ወደ ቈላ​ስ​ይስ ሰዎች 4:1-6

ወደ ቈላ​ስ​ይስ ሰዎች 4:1-6 አማ2000

ጌቶች ሆይ፥ ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ቻ​ችሁ ትክ​ክ​ለ​ኛ​ውን አድ​ር​ጉ​ላ​ቸው፤ እው​ነ​ት​ንም ፍረዱ፤ በሰ​ማይ ጌታ እን​ዳ​ላ​ችሁ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁና። በም​ስ​ጋና እየ​ተ​ጋ​ችሁ ለጸ​ሎት ፅሙ​ዳን ሁኑ። ስለ እርሱ የታ​ሰ​ር​ሁ​ለ​ትን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምሥ​ጢር እን​ድ​ን​ና​ገር፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቃ​ሉን በር ይከ​ፍ​ት​ልን ዘንድ ለእ​ኛም ደግሞ ጸል​ዩ​ልን፤ ለም​ኑ​ል​ንም፤ ልና​ገ​ርም እን​ደ​ሚ​ገ​ባኝ እገ​ል​ጠው ዘንድ ጸል​ዩ​ልኝ። ዘመ​ኑን እየ​ዋ​ጃ​ችሁ ከሃ​ይ​ማ​ኖት ወደ ተለዩ ሰዎች በማ​ስ​ተ​ዋል ሂዱ። ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ እን​ዴት እን​ደ​ም​ት​መ​ልሱ ታውቁ ዘንድ ንግ​ግ​ራ​ችሁ ሁል​ጊዜ በጨው እንደ ተቀ​መመ በጸጋ ይሁን።