የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘዳ​ግም 10

10
ሙሴ ዐሥሩ ትእ​ዛ​ዛ​ትን እንደ ገና መቀ​በሉ
(ዘፀ. 34፥1-10)
1“በዚ​ያን ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ፊተ​ኞች ያሉ​ትን ሁለት የድ​ን​ጋይ ጽላት ለአ​ንተ ቀር​ፀህ ወደ እኔ ወደ ተራ​ራው ውጣ፤ ለአ​ን​ተም የእ​ን​ጨት ታቦት ሥራ፤ 2በሰ​በ​ር​ሃ​ቸው በፊ​ተ​ኞቹ ጽላት የነ​በ​ሩ​ትን ቃሎች ሁሉ በእ​ነ​ዚህ ጽላት እጽ​ፋ​ለሁ፤ በታ​ቦ​ቱም ውስጥ ታደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለህ አለኝ። 3ከማ​ይ​ነ​ቅዝ እን​ጨ​ትም ታቦ​ቱን ሠራሁ፤ እንደ ፊተ​ኞ​ችም ሁለት የድ​ን​ጋይ ጽላት ቀረ​ፅሁ፤ ወደ ተራ​ራ​ውም ወጣሁ፤ ሁለ​ቱም ጽላት በእጄ ነበሩ፤ 4እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በተ​ራ​ራው ላይ በእ​ሳት መካ​ከል የተ​ና​ገ​ራ​ች​ሁን ዐሠ​ር​ቱን ቃላት ቀድሞ ተጽ​ፈው እንደ ነበረ በጽ​ላቱ ላይ ጻፈ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እነ​ር​ሱን ለእኔ ሰጠኝ። 5ተመ​ል​ሼም ከተ​ራ​ራው ወረ​ድሁ፤ ጽላ​ቱ​ንም በሠ​ራ​ሁት ታቦት ውስጥ አደ​ረ​ግ​ኋ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዳ​ዘ​ዘኝ በዚያ ኖሩ።
6“የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የማ​ስቢ ወገን ከሚ​ሆን ከኢ​ያ​ቅም ልጆች ቦታ ከቤ​ሮስ ተጓዙ። በዚ​ያም አሮን ሞተ፤ ተቀ​በ​ረም፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ ልጁ አል​ዓ​ዛር ካህን ሆነ። 7ከዚ​ያም ወደ ገድ​ገድ ተጓዙ፤ ከገ​ድ​ገ​ድም ወደ ውኃ ፈሳ​ሾች ምድር ወደ ኤጤ​ባታ ተጓዙ። 8በዚ​ያን ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን ታቦት ይሸ​ከም ዘንድ፥ እር​ሱ​ንም ለማ​ገ​ል​ገል በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይቆም ዘንድ፥ በስ​ሙም ይባ​ርክ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እስከ ዛሬ ድረስ የሌ​ዊን ነገድ ለየ። 9ስለ​ዚህ ለሌ​ዋ​ው​ያን ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ጋር ክፍ​ልና ርስት የላ​ቸ​ውም፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር#“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. እና በግ​እዝ የለም። እንደ ነገ​ራ​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስ​ታ​ቸው ነውና።
10“እኔም እንደ ፊተ​ኛው ጊዜ#“እንደ ፊተ​ኛው ጊዜ” የሚ​ለው በግ​እ​ዝና በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በተ​ራ​ራው ላይ ቆምሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚህ ጊዜ ደግሞ ሰማኝ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሊያ​ጠ​ፋ​ችሁ አል​ወ​ደ​ደም። 11እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ‘ተነ​ሥ​ተህ በሕ​ዝቡ ፊት ተጓዝ፤ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ልሰ​ጣ​ቸው ወደ ማል​ሁ​ላ​ቸው ምድር ይግቡ፤ ይው​ረ​ሱ​አ​ትም’ አለኝ።
ከእ​ስ​ራ​ኤል የሚ​ፈ​ለ​ገው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት መሆኑ
12“እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ አሁ​ንስ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ የሚ​ፈ​ል​ገው ምን​ድን ነው? አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትፈራ ዘንድ፥ በመ​ን​ገ​ዱም ሁሉ ትሄድ ዘንድ፥ አም​ላ​ክ​ህ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትወ​ድድ ዘንድ፥ በፍ​ጹ​ምም ልብህ፥ በፍ​ጹ​ምም ነፍ​ስህ ታመ​ል​ከው ዘንድ ነው እንጂ፥ 13መል​ካ​ምም እን​ዲ​ሆ​ን​ልህ ዛሬ ለአ​ንተ የማ​ዝ​ዘ​ውን የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛ​ዝና ሥር​ዐት ትጠ​ብቅ ዘንድ ነው እንጂ፤ 14እነሆ፥ ሰማይ፥ ሰማየ ሰማ​ያ​ትም፥ ምድ​ርም፥ በእ​ር​ስ​ዋም ያለው ሁሉ የአ​ም​ላ​ክህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው። 15ብቻ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁን መረ​ጣ​ቸው፤ ወደ​ዳ​ቸ​ውም፤ ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ እና​ን​ተን ዘራ​ቸ​ውን እንደ ዛሬው ሁሉ ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ መረጠ። 16እና​ንተ የል​ባ​ች​ሁን ክፋት ግዘሩ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አን​ገ​ታ​ች​ሁን አታ​ደ​ን​ድኑ። 17አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ማ​ል​ክት አም​ላክ፥ የጌ​ቶች ጌታ፥ ታላቅ አም​ላክ፥ ኀያ​ልም፥ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ራም፥ በፍ​ር​ድም የማ​ያ​ደላ፥ መማ​ለ​ጃም የማ​ይ​ቀ​በል ነውና። 18ለመ​ጻ​ተኛ፥ ለድሃ አደ​ጉና ለመ​በ​ለ​ቲቱ ይፈ​ር​ዳል፤ መብ​ልና ልብ​ስም ይሰ​ጠው ዘንድ ስደ​ተ​ኛ​ውን ይወ​ድ​ዳል። 19እና​ንተ በግ​ብፅ ሀገር ስደ​ተ​ኞች ነበ​ራ​ች​ሁና ስለ​ዚህ ስደ​ተ​ኛ​ውን ውደዱ። 20አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍራ፤ እር​ሱ​ንም አም​ልክ፤ እር​ሱ​ንም ተከ​ተል፤ በስ​ሙም ማል። 21ዐይ​ኖ​ችህ ያዩ​አ​ቸ​ውን እነ​ዚ​ህን ታላ​ላ​ቆች የከ​በ​ሩ​ትን ነገ​ሮች ያደ​ረ​ገ​ልህ እርሱ መመ​ኪ​ያ​ችሁ ነው፤ እር​ሱም አም​ላ​ክህ ነው። 22አባ​ቶ​ችህ ሰባ ነፍስ ሆነው ወደ ግብፅ ወረዱ፤ አሁን ግን አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብዛ​ት​ህን እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብት አደ​ረገ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ