ትንቢተ ዳንኤል 2
2
የናቡከደነፆር ሕልም
1ናቡከደነፆርም በነገሠ በሁለተኛው ዓመት ሕልም አለመ፤ መንፈሱም ታወከ፤ ሕልሙንም ዘነጋው።#ግሪክ ሰባ. ሊ. እና ዕብ. “ዕንቅልፍ ከእርሱ ራቀ” ይላል። 2ንጉሡም ሕልሙን እንዲነግሩት የሕልም ተርጓሚዎቹንና አስማተኞቹን፥ መተተኞቹንና ከለዳውያኑንም ይጠሩ ዘንድ አዘዘ፤ እነርሱም ገብተው በንጉሡ ፊት ቆሙ። 3ንጉሡም፥ “ሕልም አልሜአለሁ፤ መንፈሴም ታወከብኝ፤ ሕልሜንም ዘነጋሁት” አላቸው። 4ከለዳውያኑም ንጉሡን በሱርስት ቋንቋ፥ “ንጉሥ ሆይ! ለዘለዓለም ኑር፤ ለአገልጋዮችህ ሕልምህን ንገር፤ እኛም ፍቺውን እንነግርሃለን” ብለው ተናገሩት። 5ንጉሡም መለሰ፤ ከለዳውያኑንም፥ “ነገሩ ከእኔ ዘንድ ርቆአል፤ ሕልሙንና ፍቺውን ባታስታውቁኝ፥ ትገደላላችሁ፤ ቤቶቻችሁም የጉድፍ መጣያ ይደረጋሉ። 6ሕልሙንና ፍቺውን ግን ብትነግሩኝ፥ ከእኔ ዘንድ ስጦታና ዋጋ፥ ብዙ ክብርም ትቀበላላችሁ፤ ስለዚህም ሕልሙንና ፍቺውን ንገሩኝ” አላቸው። 7ሁለተኛም ጊዜ መልሰው፥ “ንጉሡ ለአገልጋዮቹ ሕልሙን ይንገር፥ እኛም ፍቺውን እንናገራለን” አሉት። 8ንጉሡም መልሶ፥ “ነገሩ ከእኔ ዘንድ እንደ ራቀ ታውቃላችሁና ጊዜውን እንደምታስረዝሙ እኔ አውቃለሁ። 9ሕልሙንም አሁን ባትነግሩኝ አንድ ፍርድ አለባችሁ፥#“አንድ ፍርድ አለባችሁ” የሚለው በዕብ. ብቻ። ጊዜውን ለማሳለፍ የሐሰትንና የተንኰልን ቃል#“የተንኰልን ቃል” የሚለው በዕብ. ብቻ። ልትነግሩኝ አዘጋጅታችኋል፤ ስለዚህ ሕልሙን ንገሩኝ፤ ፍቺውንም መናገር እንደምትችሉ አውቃለሁ።” 10ከለዳውያኑም በንጉሡ ፊት መልሰው፥ “የንጉሡን ነገር ያሳይ ዘንድ የሚችል ሰው በምድር ላይ የለም፤ ታላቅ ንጉሥና አለቃ የሆነ እንደዚያ ያለ ነገር የሕልም ተርጓሚንና አስማተኛን፥ ከለዳዊንም የሚጠይቅ የለም። 11ንጉሡም የሚጠይቀው ነገር ከባድ ነው፤ መኖሪያቸው ከሥጋ ለባሽ ጋር ካልሆነ ከአማልክት በቀር በንጉሡ ፊት የሚያሳየው ማንም የለም” አሉ። 12ያንጊዜ ንጉሡ ፈጽሞ ተቈጣ፤ የባቢሎንንም ጠቢባን ሁሉ ያጠፉ ዘንድ አዘዘ። 13ከንጉሡም ዘንድ ትእዛዝ ወጣ፤ ጠቢባንንም ይገድሉ ዘንድ ጀመሩ፤ ዳንኤልንና ባልንጀሮቹንም ይገድሉአቸው ዘንድ ፈለጉአቸው።
14የዚያን ጊዜም ዳንኤል የባቢሎንን ጠቢባን ይገድል ዘንድ የወጣውን የንጉሡን የዘብ አለቃ አርዮክን በፈሊጥና በማስተዋል#“በማስተዋል” የሚለው በግእዝ የለም። ተናገረው፤ 15የንጉሡ የዘብ አለቃ አርዮክን፥ “ይህ ጭንቅ ትእዛዝ ከንጉሡ ዘንድ ስለ ምን ወጣ?” ብሎ ጠየቀው፤ አርዮክም ነገሩን ለዳንኤል ነገረው። 16ዳንኤልም ገብቶ ፍቺውን ለንጉሡ የሚያስታውቅበት#ግእዝ “እስከ ሦስት ቀን” የሚል ይጨምራል። ጊዜ ይሰጠው ዘንድ ንጉሡን ለመነ።
17የዚያን ጊዜም ዳንኤል ወደ ቤቱ ገባ። ነገሩንም ለባልንጀሮቹ ለአናንያና ለሚሳኤል፥ ለአዛርያም አስታወቃቸው። 18ዳንኤልና ባልንጀሮቹም ከቀሩት ከባቢሎን ጠቢባን ጋር እንዳይሞቱ ስለዚህ ምሥጢር ምሕረትን ከሰማይ አምላክ ለመኑ።
19የዚያን ጊዜም ምሥጢሩ በሌሊት ራእይ ለዳንኤል ተገለጠለት። ዳንኤልም የሰማይ አምላክን አመሰገነ። 20እንዲህም አለ፥ “ጥበብና ምክር፥ ኀይልም ለእርሱ ነውና የእግዚአብሔር ስም ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይመስገን። 21እሱም ጊዜያትንና ዘመናትን ይለውጣል፤ ነገሥታትን ያስነሣል፤ ነገሥታትንም ይሽራል፤ ጥበብን ለጠቢባን፥ ዕውቀትንም ለአስተዋዮች ይሰጣል። 22የጠለቀውንና የተሰወረውን ይገልጣል፤ በጨለማ ያለውን ያውቃል፤ ብርሃንም ከእርሱ ጋር አለ። 23አንተ የአባቶቻችን ፈጣሪ! እውቀትንና ጥበብን#ግሪክ ሰባ. ሊ. እና ዕብ. “ጥበብና ኀይል” ይላል። ሰጥተኸኛልና፥ የለመንሁህንም ነግረኸኛልና፥ የንጉሡን ሕልም፥ ትርጓሜውንም ገልጠህልኛልና እገዛልሃለሁ፤ አመሰግንህምአለሁ።”
ዳንኤል ሕልሙን ከነትርጕሙ ለንጉሡ እንደ ነገረ
24ከዚህም በኋላ ዳንኤል ንጉሡ የባቢሎንን ጠቢባን ያጠፋ ዘንድ ወደ አዘዘው ወደ አርዮክ ገባ፤ “የባቢሎንን ጠቢባን አታጥፋቸው፤ ወደ ንጉሡ አስገባኝ፥ እኔም ሕልሙንና ፍቺውን ለንጉሡ እነግረዋለሁ” አለው 25የዚያን ጊዜም አርዮክ ዳንኤልን ፈጥኖ ወደ ንጉሡ አስገባውና፥ “ከይሁዳ የምርኮ ልጆች ለንጉሡ ሕልሙንና ፍቺውን የሚነግረውን ሰው አግኝቼአለሁ” አለው። 26ንጉሡም መለሰ፤ ብልጣሶርም የሚባለውን ዳንኤልን፥ “ያየሁትን ሕልምና ፍቺውንም ትነግረኝ ዘንድ ትችላለህን?” አለው። 27ዳንኤልም በንጉሡ ፊት እንዲህ ሲል መለሰ፥ “ንጉሥ የሚጠይቀው ይህ ምሥጢር ለአዋቂዎችና ለፈላስፎች፥ ለሟርተኞችና ለጠንቋዮች የሚገለጥ አይደለም።” 28ነገር ግን ምሥጢርን የሚገልጥ አምላክ በሰማይ ውስጥ አለ፤ እርሱም በኋለኛው ዘመን የሚሆነውን ለንጉሡ ለናቡከደነፆር አሳይቶታል። በአልጋህ ላይ የሆነው ሕልምና የራስህ ራእይ ይህ ነው። 29ንጉሥ ሆይ! ከአንተ በኋላ የሚሆነው ምን እንደ ሆነ በአልጋህ ላይ ታስብ ነበር፤ ምሥጢርንም የሚገልጠው የሚሆነውን ነገር አሳይቶሃል። 30ነገር ግን ይህ ምሥጢር ለእኔ መገለጡ ፍቺው ለንጉሡ ይታወቅ ዘንድ፥ አንተም የልብህን አሳብ ታውቅ ዘንድ ነው እንጂ በዚህ ዓለም ከአሉ ሰዎች ይልቅ በጥበብ ስለ በለጥሁ አይደለም።
31“ንጉሥ ሆይ! አንተ አየህ፤ እነሆ ይኸውም አንድ ታላቅ ምስል ነበር፤ እርሱም በፊትህ ቆሞ ነበር፤ መልኩም ግሩም ነበር። 32የዚህም ምስል ራስ ጥሩ ወርቅ፥ እጆቹ፥ ደረቱና ክንዶቹም ብር፥ ሆዱና ወገቡም ናስ፤ 33ጭኖቹም ብረት፥ እግሮቹም እኩሉ ብረት እኩሉም ሸክላ ነበረ። 34እጅም ሳይነካው ታላቅ ድንጋይ ከተራራው ተፈንቅሎ ከብረትና ከሸክላ የሆነውን የምስሉን እግሮች እስከ መጨረሻው ሲመታና ሲፈጭ አየህ። 35የዚያን ጊዜም ብረቱና ሸክላው፥ ናሱና ብሩ፥ ወርቁም በአንድነት ተፈጨ፤ በመከርም ጊዜ በአውድማ ላይ እንደአለ እብቅ ሆነ፤ ነፋስም ወሰደው፤ ቦታውም አልታወቀም፤ ምስሉንም የመታው ድንጋይ ታላቅ ተራራ ሆነ፤ ምድርንም ሁሉ ሞላ።
36“ሕልምህ ይህ ነው፤ ፍቺውንም በንጉሡ ፊት እናገራለሁ። 37ንጉሥ ሆይ! የሰማይ አምላክ ጠንካራ መንግሥትን፥ ኀይልንና ክብርን የሰጠህ የነገሥታት ንጉሥ አንተ ነህ። 38የሰው ልጆች በሚኖሩበት ስፍራ ሁሉ የምድር አራዊትን፥ የሰማይ ወፎችን፥ የባሕር ዓሣዎችንም በእጅህ ሰጥቶሃል፤ ለሁሉም ገዢ አድርጎ ሹሞሃል፤ የወርቁ ራስ አንተ ነህ። 39ከአንተም በኋላ ከአንተ የሚያንስ ሌላ መንግሥት ይነሣል፤ እርሱም የብሩ ነው። ከዚያም በኋላ በምድር ሁሉ ላይ የሚገዛ ሌላ ሦስተኛ መንግሥት ይነሣል፤ እርሱም የናሱ ነው። 40አራተኛውም መንግሥት ሁሉን እንደሚቀጠቅጥና እንደሚያደቅቅ ብረት ይበረታል፤ እነዚህንም ሁሉ እንደሚፈጭ ብረት ይቀጠቅጣል፤ ይፈጭማል። 41እግሮቹና ጣቶቹም እኩሉ ሸክላ፥ እኩሉም ብረት ሆኖ እንደአየህ፥ እንዲሁ የተከፋፈለ መንግሥት ይሆናል፤ ብረቱም ከሸክላው ጋር ተደባልቆ እንደ አየኸው፥ የብረት ብርታት ለእርሱ ይሆናል። 42የእግሮቹም ጣቶች እኩሉ ብረት፥ እኩሉም ሸክላ እንደ ነበሩ፥ እንዲሁ መንግሥቱ እኩሉ ብርቱ፥ እኩሉ ደካማ ይሆናል። 43ብረቱም ከሸክላው ጋር ተደባልቆ እንዳየህ፥ እንዲሁ ከሰው ዘር ጋር ይደባለቃሉ፤ ነገር ግን ብረት ከሸክላ ጋር እንደማይጣበቅ እንዲሁ እርስ በርሳቸው አይጣበቁም 44በእነዚያም ነገሥታት ዘመን የሰማይ አምላክ ለዘለዓለም የማይፈርስ መንግሥት ያስነሣል፤ ለሌላ ሕዝብም የማይሰጥ መንግሥት ይሆናል፤ እነዚያንም መንግሥታት ሁሉ ድል ታደርጋቸዋለች፤ ታጠፋቸውማለች፤ ለዘለዓለምም ትቆማለች። 45ድንጋዩም እጅ ሳይነካው ከተራራ ተፈንቅሎ ብረቱንና ናሱን፥ ሸክላውንና ብሩን፥ ወርቁንም ሲፈጨው እንደ አየህ፥ እንዲሁ ከዚህ በኋላ የሚሆነውን ታላቁ አምላክ ለንጉሡ አሳይቶታል፤ ሕልሙም እውነተኛ፥ ፍቺውም የታመነ ነው።”
ንጉሡ፥ ዳንኤልን እንደ አከበረው
46የዚያን ጊዜም ንጉሡ ናቡከደነፆር በግምባሩ ተደፍቶ ለዳንኤል ሰገደለት። ፈጽሞም አከበረው፥#“ፈጽሞም አከበረው” የሚለው በግእዝ ብቻ። ገጸ በረከትም ሰጠው፤ መልካም መዓዛም#ዕብ. “የእህሉን ቍርባንና ዕጣኑን ...” ይላል። ያቀርቡለት ዘንድ አዘዘ። 47ንጉሡም ዳንኤልን፥ “ይህን ምሥጢር ትገልጥ ዘንድ ተችሎሃልና በእውነት አምላካችሁ የአማልክት አምላክ፥ የነገሥታትም ጌታ፥ ምሥጢርም ገላጭ ነው” ብሎ ተናገረው። 48ንጉሡም ዳንኤልን ከፍ ከፍ አደረገው፤ ብዙም ታላቅ ስጦታ ሰጠው፤ በባቢሎንም አውራጃዎች ሁሉ ላይ ሾመው፤ በባቢሎንም ጠቢባን ሁሉ ላይ ዋነኛ አለቃ አደረገው። 49ዳንኤልም ንጉሡን ለመነ፤ እርሱም ሲድራቅንና ሚሳቅን፥ አብደናጎንም በባቢሎን አውራጃ ሥራ ላይ ሾማቸው፤ ዳንኤል ግን በንጉሡ አደባባይ ነበረ።
Currently Selected:
ትንቢተ ዳንኤል 2: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ