ኦሪት ዘዳግም 13
13
1“ከአንተም ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ቢነሣ፥ ምልክትም፥ ተአምራትም ቢሰጥህ፥ 2እርሱም፦ ሄደን የማታውቃቸውን ሌሎች አማልክት እንከተል እናምልካቸውም ብሎ የተናገረህ ምልክቱ ወይም ተአምራቱ ቢፈጸም፥ 3አምላካችሁን እግዚአብሔርን በፍጹም ልባችሁ፥ በፍጹምም ነፍሳችሁ ትወድዱት እንደሆን ያውቅ ዘንድ አምላካችሁ እግዚአብሔር ሊፈትናችሁ ነውና የዚያን ነቢይ ቃል ወይም ያን ሕልም አላሚ አትስሙ። 4አምላካችሁን እግዚአብሔርን ተከተሉ፤ እርሱንም ፍሩ፤ ትእዛዙንም ጠብቁ፤ ቃሉንም ስሙ፥#ዕብ. “እርሱንም አምልኩ” የሚል ይጨምራል። እርሱንም ተማጠኑት። 5ከግብፅ ምድር ካወጣችሁ፥ ከባርነትም ቤት ካዳናችሁ ከአምላካችሁ ከእግዚአብሔር ሊያስታችሁ፥ አምላክህ እግዚአብሔርም ትሄድባት ዘንድ ካዘዘህ መንገድ ሊያወጣህ ተናግሮአልና ያ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ይገደል፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከአንተ አርቅ።
6“የአባትህ#“የአባትህ” የሚለው በዕብ. የለም። ወይም የእናትህ ልጅ ወንድምህ ወይም ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ ወይም አብራህ የምትተኛ ሚስትህ ወይም እንደ ነፍስህ ያለ ወዳጅህ በስውር፦ ና፥ ሄደን አንተም አባቶችህም የማታውቋቸውን ሌሎች አማልክት እናምልክ ብሎ ቢያስትህ፥ 7ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ወደ አንተ የቀረቡት ከአንተም የራቁት አንተን ከብበውህ ያሉ አሕዛብ ከሚያመልኩአቸው አማልክት፥ 8ከእርሱ ጋር አትተባበር፤ አትስማውም፤ ዐይንህም አይራራለት፤ አትማረውም፤ አትሸሽገውም፤ 9ነገር ግን ፈጽመህ ተናገር፤ እርሱን ለመግደል በፊት ያንተ እጅ፥ ከዚያም በኋላ የሕዝቡ ሁሉ እጅ በላዩ ትሁን። 10ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ካወጣህ ከአምላክህ ከእግዚአብሔር ሊያርቅህ ወድዶአልና በድንጋይ ይውገሩት፤ ይግደሉትም። 11እስራኤል ሁሉ ሰምተው ይፍሩ፤ እንዲህ ያለ ክፉ ሥራም እንደገና በእናንተ መካከል አይደገም።
12“አምላክህ እግዚአብሔር ልትኖርባት ከሰጠህ ከተሞች በአንዲቱ ከተማህ፦ 13ክፋተኞች ሰዎች ከእናንተ ዘንድ ወጥተው፦ ሄደን የማታውቋቸውን ሌሎች አማልክት እናምልክ ብለው የከተማቸውን ሰዎች አሳቱ ሲሉ ወሬ ብትሰማ፥ 14ትፈልጋለህ#“ትፈልጋለህ” የሚለው በግእዝና በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ትመረምራለህም፤ ትጠይቃለህም፤ እነሆም፥ እውነት ቢሆን፥ ይህም ክፉ ነገር በመካከልህ እንደ ተደረገ ርግጥ ሆኖ ቢገኝ፥ 15የዚያችን ሀገር ሰዎች በሰይፍ ስለት ፈጽሞ ትመታቸዋለህ፤ ሀገሪቱን፥ በውስጥዋም ያለውን ሁሉ ትረግማለህ። 16ዕቃዋንም ሁሉ ወደ አደባባይዋ ትሰበስባለህ፤ ከተማይቱንም፥ ዕቃዋንም ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት በእሳት ፈጽመህ ታቃጥላለህ፤ ለዘለዓለምም ወና ትሆናለች፤ ደግሞም አትሠራም። 17የእግዚአብሔር የመቅሠፍቱ ቍጣ ይመለስ ዘንድ፥ ለአባቶችህም እንደ ማለላቸው ይምርህ ዘንድ፥ ይራራልህም ዘንድ፥ ያበዛህም ዘንድ፥ ርጉም ከሆነው አንዳች ነገር በእጅህ አትንካ። 18ዛሬም እኔ የማዝዝህን ትእዛዝ ሁሉ ብትጠብቅ፥ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት መልካምና ጥሩ የሆነውን ብታደርግ፥ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል ብትሰማ ለእርሱ ልጅ ትሆናለህ።#“ለእርሱ ልጅ ትሆናለህ” የሚለው በዕብ. እና በግሪክ ሰባ. ሊ. የምዕራፍ 14 ማንሻ ነው።
Currently Selected:
ኦሪት ዘዳግም 13: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ