ኦሪት ዘዳግም 19
19
የመማጠኛ ከተሞች
(ዘኍ. 35፥9-28፤ ኢያ. 20፥1-9)
1“አምላክህ እግዚአብሔር ምድራቸውን የሚሰጥህን አሕዛብ ባጠፋቸው ጊዜ፥ በወረስሃቸውም ጊዜ፥ በከተሞቻቸውና በቤቶቻቸውም በተቀመጥህ ጊዜ፥ 2አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ በምድርህ መካከል ሦስት ከተሞችን ለራስህ ትለያለህ። 3ለአንተም መንገድህን ታዘጋጃለህ፤ አምላክህም እግዚአብሔር የሚያወርስህን ምድር ከሦስት አድርገህ ትከፍላለህ፤ ለነፍሰ ገዳይም ሁሉ መማጸኛ ይሁን።
4“የነፍሰ ገዳይ ሕግ ይህ ነው፤ ቀድሞ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ትናንትናና ከትናንትና በፊት” ይላል። ጠላቱ ሳይሆን ባልንጀራውን ሳያውቅ የገደለ ወደዚያ ሸሽቶ በሕይወት ይኑር። 5ሰው ከባልንጀራው ጋር እንጨት ሊለቅም ወደ ዱር ቢሄድ፥ ዛፉንም ሲቈርጥ ምሳሩ ከእጁ ቢወድቅ፥ ብረቱም ከእጄታው ቢወልቅ፥ በባልንጀራውም ላይ ቢወድቅና ቢገድለው፥ ከእነዚህ ከተሞች በአንዲቱ ተማጥኖ በሕይወት ይኖራል፤ 6ባለ ደሙ ነፍሰ ገዳዩን በልቡ ተናድዶ እንዳያሳድደው መንገዱም ሩቅ ስለሆነ አግኝቶ እንዳይገድለው፥ አስቀድሞ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ትናንትናና ከትናንትና በፊት” ይላል። ጠላቱ አልነበረምና ሞት አይገባውም። 7ስለዚህ እኔ፦ ለአንተ ሦስት ከተሞችን ለይ ብዬ አዝዤሃለሁ። 8አምላክህም እግዚአብሔር ለአባቶችህ እንደ ማለላቸው ዳርቻህን ቢያሰፋ፥ ለአባቶችህ#ግእዙ “ለወንድሞችህ” ይላል። እሰጣቸዋለሁ ብሎ የተናገረውን ምድር ሁሉ ቢሰጥህ፥ 9አምላክህን እግዚአብሔርን ትወድድ ዘንድ፥ ሁልጊዜም በመንገዱ ሁሉ ትሄድ ዘንድ፥ ዛሬ የማዝዝህን ይህችን ትእዛዝ ሁሉ ታደርጋት ዘንድ ብትሰማ፥ በእነዚህ በሦስት ከተሞች ላይ ሌሎች ሦስት ከተሞችን ትጨምራለህ። 10አምላክህ እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ በሚሰጥህ ምድር ውስጥ ንጹሕ ደም እንዳይፈስስ፥ በውስጥህም የደም ወንጀለኛ እንዳይኖር።
11“ሰው ግን ባልንጀራውን ቢጠላ፥ ቢሸምቅበትም፥ በእርሱም ላይ ቢነሣ፥ ቢገድለውም፥ ከእነዚህ ከተሞች በአንዲቱ ቢማጠን፥ 12የከተማው ሽማግሌዎች ይልካሉ፤ ከዚያም ይይዙታል። በባለደሙም እጅ አሳልፈው ይሰጡታል፤ ይሞታልም። 13ዐይንህም አትራራለት፤ ነገር ግን ንጹሑን ደም ከእስራኤል ታስወግዳለህ፤ መልካምም ይሆንልሃል።
ድንበር ማፍረስ እንደማይገባ
14“አምላክህ እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ በሚሰጥህ ምድር፤ በምትካፈላት ርስትህ አባቶችህ የተከሉትን የባልንጀራህን የድንበር ምልክት አትንቀል።
ስለ ምስክሮች የተሰጠ መመሪያ
15“ስለ በደል ሁሉ፥ ክፉ በማድረግም ስለሚሠራት ኀጢአት ሁሉ በማንም ላይ አንድ ምስክር አይሁን፤ በሁለት ምስክሮች ወይም በሦስት ምስክሮች ቃል ነገር ሁሉ ይጸናል። 16በዐመፃ ይከስሰው ዘንድ በሰው ላይ ሐሰተኛ ምስክር ቢቆም፥ 17ሁለቱ ጠበኞች በእግዚአብሔር ፊት በካህናቱና በዚያ ዘመን በሚፈርዱ ፈራጆች ፊት ይቆማሉ፤ 18ፈራጆቹም አጥብቀው ይመረምራሉ፤ ያም ምስክር ሐሰተኛ ምስክር ሆኖ በወንድሙ ላይ በሐሰት ተናግሮ ቢገኝ፥ 19በወንድሙ ላይ ክፋትን ያደርግ ዘንድ እንደ ወደደ በእርሱ ላይ ታደርጉበታላችሁ፤ እንዲሁም ከእናንተ መካከል ክፉውን ታስወግዳላችሁ። 20ሌላውም ሰምቶ ይፈራል፤ እንደዚህ ያለውንም ክፋት በመካከልህ ከእንግዲህ ወዲህ ደግሞ አያደርግም። 21ዐይንህም አትራራለት፤ ነፍስ በነፍስ፥ ዐይን በዐይን፥ ጥርስ በጥርስ፥ እጅ በእጅ፥ እግር በእግር ይመለሳል።
Currently Selected:
ኦሪት ዘዳግም 19: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ