የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘዳ​ግም 17

17
1“በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ጠላ ነውና ነውር ወይም ክፉ ነገር ያለ​በ​ትን በሬ ወይም በግ ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አት​ሠዋ።
2“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ጠህ ሀገ​ሮች በአ​ን​ዲ​ትዋ ውስጥ ወንድ ወይም ሴት ቢሆን ቃል ኪዳ​ኑን በማ​ፍ​ረስ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፋት የሠራ ቢገኝ፥ 3ሄዶም ሌሎች አማ​ል​ክ​ትን ያመ​ለከ፥ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላላ​ዘ​ዘህ ለፀ​ሐ​ይና ለጨ​ረቃ ወይም ለሰ​ማይ ከዋ​ክ​ብት የሰ​ገደ ቢገኝ፥ 4ቢያ​ወ​ሩ​ል​ህም#“ቢያ​ወ​ሩ​ል​ህም” የሚ​ለው በግ​እዙ የለም። ብት​ሰ​ማም፥ ያን ፈጽ​መህ መር​ምር፤ እነ​ሆም፥ እው​ነት ቢሆን፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም መካ​ከል እን​ዲህ ያለ ርኵ​ሰት እንደ ተሠራ ርግጥ ሆኖ ቢገኝ፥ 5ይህን ክፉ ነገር የሠ​ሩ​ትን ያን ወንድ ወይም ያችን ሴት ታወ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ፥#ዕብ. “ወደ በርህ ታመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ” ይላል። እስ​ኪ​ሞ​ቱም ድረስ በድ​ን​ጋይ ትመ​ት​ዋ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ። 6በሁ​ለት ወይም በሦ​ስት ምስ​ክ​ሮች ሞት የሚ​ገ​ባ​ቸው ይገ​ደሉ፤ በአ​ንድ ምስ​ክር ግን አይ​ገ​ደሉ። 7እር​ሱን ለመ​ግ​ደል በመ​ጀ​መ​ሪያ የም​ስ​ክ​ሮች እጅ በኋ​ላም የሕ​ዝቡ ሁሉ እጅ ትሁ​ን​በት፤ እን​ዲሁ ክፉ​ውን ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ አስ​ወ​ግዱ።
በካ​ህ​ና​ትና ዳኞች የሚ​ሰጡ የፍ​ርድ ውሳ​ኔ​ዎች
8“በደ​ምና በደም መካ​ከል፥ በፍ​ር​ድና በፍ​ርድ መካ​ከል፥ በመ​ቍ​ሰ​ልና በመ​ቍ​ሰል መካ​ከል፥ በክ​ር​ክ​ርና በክ​ር​ክር መካ​ከል በሀ​ገ​ርህ ውስጥ ሰዎች ስለ​ሚ​ከ​ራ​ከ​ሩ​በት ክር​ክር የሚ​ሳ​ንህ የፍ​ርድ ነገር ቢኖር፥ አንተ ተነ​ሥ​ተህ ስሙ በዚያ ይጠራ ዘንድ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ መረ​ጠው ስፍራ ትወ​ጣ​ለህ፤ 9ወደ ሌዋ​ው​ያን ካህ​ናት በዚ​ያም ዘመን ወደ አሉ ፈራ​ጆች መጥ​ተህ ትጠ​ይ​ቃ​ለህ፤ እነ​ር​ሱም የፍ​ር​ዱን ነገር ይነ​ግ​ሩ​ሃል። 10ስሙ በዚያ ይጠራ ዘንድ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ረ​ጠው ስፍራ እንደ ነገ​ሩህ ቃል ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ ያስ​ተ​ማ​ሩ​ህ​ንም ሕጉን ታደ​ርግ ዘንድ ጠብቅ። 11እን​ዳ​ስ​ተ​ማ​ሩ​ህም ሕግ፥#“እን​ዳ​ስ​ተ​ማ​ሩ​ህም ሕግ” የሚ​ለው በግ​እዙ የለም። እንደ ነገ​ሩ​ህም ፍርድ አድ​ርግ፤ ከነ​ገ​ሩህ ፍርድ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አት​በል። 12ማና​ቸ​ውም ሰው ቢኰራ፥ በአ​ም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ለማ​ገ​ል​ገል የሚ​ቆ​መ​ውን ካህ​ኑን ወይም በዚያ ወራት ያለ​ውን ፈራ​ጁን ባይ​ሰማ ያ ሰው ይሙት፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ ክፉ​ውን አስ​ወ​ግዱ፤ 13ሕዝ​ቡም ሁሉ ሰምቶ ይፈ​ራል፤ ከዚ​ያም ወዲያ ደግሞ አይ​በ​ድ​ልም።
ስለ ንጉሥ የተ​ሰጠ መመ​ሪያ
14“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት አድ​ርጎ ወደ​ሚ​ሰ​ጥህ ምድር በገ​ባህ፥ በወ​ረ​ስ​ሃ​ትም ጊዜ፥ በተ​ቀ​መ​ጥ​ህ​ባ​ትም ጊዜ፦ በዙ​ሪ​ያዬ እን​ዳ​ሉት አሕ​ዛብ ሁሉ በላዬ አለቃ#ዕብ. “ንጉሥ አነ​ግ​ሣ​ለሁ ...” ይላል። እሾ​ማ​ለሁ ብትል፥ 15ከወ​ን​ድ​ሞ​ችህ መካ​ከል አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የመ​ረ​ጠ​ውን ለአ​ንተ አለቃ ትሾ​ማ​ለህ፤#ዕብ. “ለአ​ንተ ታነ​ግ​ሣ​ለህ ...” ይላል። ወን​ድ​ምህ ያል​ሆ​ነ​ውን ሌላ ሰው በአ​ንተ ላይ መሾም አት​ች​ልም። 16ለእ​ርሱ ፈረ​ሶ​ችን እን​ዳ​ያ​በዛ፥ ሕዝ​ቡ​ንም ወደ ግብፅ እን​ዳ​ይ​መ​ልስ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ በዚ​ያች መን​ገድ መመ​ለ​ስን አት​ድ​ገም ብሎ​አ​ልና። 17ልቡም እን​ዳ​ይ​ስት ሚስ​ቶ​ችን ለእ​ርሱ አያ​ብዛ፤ ወር​ቅና ብርም ለእ​ርሱ እጅግ አያ​ብዛ።
18“በግ​ዛ​ቱም#ዕብ. “በመ​ን​ግ​ሥቱ ዙፋን ...” ይላል። በተ​ቀ​መጠ ጊዜ ከሌ​ዋ​ው​ያን ካህ​ናት ወስዶ ይህን ሁለ​ተኛ ሕግ ለራሱ በመ​ጽ​ሐፍ ይጻፍ። 19መጽ​ሐፉ ከእ​ርሱ ጋር ይኑር፤ ዕድ​ሜ​ው​ንም ሁሉ ያን​ብ​በው። አም​ላ​ኩን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት ይማር ዘንድ፥ የዚ​ህን ሕግ ቃል ሁሉ፥ ይህ​ች​ንም ሥር​ዐት ጠብቆ ያደ​ርግ ዘንድ፥ 20ልቡ በወ​ን​ድ​ሞቹ ላይ እን​ዳ​ይ​ኰራ፥ የአ​ም​ላኩ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ እን​ዳ​ይ​ተው፥ ቀኝና ግራም እን​ዳ​ይል፥ እር​ሱም ልጆ​ቹም በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ረዥም ዘመን ይገዙ ዘንድ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ