የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ዳን​ኤል 3

3
ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ያቆ​መው የወ​ርቅ ምስል
1ንጉሡ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በነ​ገሠ በዐ​ሥራ ስም​ን​ተ​ኛው ዓመት#“በነ​ገሠ በዐ​ሥራ ስም​ን​ተ​ኛው ዓመት” የሚ​ለው በዕብ. የለም። ቁመቱ ስድሳ ክንድ፥ ወር​ዱም ስድ​ስት ክንድ የሆነ የወ​ርቅ ምስል አሠራ፤ በባ​ቢ​ሎ​ንም አው​ራጃ በዱራ ሜዳ አቆ​መው። 2ንጉ​ሡም ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር መኳ​ን​ን​ት​ንና ሹሞ​ችን፥ አዛ​ዦ​ች​ንና አዛ​ው​ን​ቶ​ችን፥ በጅ​ሮ​ን​ዶ​ች​ንና አማ​ካ​ሪ​ዎ​ችን፥ መጋ​ቢ​ዎ​ች​ንም፥ አው​ራጃ ገዢ​ዎ​ች​ንም ሁሉ ይሰ​በ​ስቡ ዘንድ፥ ንጉሡ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርም ላቆ​መው ምስል ምረቃ ይመጡ ዘንድ ላከ። 3በዚ​ያን ጊዜም መኳ​ን​ን​ቱና ሹሞቹ፥ አዛ​ዦ​ቹና አዛ​ው​ን​ቶቹ፥ በጅ​ሮ​ን​ዶ​ቹና አማ​ካ​ሪ​ዎቹ፥ መጋ​ቢ​ዎ​ቹና አው​ራጃ ገዢ​ዎቹ ሁሉ ንጉሡ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ላቆ​መው ምስል ምረቃ ተሰ​በ​ሰቡ፤ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርም ባቆ​መው ምስል ፊት ቆሙ። 4አዋጅ ነጋ​ሪ​ውም እየ​ጮኸ እን​ዲህ አለ፥ “ሕዝ​ብና አሕ​ዛብ፥ በልዩ ልዩ ቋን​ቋም የም​ት​ና​ገሩ ሆይ! ንጉሥ ይላ​ች​ኋል፥ 5የመ​ለ​ከ​ት​ንና የእ​ን​ቢ​ል​ታን፥ የመ​ሰ​ን​ቆ​ንና የክ​ራ​ርን፥ የበ​ገ​ና​ንና የዋ​ሽ​ን​ትን፥ የዘ​ፈ​ን​ንም ሁሉ ድምፅ በሰ​ማ​ችሁ ጊዜ ወድ​ቃ​ችሁ ንጉሡ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ላቆ​መው ለወ​ርቁ ምስል ስገዱ፤ 6ወድ​ቆም የማ​ይ​ሰ​ግድ በዚ​ያን ጊዜ በሚ​ነ​ድድ እሳት እቶን ውስጥ ይጣ​ላል።” 7ስለ​ዚህ በዚ​ያን ጊዜ አሕ​ዛብ ሁሉ የመ​ለ​ከ​ቱ​ንና የእ​ን​ቢ​ል​ታ​ውን፥ የመ​ሰ​ን​ቆ​ው​ንና የክ​ራ​ሩን፥ የበ​ገ​ና​ው​ንና የዘ​ፈ​ኑ​ንም ሁሉ ድምፅ በሰሙ ጊዜ፥ ወገ​ኖ​ችና አሕ​ዛብ፥ በልዩ ልዩ ቋን​ቋም የሚ​ና​ገሩ ሁሉ ወድ​ቀው፤ ንጉሡ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ላቆ​መው ለወ​ርቅ ምስል ሰገዱ።
ሠለ​ስቱ ደቂቅ
8በዚ​ያን ጊዜ ከለ​ዳ​ው​ያን ቀር​በው አይ​ሁ​ድን በን​ጉሡ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ዘንድ ከሰሱ። 9እን​ዲ​ህም አሉት፦“ንጉሥ ሆይ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ኑር! 10ንጉሥ ሆይ! የመ​ለ​ከ​ት​ንና የእ​ን​ቢ​ል​ታን፥ የመ​ሰ​ን​ቆ​ንና የክ​ራ​ርን፥ የበ​ገ​ና​ንና የዋ​ሽ​ን​ትን፥ የዘ​ፈ​ን​ንም ሁሉ ድምፅ የሚ​ሰማ ሰው ሁሉ ወድቆ ለወ​ርቁ ምስል ይስ​ገድ፥#“ወድ​ቆም ለወ​ርቁ ምስል ይስ​ገድ” የሚ​ለው በዕብ. ብቻ። 11ወድ​ቆም የማ​ይ​ሰ​ግድ በሚ​ነ​ድድ እሳት እቶን ውስጥ ይጣ​ላል ብለህ በቃ​ልህ አዘህ ነበር። 12አሁ​ንም ንጉሥ በባ​ቢ​ሎን ሀገ​ሮች ለሚ​ሠራ ሥራ የሾ​ም​ኻ​ቸው፥ ከአ​ይ​ሁድ ወገን የሚ​ሆኑ ትእ​ዛ​ዝ​ህን እምቢ ያሉ፥ አም​ላ​ክ​ህን ያላ​መ​ለኩ፥ ለሠ​ራ​ኸ​ውም ለወ​ርቁ ምስል ያል​ሰ​ገዱ ሚሳ​ቅና ሲድ​ራቅ፥ አብ​ደ​ና​ጎም የሚ​ባሉ ሦስት ሰዎች አሉ።”
13ያን​ጊ​ዜም ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ተቈጣ፤ በቍ​ጣም ሲድ​ራ​ቅ​ንና ሚሳ​ቅን፥ አብ​ደ​ና​ጎ​ንም ያመጡ ዘንድ አዘዘ፤ እነ​ዚ​ህ​ንም ሰዎች ወደ ንጉሡ ፊት አመ​ጡ​አ​ቸው። 14ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርም፥ “ሲድ​ራ​ቅና ሚሳቅ አብ​ደ​ና​ጎም ሆይ፥ አም​ላ​ኬን አለ​ማ​ም​ለ​ካ​ችሁ፥ ላቆ​ም​ሁ​ትም ለወ​ርቁ ምስል አለ​መ​ስ​ገ​ዳ​ችሁ እው​ነት ነውን? 15አሁ​ንም የመ​ለ​ከ​ቱ​ንና የእ​ን​ቢ​ል​ታ​ውን፥ የመ​ሰ​ን​ቆ​ው​ንና የክ​ራ​ሩን፥ የበ​ገ​ና​ው​ንና የዋ​ሽ​ን​ቱን የዘ​ፈ​ኑ​ንም ሁሉ ድምፅ በሰ​ማ​ችሁ ጊዜ ወድ​ቃ​ችሁ ላሠ​ራ​ሁት ምስል ብት​ሰ​ግዱ መል​ካም ነው፤ ባት​ሰ​ግዱ ግን በዚያ ጊዜ በሚ​ነ​ድድ እሳት እቶን ውስጥ ትጣ​ላ​ላ​ችሁ፤ ከእ​ጄስ የሚ​ያ​ድ​ና​ችሁ አም​ላክ ማን ነው?” ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው። 16ሲድ​ራ​ቅና ሚሳቅ፥ አብ​ደ​ና​ጎም መለሱ፤ ንጉ​ሡ​ንም፥ “ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ሆይ! በዚህ ነገር እን​መ​ል​ስ​ልህ ዘንድ አን​ፈ​ል​ግም። 17ንጉሥ ሆይ! እኛ የም​ና​መ​ል​ከው አም​ላክ በሰ​ማይ አለ፥#“በሰ​ማይ አለ” የሚ​ለው በዕብ. የለም። ከሚ​ነ​ድ​ደው ከእ​ሳቱ እቶን ያድ​ነን ዘንድ ይች​ላል፤ ከእ​ጅ​ህም ያድ​ነ​ናል፤ 18ንጉሥ ሆይ! ይህም ባይ​ሆን፥ አማ​ል​ክ​ት​ህን እን​ዳ​ና​መ​ልክ፥ ላቆ​ም​ኸ​ውም ለወ​ርቁ ምስል እን​ዳ​ን​ሰ​ግ​ድ​ለት ዕወቅ” አሉት።
19የዚ​ያን ጊዜም ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በሲ​ድ​ራ​ቅና በሚ​ሳቅ፥ በአ​ብ​ደ​ና​ጎም ላይ ቍጣ ሞላ​በት፤ የፊ​ቱም መልክ ተለ​ወ​ጠ​ባ​ቸው፤ እር​ሱም ተና​ገረ፤ የእ​ቶ​ንም እሳት ይነ​ድድ ከነ​በ​ረው ይልቅ ሰባት እጥፍ አድ​ር​ገው እን​ዲ​ያ​ነ​ድ​ዱት አዘዘ። 20ሲድ​ራ​ቅ​ንና ሚሳ​ቅን፥ አብ​ደ​ና​ጎ​ንም አስ​ረው፥ ወደ​ሚ​ነ​ድድ ወደ እቶን እሳት ይጥ​ሉ​አ​ቸው ዘንድ ኃያ​ላን ሰዎ​ችን አዘዘ። 21የዚ​ያን ጊዜም እነ​ዚያ ሰዎች ከሰ​ና​ፊ​ላ​ቸ​ውና ከጫ​ማ​ቸው፥ ከቀ​ሚ​ሳ​ቸ​ውና ከመ​ጎ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ቸ​ውም፥ ከቀ​ረ​ውም ልብ​ሳ​ቸው ጋር አስ​ረው በሚ​ነ​ድድ በእ​ቶን እሳት ውስጥ ጣሉ​አ​ቸው። 22የን​ጉ​ሡም ትእ​ዛዝ እጅግ ስለ በረታ፥ የእ​ቶ​ኑም እሳት እጅግ ስለ​ሚ​ነ​ድድ፥ ሲድ​ራ​ቅ​ንና ሚሳ​ቅን፥ አብ​ደ​ና​ጎ​ንም የጣ​ሉ​አ​ቸ​ውን ሰዎች የእ​ሳቱ ወላ​ፈን ገደ​ላ​ቸው።#“ሲድ​ራ​ቅ​ንና ሚሳ​ቅን አብ​ድ​ና​ጎ​ንም የጣ​ሉ​አ​ቸ​ውን ሰዎች የእ​ሳቱ ወላ​ፈን ገደ​ላ​ቸው” የሚ​ለው በዕብ. ብቻ። 23እነ​ዚ​ህም ሦስቱ ሰዎች ሲድ​ራ​ቅና ሚሳቅ፥ አብ​ደ​ና​ጎም ታስ​ረው በሚ​ነ​ድ​ደው በእ​ቶኑ እሳት መካ​ከል ወደቁ።
ጸሎተ ሠለ​ስቱ ደቂቅ
24 በእ​ሳት መካ​ከ​ልም ተመ​ላ​ለሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ፈጽ​መው አመ​ሰ​ገ​ኑት።
25 አዛ​ር​ያም ቁሞ እን​ዲህ ብሎ ጸለየ፥ በእ​ሳ​ቱም መካ​ከል ምስ​ጋ​ናን ጀመረ፦
26 “የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይክ​በር፤
ስም​ህም ለዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​መ​ሰ​ገ​ነና የከ​በረ ነው።
27 ባመ​ጣ​ህ​ብን ነገር ሁሉ አንተ ጻድቅ ነህና፤ ሥራህ ሁሉ የታ​መነ ነው፤ ሥር​ዐ​ት​ህም ሁሉ የቀና ነው፤
ፍር​ድ​ህም ሁሉ እው​ነት ነው።
28 ባደ​ረ​ግ​ህ​ብን ነገር ሁሉ ፍትሕ ርትዕ አደ​ረ​ግህ፤
በእ​ው​ነ​ተኛ ፍር​ድህ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችን ይህን ሁሉ መከራ አም​ጥ​ተ​ህ​ብ​ና​ልና
በከ​በ​ረች በአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ሀገር በቅ​ድ​ስት ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም
በእ​ው​ነ​ተኛ ፍር​ድህ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችን ይህን ሁሉ መከራ አም​ጥ​ተ​ህ​ብ​ና​ልና።
29 የተ​ው​ንህ እኛ በድ​ለ​ናል፤ ስተ​ና​ልና
በሁሉ በደ​ልን፤
30 መል​ካም ይሆ​ን​ልን ዘንድ፥
እን​ዳ​ዘ​ዝ​ኸን ሕግ​ህን አል​ጠ​በ​ቅ​ንም፤ ትእ​ዛ​ዝ​ህ​ንም አላ​ደ​ረ​ግ​ንም።
31 ያመ​ጣ​ህ​ብ​ን​ንና ያደ​ረ​ግ​ህ​ብ​ንን ሁሉ በእ​ው​ነ​ተኛ ፍር​ድህ አደ​ረ​ግ​ህ​ብን።
32 ከአ​ንተ ፈጽ​መው በራቁ ኀጢ​አ​ተ​ኞ​ችና ወን​ጀ​ለ​ኞች በሚ​ሆኑ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችን እጅ ጣል​ኸን፤
ከሰው ሁሉ ዐመ​ፀ​ኛና ክፉ በሆነ ንጉ​ሥም እጅ አሳ​ል​ፈህ ጣል​ኸን።#“ከሰው ሁሉ ዐመ​ፀ​ኛና ክፉ በሆነ ንጉ​ሥም እጅ አሳ​ል​ፈህ ጣል​ኸን” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም።
33 አሁ​ንም አፋ​ች​ንን እን​ከ​ፍት ዘንድ አገ​ባ​ባ​ችን አይ​ደ​ለም
ለሚ​ፈ​ሩህ ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ኀፍ​ረ​ትና ማሽ​ሟ​ጠጫ ሆነ​ባ​ቸው።
34 ስለ ስምህ ብለህ ፈጽ​መህ አሳ​ል​ፈህ አት​ስ​ጠን።
ቃል ኪዳ​ን​ህ​ንም አት​ለ​ው​ጥ​ብን፤
35 ይቅ​ር​ታ​ህ​ንም አታ​ር​ቅ​ብን።
ስለ ወዳ​ጅህ ስለ አብ​ር​ሃም፥
ስለ ባለ​ም​ዋ​ልህ ስለ ይስ​ሐቅ፤
ስለ ቅዱ​ስህ ስለ እስ​ራ​ኤል።
36 ዘራ​ቸ​ውን እንደ ሰማይ ኮከብ፥
በባ​ሕር ዳር እንደ አለ አሸ​ዋም ታበ​ዛ​ላ​ቸው ዘንድ ስለ ሰጠ​ሃ​ቸው ስለ እነ​ዚህ፥
እነ​ርሱ ከሕ​ዛብ ሁሉ ጥቂ​ቶች ነበ​ሩና።
37 ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችን በሀ​ገሩ ሁሉ ዛሬ የተ​ዋ​ረ​ድን ሆን።
38 በዚህ ወራት አለቃ የለም፤ ነቢ​ይም የለም፤ ንጉ​ሥም የለም፤
ቍር​ባ​ንም፥ መሥ​ዋ​ዕ​ትም፥ ዕጣ​ንም የሚ​ያ​ጥ​ኑ​በት የለም፤
ይቅ​ር​ታ​ህን ያገኙ ዘንድ በፊ​ትህ ፍሬ የሚ​ያ​ፈ​ሩ​በት ሀገ​ርም የለም።
39 በየ​ዋህ ልቡና በቀና መን​ፈስ ተቀ​በ​ል​ልን እንጂ፤
40 እንደ ጊደ​ሮ​ችና ላሞች፥
እንደ ሰቡ ብዙ በጎ​ችም መሥ​ዋ​ዕት፤
መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ችን ዛሬ በፊ​ትህ እን​ደ​ዚያ ይሁን።
በአ​ን​ተም ዘንድ ፍጹም ይሁን፤
ያመ​ኑ​ብህ ሁሉ እን​ዳ​ያ​ፍሩ።
41 አሁ​ንም በፍ​ጹም ልቡ​ና​ችን እን​ከ​ተ​ል​ሃ​ለን፤ እን​ፈ​ራ​ሃ​ለ​ንም፤
ፊት​ህ​ንም እን​ፈ​ል​ጋ​ለን።
42 አታ​ሳ​ፍ​ረን፤ ነገር ግን እንደ ቸር​ነ​ት​ህና እንደ ይቅ​ር​ታህ ብዛት አድ​ር​ግ​ልን፥
43 በተ​አ​ም​ራ​ት​ህም አድ​ነን፤
አቤቱ፥ ለስ​ምህ ምስ​ጋ​ናን ስጥ።
44 አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህን ስቃይ ያሳ​ዩ​አ​ቸው ሁሉ ይፈሩ፤ በቅ​ሚ​አ​ቸ​ውም ሁሉ ይፈሩ፤ ኀይ​ላ​ቸ​ውም ይድ​ከም፤
45 አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብቻህ አም​ላክ፥
በዓ​ለሙ ሁሉና በሀ​ገ​ሩም ሁሉ የተ​መ​ሰ​ገ​ንህ እንደ ሆንህ ይወቁ።
46 እነ​ዚ​ያም ብላ​ቴ​ና​ዎች በን​ጉሥ ዘንድ ነገር ሠር​ተው ማጣ​ላ​ታ​ቸ​ውን አል​ተ​ዉም፤ በእ​ሳ​ቱም ድኝ አደ​ሮ​ማር፥ ቁል​ቋል፥ ቅን​ጭብ ጨመሩ።
47 ነበ​ል​ባ​ሉም ከጕ​ድ​ጓዱ አርባ ዘጠኝ ክንድ ከፍ ከፍ አለ።
48 እሳ​ቱም እየ​ተ​መ​ላ​ለሰ በከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድጃ ጕድ​ጓድ አጠ​ገብ ያገ​ኘ​ውን ሁሉ ያቃ​ጥል ነበር።
49 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ከአ​ና​ን​ያና ከአ​ዛ​ርያ ከሚ​ሳ​ኤ​ልም ጋር ወደ​ሚ​ነ​ደው ወደ እሳቱ ምድጃ ወርዶ ከም​ድጃ ያለ​ውን እሳት መታው፤
50 የእ​ሳ​ቱ​ንም ነበ​ል​ባል እንደ ቀዝ​ቃዛ ነፋስ አደ​ረ​ገው፤ እነ​ዚ​ያ​ንም ሰዎች እሳቱ ምንም አል​ነ​ካ​ቸ​ውም፤ የራ​ሳ​ቸ​ው​ንም ጠጕር አል​ለ​በ​ለ​ባ​ቸ​ውም፤ አላ​ስ​ጨ​ነ​ቃ​ቸ​ው​ምም።
51 ያን​ጊ​ዜም እነ​ዚያ ሦስቱ ሰዎች ሁሉ በአ​ንድ አፍ ፈጽ​መው አመ​ሰ​ገኑ፤ በእ​ሳቱ ጕድ​ጓድ ውስ​ጥም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገ​ኑት፤ እን​ዲ​ህም አሉ፦
52 የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይክ​በር ይመ​ስ​ገን፤
እርሱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​መ​ሰ​ገነ ነው፤ ከፍ ከፍም ያለ ነው።
53 የጌ​ት​ነቱ ቅዱስ ስምም ይክ​በር ይመ​ስ​ገን፤
እርሱ የተ​መ​ሰ​ገነ ነው፤ በዓ​ለ​ሙም ሁሉ ከፍ ከፍ ያለ ነው።
54 በም​ት​መ​ሰ​ገ​ን​በት ቅዱስ ቦታ አንተ የከ​በ​ርህ ነህ፤
አንተ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​መ​ሰ​ገ​ን​ህና የከ​በ​ርህ ነህ።
55 በኪ​ሩ​ቤል ላይ ሆነህ ጥል​ቆ​ችን የም​ታይ አንተ የከ​በ​ርህ ነህ፤
አንተ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​መ​ሰ​ገ​ንህ ነህ፤ ከፍ ከፍም ያልህ ነህ።
56 በጌ​ት​ነ​ት​ህም ዙፋን አንተ የከ​በ​ርህ ነህ፤
አንተ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​መ​ሰ​ገ​ንህ ነህ፤ የከ​በ​ር​ህም ነህ።
57 ከሰ​ማ​ዮች በላይ የተ​መ​ሰ​ገ​ንህ ነህ፤
አንተ ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ ፈጽ​መህ የከ​በ​ርህ ነህ።
58 የጌታ ፍጥ​ረ​ቶች ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤
እርሱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​መ​ሰ​ገነ ነው፤ ከፍ ከፍ ያለም ነው።
59 ሰማ​ዮች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤
እርሱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​መ​ሰ​ገነ ነው፥ ከፍ ከፍ ያለም ነው።
60 የጌታ መላ​እ​ክት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤
እርሱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​መ​ሰ​ገነ ነው፤ ከፍ ከፍ ያለም ነው።
61 ከሰ​ማ​ዮች በላይ ያሉ ውኃ​ዎች ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤
እርሱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​መ​ሰ​ገነ ነው፤ ከፍ ከፍ ያለም ነው።
62 የጌታ ኀይ​ላት ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤
እርሱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​መ​ሰ​ገነ ነው፤ ከፍ ከፍ ያለም ነው።
63 ፀሐ​ይና ጨረቃ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤
እርሱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​መ​ሰ​ገነ ነው፤ ከፍ ከፍ ያለም ነው።
64 የሰ​ማይ ከዋ​ክ​ብት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤
እርሱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​መ​ሰ​ገነ ነው፤ ከፍ ከፍ ያለም ነው።
65 ጠልና ዝናም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤
እርሱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​መ​ሰ​ገነ ነው፤ ከፍ ከፍ ያለም ነው።
66 ነፋ​ሳት ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤
እርሱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​መ​ሰ​ገነ ነው፤ ከፍ ከፍ ያለም ነው።
67 እሳ​ትና ዋዕይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤
እርሱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​መ​ሰ​ገነ ነው፤ ከፍ ከፍ ያለም ነው።
68 መዓ​ል​ትና ሌሊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤
እርሱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​መ​ሰ​ገነ ነው፤ ከፍ ከፍ ያለም ነው።
69 ጠልና ጤዛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤
እርሱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​መ​ሰ​ገነ ነው፤ ከፍ ከፍ ያለም ነው።
70 ብር​ድና ውርጭ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤
እርሱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​መ​ሰ​ገነ ነው፤ ከፍ ከፍ ያለም ነው።
71 ብር​ሃ​ንና ጨለማ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤
እርሱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​መ​ሰ​ገነ ነው፤ ከፍ ከፍ ያለም ነው።
72 ደጋና ቈላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤
እርሱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​መ​ሰ​ገነ ነው፤ ከፍ ከፍ ያለም ነው።
73 በረ​ድና ጕም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤
እርሱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​መ​ሰ​ገነ ነው፤ ከፍ ከፍ ያለም ነው።
74 መብ​ረ​ቅና ደመና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤
እርሱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​መ​ሰ​ገነ ነው፤ ከፍ ከፍ ያለም ነው።
75 ምድር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለች፤
እርሱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​መ​ሰ​ገነ ነው፤ ከፍ ከፍ ያለም ነው።
76 ተራ​ሮ​ችና ኮረ​ብ​ቶች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤
እርሱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​መ​ሰ​ገነ ነው፤ ከፍ ከፍ ያለም ነው።
77 በም​ድር የሚ​በ​ቅሉ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤
እርሱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​መ​ሰ​ገነ ነው፤ ከፍ ከፍ ያለም ነው።
78 ጥል​ቆች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤
እርሱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​መ​ሰ​ገነ ነው፤ ከፍ ከፍ ያለም ነው።
79 ባሕ​ርና ፈሳ​ሾች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤
እርሱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​መ​ሰ​ገነ ነው፤ ከፍ ከፍ ያለም ነው።
80 አን​በ​ሪና በውኃ ውስጥ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀስ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤
እርሱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​መ​ሰ​ገነ ነው፤ ከፍ ከፍ ያለም ነው።
81 በሰ​ማይ የሚ​በ​ርሩ ወፎች ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤
እርሱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​መ​ሰ​ገነ ነው፤ ከፍ ከፍ ያለም ነው።
82 አራ​ዊ​ትና እን​ስ​ሳት ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤
እርሱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​መ​ሰ​ገነ ነው፤ ከፍ ከፍ ያለም ነው።
83 የሰው ልጆች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤
እርሱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​መ​ሰ​ገነ ነው፤ ከፍ ከፍ ያለም ነው።
84 እስ​ራ​ኤል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤
እርሱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​መ​ሰ​ገነ ነው፤ ከፍ ከፍ ያለም ነው።
85 የጌታ ካህ​ናት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤
እርሱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​መ​ሰ​ገነ ነው፤ ከፍ ከፍ ያለም ነው።
86 የጌታ ባሪ​ያ​ዎች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤
እርሱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​መ​ሰ​ገነ ነው፤ ከፍ ከፍ ያለም ነው።
87 መን​ፈ​ስና የጻ​ድ​ቃን ነፍ​ሳት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤
እርሱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​መ​ሰ​ገነ ነው፤ ከፍ ከፍ ያለም ነው።
‘65’ ጻድ​ቃ​ንና ልባ​ቸው ትሑት የሆኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤
እርሱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​መ​ሰ​ገነ ነው፤ ከፍ ከፍ ያለም ነው።
88 አና​ን​ያና አዛ​ርያ፥ ሚሳ​ኤ​ልም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤
እርሱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​መ​ሰ​ገነ ነው፤ ከፍ ከፍ ያለም ነው።
89 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሞ​ትና ከሲ​ኦል እጅ አድ​ኖ​ና​ልና፥ ከሚ​ነ​ድ​ድም ከም​ድ​ጃው እሳት አስ​ጥ​ሎ​ና​ልና፥ ከነ​በ​ል​ባ​ሉም መካ​ከል አው​ጥ​ቶ​ና​ልና፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተገዙ፤ ስሙ​ንም አመ​ስ​ግ​ኑት፤ ቸር ነውና ምሕ​ረ​ቱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና።
90 የአ​ማ​ል​ክ​ትን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ት​ፈሩ ሁላ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግ​ኑት፤ ተገ​ዙ​ለት፤ አመ​ስ​ግ​ኑ​ትም፤ ቸር​ነቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና።#ምዕ. 3 ከቍ. 23‘1’ እስከ ‘68’ ያለው በዕብ. የለም።
91 ንጉሡ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርም ሲያ​መ​ሰ​ግኑ ሰምቶ#“ሲያ​መ​ሰ​ግኑ ሰምቶ” የሚ​ለው በዕብ. የለም። ተደ​ነቀ፤ ፈጥ​ኖም ተነሣ፤ አማ​ካ​ሪ​ዎ​ቹ​ንም፥ “ሦስት ሰዎች አስ​ረን በእ​ሳት ውስጥ ጥለን አል​ነ​በ​ረ​ምን?” ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው። እነ​ር​ሱም፥ “ንጉሥ ሆይ! እው​ነት ነው” አሉት። 92 ንጉ​ሡም፥ “እኔ የተ​ፈቱ በእ​ሳ​ቱም መካ​ከል የሚ​መ​ላ​ለሱ አራት ሰዎ​ችን በዚያ አያ​ለሁ፤ ምንም የነ​ካ​ቸው የለም፤ የአ​ራ​ተ​ኛ​ውም መልክ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ልጅ ይመ​ስ​ላል” አለ። 93 የዚ​ያን ጊዜም ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ወደ​ሚ​ነ​ድ​ደው ወደ እሳቱ እቶን በር ቀርቦ፥ “እና​ንተ የል​ዑል አም​ላክ ባሪ​ያ​ዎች፥ ሲድ​ራ​ቅና ሚሳቅ፥ አብ​ደ​ና​ጎም፥ ኑ ውጡ” ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው። ሲድ​ራ​ቅና ሚሳቅ፥ አብ​ደ​ና​ጎም ከእ​ሳቱ መካ​ከል ወጡ። 94 አለ​ቆች፥ መሳ​ፍ​ን​ቱና ሹሞ​ቹም፥ አዛ​ዦ​ቹና የን​ጉሡ ኃያ​ላን#ዕብ. “አማ​ካ​ሪ​ዎች” ይላል። ተሰ​ብ​ስ​በው እሳቱ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን እን​ዳ​ል​በ​ላው፥ የራ​ሳ​ቸ​ውም ጠጕር እን​ዳ​ል​ተ​ነካ፥ ሰና​ፊ​ላ​ቸ​ውም እን​ዳ​ል​ተ​ለ​ወጠ፥ የእ​ሳ​ቱም ሽታ በላ​ያ​ቸው እን​ዳ​ል​ነ​በረ አዩ።
95 ንጉ​ሡም በፊ​ታ​ቸው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰገደ፥#“ንጉ​ሡም በፊ​ታ​ቸው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰገደ” የሚ​ለው በግ​እዝ ብቻ። ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርም መልሶ እን​ዲህ አለ፦ መል​አ​ኩን የላከ፥ ከአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ውም በቀር ማን​ንም አም​ላክ እን​ዳ​ያ​መ​ልኩ፥ ለእ​ር​ሱም እን​ዳ​ይ​ሰ​ግዱ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን አሳ​ል​ፈው የሰ​ጡ​ትን፥ የን​ጉ​ሡ​ንም ቃል የተ​ላ​ለ​ፉ​ትን፥ በእ​ርሱ የታ​መ​ኑ​ትን ባሪ​ያ​ዎ​ቹን ያዳነ፥ የሲ​ድ​ራ​ቅና የሚ​ሳቅ፥ የአ​ብ​ደ​ና​ጎም አም​ላክ ይመ​ስ​ገን። 96 እኔም እን​ደ​ዚህ የሚ​ያ​ድን ሌላ አም​ላክ የለ​ምና በሲ​ድ​ራ​ቅና በሚ​ሳቅ፥ በአ​ብ​ደ​ና​ጎም አም​ላክ ላይ የስ​ድ​ብን ነገር የሚ​ና​ገር ወገ​ንና ሕዝብ በልዩ ልዩ ቋን​ቋም የሚ​ና​ገሩ ይቈ​ረ​ጣሉ፤ ቤታ​ቸ​ውም ይዘ​ረ​ፋል ብየ አዝ​ዣ​ለሁ አለ። 97 የዚ​ያን ጊዜም ንጉሡ፥ ሲድ​ራ​ቅን ሚሳ​ቅ​ንና አብ​ደ​ና​ጎ​ንም በባ​ቢ​ሎን አው​ራጃ ውስጥ ሾማ​ቸው፤#“ሾማ​ቸው” የሚ​ለው በግ​እዝ ብቻ። ከፍ ከፍም አደ​ረ​ጋ​ቸው፤ በግ​ዛቱ ያሉ አይ​ሁ​ድ​ንም ሁሉ አስ​ገ​ዛ​ላ​ቸው።#“በግ​ዛቱ ያሉ አይ​ሁ​ድ​ንም ሁሉ አስ​ገ​ዛ​ላ​ቸው” የሚ​ለው በግ​እዝ ብቻ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ