ኦሪት ዘዳግም 21
21
ባልታወቀ ሰው ስለ ተፈጸመ ግድያ
1“አምላክህ እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ በሚሰጥህ ምድር የተገደለ ሰው በሜዳ ወድቆ ቢገኝ፥ ገዳዩም ባይታወቅ፥ 2ሽማግሌዎችህና ፈራጆችህ ወጥተው በተገደለው ሰው ዙሪያ እስካሉት ከተሞች ድረስ በስፍር ይለኩ፤ 3ለተገደለውም ሰው አቅራቢያ የሆነች የከተማዪቱ ሽማግሌዎች ከላሞች ለሥራ ያልደረሰችውን፥ ቀንበርም ያልተጫነባትን ጊደር ይውሰዱ፤ 4የዚያችም ከተማ ሽማግሌዎች ጊደሪቱን ይዘው ፈሳሽ ውኃ ወዳለበት ወዳልታረሰና ዘርም ወዳልተዘራበት ሽለቆ ይሄዳሉ፤ በዚያም በሸለቆው ውስጥ የጊደሪቱን ቋንጃዋን ይቈርጣሉ። 5የሌዊ ልጆች ካህናትም ይቀርባሉ፤ በፊቱ እንዲያገለግሉ፥ በስሙም እንዲባርኩ አምላክህ እግዚአብሔር መርጦአቸዋልና፤ በእነርሱም ቃል ክርክር ሁሉ ጕዳትም ሁሉ ይቆማልና፤ 6ወደ ተገደለው ሰው አቅራቢያ የሆነችው የከተማዪቱ ሽማግሌዎች በሸለቆው ውስጥ ቋንጃዋ በተቈረጠው ጊደር ራስ ላይ እጃቸውን ይታጠቡ፦ 7‘እጆቻችን ይህን ደም አላፈሰሱም፤ ዐይኖቻችንም አላዩም፤ 8አቤቱ፥ ከግብፅ ምድር የተቤዠኸውን ሕዝብህን እስራኤልን ይቅር በል፤ በሕዝብህም በእስራኤል ላይ የንጹሑን ደም በደል አትቍጠር’ ብለው ይናገሩ፤ ስለ ደሙም ይሰረይላቸዋል። 9አንተም በእግዚአብሔር ፊት መልካምና ጥሩ የሆነውን ባደረግህ ጊዜ የንጹሑን ደም በደል#“በደል” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ከመካከላቸው ታርቃለህ።
በጦርነት ስለ ተማረኩ ሴቶች
10“ጠላቶችህን ልትወጋ በወጣህ ጊዜ አምላክህም እግዚአብሔር በእጅህ አሳልፎ በሰጣቸውና በማረክሃቸው ጊዜ፥ 11በምርኮው ውስጥ የተዋበች ሴት ብታይ፥ ብትመኛትም፥ ሚስትም ልታደርጋት ብትወድድ፥ 12ወደ ቤትህ ታመጣታለህ፤ ራስዋንም ትላጫታለህ፤ ጥፍርዋንም ትቈርጥላታለህ፤ 13የተማረከችበትንም ልብስ ታወልቅላታለህ፤ በቤትህም ታስቀምጣታለህ፤ ስለ አባቷና ስለ እናቷ አንድ ወር ሙሉ ታለቅሳለች፤ ከዚያም በኋላ ትደርስባታለህ፤ ባልም ትሆናታለህ፤ እርስዋም ሚስት ትሆንልሃለች። 14ከዚያም በኋላ በእርስዋ ደስ ባይልህ አርነት አውጥተህ ትለቅቃታለህ፤ በዋጋ ግን አትሸጣትም፤ አግብተሃታልና እንደባሪያ አትቍጠራት።
ስለ በኵር ልጅ መብት
15“ለአንድ ሰው አንዲቱ የተወደደች፥ አንዲቱም የተጠላች ሁለት ሚስቶች ቢኖሩት፥ ለእርሱም የተወደደችው፥ ደግሞም የተጠላችው ልጆችን ቢወልዱ፥ በኵሩም ከተጠላችው ሚስት የተወለደው ልጅ ቢሆን፥ 16ለልጆቹ ከብቱን በሚያወርስበት ቀን ከተጠላችው ሚስት በተወለደው በበኵሩ ፊት ከተወደደችው ሚስት የተወለደውን ልጅ በኵር ያደርገው ዘንድ አይገባውም፤ 17ነገር ግን ከከብቱ ሁለት እጥፍ ለእርሱ በመስጠት ከተጠላችው ሚስት የተወለደው ልጅ በኵር እንደ ሆነ ያስታውቅ። የኀይሉ መጀመሪያ ነውና በኵርነቱ የእርሱ ነው።
ስለማይታዘዙ ልጆች
18“ማንም ሰው ለአባቱ ቃልና ለእናቱ ቃል የማይታዘዝ፥ ቢገሥጹትም የማይሰማቸው ትዕቢተኛና ዐመፀኛ ልጅ ቢኖረው፥ 19አባቱና እናቱ ይዘው ወደ ከተማዉ ሽማግሌዎች፥ ወደሚኖርበትም ስፍራ በር ይውሰዱት፤ 20የከተማዉንም ሰዎች፦ ‘ይህ ልጃችን ትዕቢተኛና ዐመፀኛ ነው፥ ቃላችንንም አይሰማም፤ ስስታምና ሰካራም ነው’ ይበሉአቸው። 21የከተማዉም ሰዎች ሁሉ በድንጋይ ደብድበው ይግደሉት፤ እንዲህም ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታርቃለህ፤ እስራኤልም ሁሉ ሰምተው ይፈራሉ።
ልዩ ልዩ ሕጎች
22“ማንም ሰው ለሞት የሚያበቃውን ኀጢአት ቢሠራ፥ እንዲሞትም ቢፈረድበት፥ በእንጨትም ላይ ብትሰቅለው፥ 23በእንጨት ላይ የተሰቀለ በእግዚአብሔር ዘንድ የተረገመ ነውና ሥጋው በእንጨት ላይ አይደር፤ ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ የሰጠህን ምድር እንዳታረክስ በእርግጥ በዚያው ቀን ቅበረው።
Currently Selected:
ኦሪት ዘዳግም 21: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ