የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘዳ​ግም 13:1-3

ኦሪት ዘዳ​ግም 13:1-3 አማ2000

“ከአ​ን​ተም ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ቢነሣ፥ ምል​ክ​ትም፥ ተአ​ም​ራ​ትም ቢሰ​ጥህ፥ እር​ሱም፦ ሄደን የማ​ታ​ው​ቃ​ቸ​ውን ሌሎች አማ​ል​ክት እን​ከ​ተል እና​ም​ል​ካ​ቸ​ውም ብሎ የተ​ና​ገ​ረህ ምል​ክቱ ወይም ተአ​ም​ራቱ ቢፈ​ጸም፥ አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በፍ​ጹም ልባ​ችሁ፥ በፍ​ጹ​ምም ነፍ​ሳ​ችሁ ትወ​ድ​ዱት እን​ደ​ሆን ያውቅ ዘንድ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊፈ​ት​ና​ችሁ ነውና የዚ​ያን ነቢይ ቃል ወይም ያን ሕልም አላሚ አት​ስሙ።