ግን በኢየሩሳሌም እንደ ታሰርሁ ለሮም ሰዎች አሳልፈው ሰጡኝ። 18እነርሱም መርምረው ለሞት የሚያበቃ በደል ስለአላገኙብኝ ሊፈቱኝ ወደዱ። 19#የሐዋ. 25፥11። አይሁድ ግን ሊቃወሙኝ በተነሡ ጊዜ ወደ ቄሣር ይግባኝ ለማለት ግድ ሆነብኝ፤ ነገር ግን ወገኖችን የምከስበት ነገር ኖሮኝ አይደለም። 20ስለዚህም ላያችሁ፥ ልነግራችሁና ላስረዳችሁ ወደ እኔ እንድትመጡ ማለድኋችሁ፤ ስለ እስራኤል ተስፋ በዚህ ሰንሰለት ታስሬአለሁና።” 21የአይሁድ ታላላቅ ሰዎችም እንዲህ አሉት፥ “ለእኛስ ከይሁዳ ሀገር ስለ አንተ መልእክት አልደረሰንም፤ ከኢየሩሳሌም#“ከኢየሩሳሌም” የሚለው በግሪኩ ዘር የለም። ከመጡት ወንድሞችም ቢሆን አንድ ስንኳ ከዚህ አስቀድሞ ስለ አንተ ክፉ ነገር ያወራን፥ የነገረንም የለም። 22ነገር ግን በዚህ ነገር በየስፍራው ሁሉ እንዲጣሉ በእኛ ዘንድ ታውቋልና የአንተን ዐሳብ ደግሞ ከአንተ እንሰማ ዘንድ እንወድዳለን።” 23ከዚህም በኋላ ወደ እርሱ የሚመጡበትን ቀን ቀጠሩትና ብዙዎች ወዳረፈበት ወደ እርሱ መጡ፤ ከጥዋትም ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት እየመሰከረ ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስም ከሙሴ ኦሪትና ከነቢያት እየጠቀሰ ነገራቸው። 24ከእነርሱም እኩሌቶቹ የተናገረውን አመኑ፤ እኩሌቶቹ ግን አልተቀበሉትም። 25እርስ በርሳቸውም ባልተስማሙ ጊዜ ጳውሎስ አንዲት ቃል ከተናገረ በኋላ ከእርሱ ተመለሱ፤ እንዲህም አላቸው፥ “መንፈስ ቅዱስ በነቢዩ በኢሳይያስ አንደበት ለአባቶቻችን በእውነት እንዲህ ብሎ መልካም ነገር ተናግሮአል። 26‘ወደዚህ ሕዝብ ሂድና እንዲህ በላቸው፦ መስማትን ትሰማላችሁ፤ ግን አታስተውሉም፤ ማየትንም ታያላችሁ፤ ግን አትመለከቱም። 27#ኢሳ. 6፥9-10። በዐይናቸው እንዳያዩ፥ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ ወደ እኔም እንዳይመለሱና ይቅር እንዳልላቸው#በግሪኩ “እንዳልፈውሳቸው” ይላል። የዚህ ሕዝብ ልባቸው ደንድኖአልና፥ ጆሮአቸውም ደንቁሮአልና፥ ዐይናቸውንም ጨፍነዋልና’። 28እንግዲህ ከእግዚአብሔር የተገኘች ይህቺ ድኅነት ለአሕዛብ እንደምትሆን ዕወቁ፤ እነርሱም ይሰሙታል።” 29ይህንም በተናገራቸው ጊዜ አይሁድ እርስ በርሳቸው እጅግ እየተከራከሩ ወጥተው ሄዱ። 30ጳውሎስም በገንዘቡ በተከራየው ቤት ሁለት ዓመት ተቀመጠ፤ ወደ እርሱ የሚመጣውንም ሁሉ ይቀበል ነበር። 31ማንም ሳይከለክለው የእግዚአብሔርን መንግሥት ይሰብክ ነበር፤ ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስም እጅግ ገልጦ ያስተምር ነበር። 32ጳውሎስም በመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኔሮን ቄሣር ገብቶ ነበርና ረትቶ በሰላም ሄደ፤ ከዚህም በኋላ ሁለት ዓመት ኖሮ ከሮም ወጣ። 33ከዚህም በኋላ ወደ ሮም ተመልሶ የኔሮን ቄሣር ዘመዶችን አጠመቀ፤ በኔሮን ትእዛዝም በሰይፍ ተመትቶ መከራውንም ታግሦ ሰማዕት ሆነ።#ምዕ. 28 ቍ. 32 እና 33 በአንዳንድ የግእዝ ዘርዕ ብቻ የሚገኝ ነው።
ወንጌላዊው ሉቃስ የጻፈው የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ተፈጸመ።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን አሜን።
Currently Selected:
የሐዋርያት ሥራ 28: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ