ኦሪት ዘዳግም 2
2
እስራኤል በበረሃ የዞሩባቸው ዓመታት
1“እግዚአብሔርም እንዳለኝ ተመልሰን በኤርትራ ባሕር መንገድ ወደ ምድረ በዳ ሄድን፤ የሴይርንም ተራራ ብዙ ቀን ዞርን። 2እግዚአብሔርም እንዲህ ብሎ ተናገረኝ፦ 3‘ይህን ተራራ መዞር ይበቃችኋል፤ ተመልሳችሁ ወደ መስዕ ሂዱ።’ 4ሕዝቡንም እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፦ በሴይር ላይ በተቀመጡት በወንድሞቻችሁ በዔሳው ልጆች ሀገር ታልፋላችሁ፤ እነርሱ ይፈሩአችኋል፤ እንግዲህ እጅግ ተጠንቀቁ። 5የሴይርን ተራራ ለዔሳው ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ እኔ ከምድራቸው የጫማ መርገጫ ታህል እንኳን አልሰጣችሁምና አትጣሉአቸው። 6ከእነርሱ በገንዘብ ምግብ ገዝታችሁ ትበላላችሁ፤ ውኃም ደግሞ በገንዘብ በመለኪያ ገዝታችሁ ትጠጣላችሁ። 7አምላክህ እግዚአብሔር የእጅህን ሥራ ሁሉ ባርኮልሃልና፤ ይህን ታላቅና የሚያስፈራ ምድረ በዳ እንዴት እንደ ዞርኸው ዕወቅ፤#ዕብ. “በዚህ በታላቅ ምድረ በዳ መሄድህን ዐውቆአል” ይላል። በዚህ አርባ ዓመት ውስጥ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነበረ፤ ከተናገርኸው ሁሉ አንዳችም አላሳጣህም። 8በሴይርም ከተቀመጡት ከወንድሞቻችን ከዔሳው ልጆች በዓረባ መንገድ ከኤሎንና#ዕብ. “ከኤላትና” ይላል። ከጋስዮን-ጋብር አለፍን። ተመልሰንም በሞዓብ ምድረ በዳ መንገድ አለፍን።
9“እግዚአብሔርም አለኝ፦ እኔ አሮኤርን#ዕብ. “ዔርን” ይላል። ለሎጥ ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ ከምድሩ ርስት አልሰጣችሁምና ሞዓባውያንን አትጣላ፤ በሰልፍም አትውጋቸው። 10እንደ ዔናቃውያን ታላቅና ብዙ ሕዝብ ኀያላንም የሆኑ ኦሚናውያን አስቀድሞ በዚያ ይቀመጡ ነበር። 11እነርሱም ደግሞ እንደ ዔናቃውያን ራፋይም ተብለው ይታወቁ ነበር፤ ሞዓባውያን ግን “ኦሚን” ብለው ይጠሩአቸው ነበር። 12ሖራውያንም ደግሞ አስቀድሞ በሴይር ላይ ተቀምጠው ነበር፤ የዔሳው ልጆች ግን መቱአቸው፤ ከፊታቸውም አጠፉአቸው፤ እግዚአብሔርም በሰጠው በርስቱ ምድር እስራኤል እንዳደረገ፥ በስፍራቸው ተቀመጡ። 13አሁንም ‘ተነሡና ተጓዙ፤ የዛሬድንም ፈፋ ተሻገሩ፤’ የዛሬድንም ፈፋ ተሻገርን። 14የዛሬድንም ፈፋ እስከ ተሻገርንበት ድረስ፥ እግዚአብሔር እንደ ማለባቸው ተዋጊዎች የሆኑ የዚያች ትውልድ ሰዎች ከሰፈሩ መካከል እስከ ጠፉ ድረስ፥ ከቃዴስ በርኔ የተጓዝንበት ዘመን ሠላሳ ስምንት ዓመት ሆነ። 15ከሰፈርም መካከል ተለይተው እስኪጠፉ ድረስ የእግዚአብሔር እጅ በላያቸው ነበረ።
16“እንዲህም ሆነ፤ ተዋጊዎቹ ከጠፉ፥ ከሕዝቡም መካከል ከሞቱ በኋላ፥ 17እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናገረኝ፦ 18‘አንተ ዛሬ የሞዓብን ዳርቻ አሮኤርን ታልፋለህ፤ 19ለሎጥም ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ ከአሞን ልጆች ምድር ርስት አልሰጥህምና በአሞን ልጆች አቅራቢያ ስትደርስ አትጣላቸው፤ አትውጋቸውም።’ 20ያም ደግሞ የራፋይም ምድር ተብሎ ተቈጠረ፤ ራፋይምም አስቀድሞ በዚያ ተቀምጠው ነበረ፤ አሞናውያን ግን “ዘምዞማውያን” ብለው ይጠሩአቸዋል። 21እነርሱም እንደ ዔናቃውያን ታላቅና ብዙ፥ ጽኑዓንም ሕዝብ ነበሩ፤#ዕብ. “እንደ ዔናቅም ልጆች ቁመታቸው የረዘመ ነበሩ” ይላል። እግዚአብሔርም ከፊታቸው አጠፋቸው፤ እነርሱንም አሳድደው በስፍራቸው ተቀመጡ። 22ሖራውያንን ከፊታቸው አጥፍቶ በሴይር ለተቀመጡት ለዔሳው ልጆች እንዳደረገ#ዕብ. “እንዲሁ ለእነርሱ አደረገ እነርሱንም አሳድደው ...” ይላል። እነርሱ ወረሱአቸው፤ በእነርሱም ፋንታ#ዕብ. “በስፍራቸው” ይላል። እስከ ዛሬ ድረስ ተቀመጡ። 23እስከ ጋዛም ድረስ በአሴሮት ተቀምጠው የነበሩትን ኤዋውያንንና ከቀጰዶቅያ የወጡ ቀጰዶቃውያንን#ዕብ. “ከከፍቶር የወጡ ከፍቶራውያን” ይላል። አጠፉአቸው፤ በእነርሱም ፋንታ ተቀመጡ። 24ደግሞም አለ፦ ተነሥታችሁ ሂዱ፤ የአርኖንንም ሸለቆ ተሻገሩ፤ እነሆ፥ አሞሬዎናዊውን የሐሴቦንን ንጉሥ ሴዎንን፥ ምድሩንም በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁ፤ እርስዋን ግዛት፤ ውረሳት፥ ከእርሱም ጋር ተዋጋ። 25ከሰማይ በታች ባሉ አሕዛብ ሁሉ ላይ ማስደንገጥህንና ማስፈራትህን እሰድድ ዘንድ ዛሬ እጀምራለሁ፤ ስምህን በሰሙ ጊዜ በፊትህ ይንቀጠቀጣሉ፤ ድንጋጤም ይይዛቸዋል።
እስራኤል ንጉሥ ሴዎንን ድል እንደ አደረጉ (ዘኍ. 21፥ 21-30)
26“ከቄድሞትም ምድረ በዳ የሰላምን ቃል ይነግሩት ዘንድ ወደ ሐሴቦን ንጉሥ ወደ ሴዎን እንዲህ ብዬ መልእክተኞችን ላክሁ፦ 27‘በሀገርህ ላይ ልለፍ፤ በአውራ ጎዳና እሄዳለሁ፤ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አልተላለፍም። 28የምበላውን ምግብ በገንዘብ ሽጥልኝ፤ የምጠጣውንም ውኃ በገንዘብ ስጠኝ፤ በእግሬ ብቻ ልለፍ፤ 29በሴይር የተቀመጡ የዔሳው ልጆች፥ በአሮዔርም የተቀመጡ ሞዓባውያን እንዳደረጉልኝ፥ አምላካችን እግዚአብሔር ወደሚሰጠን ምድር ዮርዳኖስን እስክሻገር ድረስ በእግሬ ልለፍ። 30የሐሴቦን ንጉሥ ሴዎን ግን ያሳልፈን ዘንድ አልፈቀደም፤ እንደ ዛሬው ሁሉ በእጅህ አሳልፎ ይሰጠው ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር መንፈሱን አደንድኖታልና፥ ልቡንም አጽንቶታልና። 31እግዚአብሔርም፦ ‘የሐሴቦንን ንጉሥ አሞራዊውን ሴዎንንና ምድሩን በፊትህ በእጅህ አሳልፌ መስጠት እነሆ፥ ጀመርሁ፤ ምድሩን ትገዛ ዘንድ መውረስ ጀምር’ አለኝ። 32ሴዎንም ሕዝቡም ሁሉ ሊዋጉን ወደ ኢያሳ ወጡ። 33አምላካችንም እግዚአብሔር እርሱን አሳልፎ በእጃችን ሰጠን፤ እርሱንም፥ ልጆቹንም፥ ሕዝቡንም ሁሉ መታን። 34በዚያን ጊዜም ከተሞቹን ሁሉ ወሰድን፤ ከተማውንም#ዕብ. “የተቀመጡባቸውን ሰዎች” ይላል። ሁሉ፥ ሴቶችንም፥ ሕፃኖችንም አጠፋን፤ አንዳችም የሸሸ በሕይወት አላስቀረንም፥ 35ለእኛ ከማረክናቸው ከብቶቻቸውና ከከተሞቻቸው ከወሰድነው ምርኮ በቀር። 36በአርኖን ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔርና በሸለቆውም ውስጥ ካለችው ከተማ ጀምረን እስከ ገለዓድ ተራራ ድረስ ማንኛዪቱም ከተማ አላመለጠችንም፤ አምላካችን እግዚአብሔር ሁሉን አሳልፎ በእጃችን ሰጠን። 37ዳሩ ግን አምላካችን እግዚአብሔር እንዳዘዘን ወደ አሞን ልጆች ምድር፥ በያቦቅም ወንዝ አጠገብ ወደ አለው ስፍራ ሁሉ፥ በተራራማውም ሀገር ወደ አሉ ከተሞች አልደረስንም።
Currently Selected:
ኦሪት ዘዳግም 2: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ