የሐዋርያት ሥራ 8
8
በቤተ ክርስቲያን ስለ ደረሰው ስደት
1በዚያ ወራትም በኢየሩሳሌም ባለችው ቤተ ክርስቲያን ላይ ታላቅ ስደት ሆነ፤ ከሐዋርያትም በቀር ሁሉም በይሁዳና በሰማርያ ባሉ አውራጃዎች ሁሉ ተበተኑ። 2እስጢፋኖስንም ደጋግ ሰዎች አንሥተው ቀበሩት፤ ታላቅ ልቅሶም አለቀሱለት።
ሳውል ቤተ ክርስቲያንን እንደ አሳደደ
3 #
የሐዋ. 22፥4-5፤ 26፥9-11። ሳውል ግን ገና አብያተ ክርስቲያናትን ይቃወም ነበር፤ የሰውንም ቤት ሁሉ ይበረብር ነበር፤ ወንዶችንም ሴቶችንም እየጐተተ ወደ ወኅኒ ቤት ያስገባቸው ነበር። 4የተበተኑት ግን እየተዘዋወሩ የእግዚአብሔርን ቃል ሰበኩ፥ አስተማሩም። 5ፊልጶስም ወደ ሰማርያ ከተማ ወረደ፤ ስለ ክርስቶስም ሰበከላቸው። 6ሕዝቡም የነገራቸውን በሰሙና ያደርገው የነበረውን ተአምራት በአዩ ጊዜ በአንድ ልብ የፊልጶስን ነገር ተቀበሉ። 7ርኩሳን መናፍስት ያደሩባቸውም ብዙዎች ነበሩና፥ በታላቅ ቃል እየጮኹ ይወጡ ነበር፤ ብዙዎች ልምሾዎችና አንካሶችም ይፈወሱ ነበር። 8በዚያችም ከተማ ታላቅ ደስታ ሆነ። 9በዚያችም ከተማ ሲሞን የሚባል አንድ ሰው ነበር፤ የሰማርያ ሰዎችንም ያስት ነበር፤ ሰውየዉ ሥራየኛ ነበር፤ ራሱንም ታላቅ ያደርግ ነበር። 10ከታናናሾቹም ጀምሮ እስከ ታላላቆቹ ድረስ “ታላቁ የእግዚአብሔር ኀይል ይህ ነው” እያሉ ሁሉም ያደምጡት ነበር። 11ከብዙ ዘመንም ጀምሮ በጥንቈላው ያታልላቸው ስለ ነበር ያዳምጡት ነበር። 12ነገር ግን ፊልጶስ ስለ እግዚአብሔር መንግሥትና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰብኮላቸው በአመኑ ጊዜ ሴቶችም ወንዶችም ተጠመቁ። 13ሲሞንም ወዲያውኑ አምኖ ተጠመቀ፤ ፊልጶስንም ይከተል ጀመር፤ በፊልጶስም እጅ የሚደረገውን ተአምርና ታላቅ ኀይል ባየ ጊዜ ይደነቅ ነበር።
14በኢየሩሳሌም የነበሩ ሐዋርያትም የሰማርያ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል እንደ ተቀበሉ በሰሙ ጊዜ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ወደ እነርሱ ላኩላቸው። 15ወርደውም መንፈስ ቅዱስን እንዲቀበሉ ጸለዩላቸው። 16በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ እንጂ ከመካከላቸው በአንዱ ላይ ስንኳ መንፈስ ቅዱስ ገና አልወረደም ነበርና። 17በዚያ ጊዜም እጃቸውን ጫኑባቸው፤ መንፈስ ቅዱስንም ተቀበሉ። 18ሲሞንም ሐዋርያት እጃቸውን በጫኑበት ሰው ላይ መንፈስ ቅዱስ እንደሚወርድ ባየ ጊዜ ገንዘብ አመጣላቸውና፥ 19“እጄን በምጭንበት ሰው ላይ መንፈስ ቅዱስ ይወርድ ዘንድ ለእኔም ይህን ሥልጣን ስጡኝ” አላቸው። 20ጴጥሮስ ግን እንዲህ አለው፥ “የእግዚአብሔርን ጸጋ በገንዘብ ልትገዛ ዐስበሃልና ገንዘብህ ከአንተ ጋር ይጥፋ። 21በዚህ ነገር ዕድልና ርስት የለህም፥ በእግዚአብሔር ፊት ልብህ የቀና አይደለምና። 22አሁንም ከክፋትህ ተመለስና ንስሓ ግባ። የልቡናህንም ዐሳብ ይተውልህ እንደ ሆነ እግዚአብሔርን ለምን። 23በመራራ መርዝ ተመርዘህ፥ በዐመፃ ማሰሪያ ተተብትበህ የምትኖር ሆነህ አይሃለሁና።” 24ሲሞንም መልሶ፥ “ካላችሁት ሁሉ ምንም እንዳይደርስብኝ እናንተ ወደ እግዚአብሔር ለምኑልኝ” አለ። 25እነርሱም ከመሰከሩና የእግዚአብሔርን ቃል ከተናገሩ በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ በብዙዎች የሰማርያ መንደሮችም የእግዚአብሔርን ቃል አስተማሩ።
ስለ ፊልጶስና ስለ ኢትዮጵያዊዉ ጃንደረባ
26የእግዚአብሔር መልአክም ፊልጶስን ተናገረው፤ እንዲህም አለው፥ “በቀትር ጊዜ ተነሣና በደቡብ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ በሚያወርደው በምድረ በዳው መንገድ ሂድ።” 27ተነሥቶም ሄደ፤ እነሆም፥ የኢትዮጵያ ንግሥት የሕንደኬ ጃንደረባ ከሹሞችዋ የበለጠ፥ በሀብቷም ሁሉ ላይ በጅሮንድ የነበረ፥ አንድ የኢትዮጵያ ሰው ነበር፤ እርሱም ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ። 28ሲመለስም በሰረገላው ላይ ተቀምጦ የነቢዩ የኢሳይያስን መጽሐፍ ያነብ ነበር። 29መንፈስ ቅዱስም ፊልጶስን፥ “ሂድ፤ ይህን ሰረገላ ተከተለው” አለው። 30ፊልጶስም ፈጥኖ ደርሶ የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ሲያነብ ሰማው፤ ፊልጶስም፥ “በውኑ የምታነበውን ታውቀዋለህን?” አለው። 31ጃንደረባውም፥ “ያስተማረኝ ሳይኖር በምን አውቀዋለሁ?” አለው፤ ወደ ሰረገላውም ወጥቶ አብሮት ይቀመጥ ዘንድ ፊልጶስን ለመነው። 32ያነበው የነበረ የመጽሐፉ ቃልም እንዲህ የሚል ነበር፤ “እንደ በግ ወደ መታረድ ተነዳ፤ የበግ ጠቦትም በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንዲሁ አፉን አልከፈተም። 33#ኢሳ. 53፥7-8። በውርደቱ ፍርዱ ተወገደ፤ ሕይወቱ ከምድር ተወግዶአልና ትውልዱን ማን ይናገራል?” 34ጃንደረባውም ለፊልጶስ መልሶ፥ “ነቢዩ ስለ ማን እንዲህ ይላል? ስለ ራሱ ነውን? ወይስ ስለ ሌላ? እባክህ ንገረኝ” አለው። 35ፊልጶስም አፉን ከፈተ፤ ስለ ኢየሱስም ከዚያው መጽሐፍ ጀምሮ አስተማረው። 36በመንገድ ሲሄዱም ወደ ውኃ ደረሱ፤ ጃንደረባውም፥ “እነሆ፥ ውኃ፥ መጠመቅን ምን ይከለክለኛል?” አለው። 37ፊልጶስም፥ “በፍጹም ልብህ ብታምን ይገባሃል” አለው፤ ጃንደረባውም መልሶ፥ “ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ እኔ አምናለሁ” አለው። 38ሰረገላውንም እንዲያቆሙ አዘዘ፤ አቁመውም ፊልጶስና ጃንደረባው በአንድነት ወደ ውኃው ወረዱ፤ አጠመቀውም። 39ከውኃዉም ከወጡ በኋላ የእግዚአብሔር መንፈስ ፊልጶስን ነጥቆ ወሰደው፤ ጃንደረባዉም ከዚያ ወዲያ አላየውም፤ ደስ እያለውም መንገዱን ሄደ። 40ፊልጶስም አዛጦን ወደምትባል ሀገር ደረሰ፤ በከተማዎችም ሁሉ እየተዘዋወረ ወደ ቂሳርያ እስኪደርስ ድረስ ያስተምር ነበር።
Currently Selected:
የሐዋርያት ሥራ 8: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ