የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 6

6
ስለ ሰብ​ዐቱ ዲያ​ቆ​ናት መሾም
1በዚ​ያም ወራት ደቀ መዛ​ሙ​ርት በበዙ ጊዜ ከግ​ሪክ የመጡ ደቀ መዛ​ሙ​ርት በአ​ይ​ሁድ ምእ​መ​ናን ላይ አን​ጐ​ራ​ጐ​ሩ​ባ​ቸው፤ የዕ​ለት የዕ​ለ​ቱን ምግብ ሲያ​ካ​ፍሉ ባል​ቴ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ቸል ይሉ​ባ​ቸው ነበ​ርና። 2ዐሥራ ሁለ​ቱም ሐዋ​ር​ያት ሕዝ​ቡን ሁሉ ጠር​ተው እን​ዲህ አሉ​አ​ቸው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ትተን ማዕ​ድን እና​ገ​ለ​ግል ዘንድ የሚ​ገባ አይ​ደ​ለም። 3ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ከእ​ና​ንተ ወገን በመ​ል​ካም የተ​መ​ሰ​ከ​ረ​ላ​ቸ​ውን መን​ፈስ ቅዱ​ስና ጥበብ የሞ​ላ​ባ​ቸ​ውን ሰባት ሰዎ​ችን ምረጡ፤ ለዚህ ሥራም እን​ሾ​ማ​ቸ​ዋ​ለን። 4እኛ ግን ለጸ​ሎ​ትና ቃሉን ለማ​ስ​ተ​ማር እን​ተ​ጋ​ለን።” 5#አን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ “ሕዝ​ቡም ሁሉ ተስ​ማሙ” የሚል ይጨ​ም​ራል።ይህም ነገር በእ​ነ​ርሱ ዘንድ የተ​ወ​ደደ ሆነ፤ ሃይ​ማ​ኖቱ የቀ​ናና መን​ፈስ ቅዱስ ያደ​ረ​በ​ትን ሰው እስ​ጢ​ፋ​ኖ​ስን፥ ፊል​ጶ​ስን፥ ጵሮ​ኮ​ሮ​ስን፥ ኒቃ​ሮ​ናን፥ ጢሞ​ናን፥ ጰር​ሜ​ናን፥ ወደ ይሁ​ዲ​ነት የተ​መ​ለ​ሰ​ውን የአ​ን​ጾ​ኪ​ያ​ውን ኒቆ​ላ​ዎ​ስ​ንም መረጡ። 6በሐ​ዋ​ር​ያ​ትም ፊት አቆ​ሙ​አ​ቸው፤ ጸል​የ​ውም እጃ​ቸ​ውን በራ​ሳ​ቸው ላይ ጫኑ።
7የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ከፍ ከፍ አለ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ምእ​መ​ናን እጅግ በዙ፤ ከካ​ህ​ና​ትም መካ​ከል ያመኑ ብዙ​ዎች ነበሩ።
አይ​ሁድ እስ​ጢ​ፋ​ኖ​ስን እንደ ተቃ​ወ​ሙት
8እስ​ጢ​ፋ​ኖ​ስም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋና ኀይል የመ​ላ​በት ሰው ነበር፤ በሕ​ዝ​ቡም መካ​ከል ታላ​ላቅ ተአ​ም​ራ​ት​ንና ድንቅ ሥራን ይሠራ ነበር። 9የነጻ ወጭ​ዎች ከም​ት​ባ​ለው ምኵ​ራ​ብም ከቀ​ሬ​ናና ከእ​ስ​ክ​ን​ድ​ርያ፥ ከቂ​ል​ቅ​ያና ከእ​ስያ የሆኑ ሰዎ​ችም ተነ​ሥ​ተው እስ​ጢ​ፋ​ኖ​ስን ይከ​ራ​ከ​ሩት ነበር። 10ነገር ግን ይቃ​ወ​ሙት ዘንድ አል​ቻ​ሉም፤ በጥ​በ​ብና በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ይከ​ራ​ከ​ራ​ቸው ነበ​ርና። 11ከዚ​ህም በኋላ “ይህን ሰው በሙ​ሴና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ የስ​ድ​ብን ቃል ሲና​ገር ሰም​ተ​ነ​ዋል” የሚሉ የሐ​ሰት ምስ​ክ​ሮ​ችን አስ​ነ​ሡ​በት፤ 12ሕዝ​ቡን፥ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ች​ንና ጸሓ​ፊ​ዎ​ች​ንም አነ​ሳ​ሡ​አ​ቸው፤ ከበ​ውም እየ​ጐ​ተቱ ወደ ሸንጎ አቀ​ረ​ቡት። 13የሐ​ሰት ምስ​ክ​ሮ​ች​ንም አቆ​ሙ​በት፤ እነ​ር​ሱም እን​ዲህ አሉ፥ “ይህ ሰው በዚህ ቤተ መቅ​ደስ ላይና በኦ​ሪት ላይ የስ​ድብ ቃል እየ​ተ​ና​ገረ ዝም በል ቢሉት እንቢ አለ፤ 14የና​ዝ​ሬቱ ኢየ​ሱስ ይህን ቤተ መቅ​ደስ ያፈ​ር​ሰ​ዋል፤ ሙሴም የሰ​ጠ​ንን ኦሪ​ታ​ች​ንን ይሽ​ራል ሲል ሰም​ተ​ነ​ዋል።” 15በሸ​ን​ጎም ተቀ​ም​ጠው የነ​በ​ሩት ሁሉ ትኩር ብለው ተመ​ለ​ከ​ቱት፤ ፊቱ​ንም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ፊት ሆኖ አዩት።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ