የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘዳ​ግም 28

28
በታ​ዛ​ዥ​ነት የሚ​ገኝ በረ​ከት
(ዘሌ. 26፥3-13ዘዳ. 7፥12-24)
1 # ግሪክ ሰባ. ሊ. “አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ​ሚ​ሰ​ጠን ምድር ለመ​ግ​ባት ዮር​ዳ​ኖ​ስን በተ​ሻ​ገ​ርህ ጊዜ” የሚል አለው። “እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ፈጽ​መህ ብት​ሰማ፥ ዛሬም ያዘ​ዝ​ሁ​ህን ትእ​ዛ​ዙን ሁሉ ብታ​ደ​ርግ፥ ብት​ጠ​ብ​ቅም፥ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከም​ድር አሕ​ዛብ ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያደ​ር​ግ​ሃል። 2የአ​ም​ላ​ክ​ህ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ብት​ሰማ እነ​ዚህ በረ​ከ​ቶች ሁሉ ይመ​ጡ​ል​ሃል፤ ያገ​ኙ​ህ​ማል። 3አንተ በከ​ተማ ቡሩክ ትሆ​ና​ለህ፤ በእ​ር​ሻም ቡሩክ ትሆ​ና​ለህ። 4የሆ​ድህ ፍሬ፥ የም​ድ​ር​ህም ፍሬ፥ የከ​ብ​ት​ህም ፍሬ፥#“የከ​ብ​ት​ህም ፍሬ” የሚ​ለው በግ​እ​ዝና በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። የላ​ም​ህም መንጋ፥ የበ​ግ​ህም መንጋ ቡሩክ ይሆ​ናል። 5መዛ​ግ​ብ​ት​ህና የቀ​ረ​ውም ሁሉ ቡሩክ ይሆ​ናል።#ዕብ. “እን​ቅ​ብ​ህና ቡሃ​ቃህ ቡሩክ ይሆ​ናል” ይላል። 6አን​ተም በመ​ግ​ባ​ትህ ቡሩክ ትሆ​ና​ለህ፥ በመ​ው​ጣ​ት​ህም ቡሩክ ትሆ​ና​ለህ።
7“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ግ​ርህ በታች ይወ​ድቁ ዘንድ የሚ​ቃ​ወ​ሙ​ህን ጠላ​ቶ​ች​ህን በእ​ጅህ ይጥ​ላ​ቸ​ዋል፤ በአ​ንድ መን​ገድ ይመ​ጡ​ብ​ሃል፤ በሰ​ባ​ትም መን​ገድ ከፊ​ትህ ይሸ​ሻሉ። 8እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በረ​ከ​ቱን በአ​ንተ ላይ፥ በጎ​ተ​ራህ፥ በእ​ህ​ል​ህም ሥራ ሁሉ እን​ዲ​ወ​ርድ ይል​ካል፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ሰ​ጥ​ህም ምድር ይባ​ር​ክ​ሃል። 9የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ብት​ሰማ፥ በመ​ን​ገ​ዱም ብት​ሄድ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ባ​ቶ​ችህ እንደ ማለ ለእ​ርሱ የተ​ቀ​ደሰ ሕዝብ አድ​ርጎ ያቆ​ም​ሃል። 10የም​ድር አሕ​ዛ​ብም ሁሉ የአ​ም​ላ​ክህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም በአ​ንተ ላይ እንደ ተጠራ አይ​ተው ይፈ​ሩ​ሃል። 11አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እር​ስ​ዋን ይሰ​ጥህ ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ችህ በማ​ለ​ላ​ቸው በም​ድ​ርህ ላይ፥ በሆ​ድህ ፍሬ፥ በእ​ር​ሻ​ህም ፍሬ፥ ከብ​ቶ​ች​ህን በማ​ብ​ዛት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ​ነ​ቱን ያበ​ዛ​ል​ሃል። 12እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለም​ድ​ርህ በወ​ራቱ ዝና​ብን ይሰጥ ዘንድ፥ የእ​ጅ​ህ​ንም ሥራ ሁሉ ይባ​ርክ ዘንድ መል​ካ​ሙን መዝ​ገብ ሰማ​ዩን ይከ​ፍ​ት​ል​ሃል፤ ለብዙ አሕ​ዛ​ብም ታበ​ድ​ራ​ለህ፥ አንተ ግን ከማ​ንም አት​በ​ደ​ርም፤ ብዙ አሕ​ዛ​ብን ትገ​ዛ​ለህ፥ አን​ተን ግን እነ​ርሱ አይ​ገ​ዙ​ህም።#“ብዙ አሕ​ዛ​ብን ትገ​ዛ​ለህ ፤ አን​ተን ግን እነ​ርሱ አይ​ገ​ዙ​ህም” የሚ​ለው በዕብ. የለም። 13ዛሬም ያዘ​ዝ​ሁ​ህን የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ሰም​ተህ ብት​ጠ​ብ​ቃት፥ ብታ​ደ​ር​ጋ​ትም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራስ ያደ​ር​ግ​ሃል እንጂ ጅራት አያ​ደ​ር​ግ​ህም፤ ሁል​ጊ​ዜም በላይ እንጂ በታች አት​ሆ​ንም። 14ዛሬም ካዘ​ዝ​ሁህ ከእ​ነ​ዚህ ቃሎች ወደ ቀኝ፥ ወደ ግራም ፈቀቅ ባትል፥ ታመ​ል​ካ​ቸ​ውም ዘንድ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ባት​ከ​ተል።
በማ​ይ​ታ​ዘዙ ላይ የሚ​ደ​ርስ ርግ​ማን
(ዘሌ. 26፥14-46)
15“ነገር ግን የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ባት​ሰማ፥ ዛሬም ያዘ​ዝ​ሁ​ህን ሥር​ዐ​ቱ​ንና ትእ​ዛ​ዙን ሁሉ ባት​ጠ​ብቅ፥ ባታ​ደ​ር​ግም፥ እነ​ዚህ መር​ገ​ሞች ሁሉ ይመ​ጡ​ብ​ሃል፤ ያገ​ኙ​ህ​ማል። 16በከ​ተማ ርጉም ትሆ​ና​ለህ፤ በእ​ር​ሻም ርጉም ትሆ​ና​ለህ። 17መዛ​ግ​ብ​ት​ህና የቀ​ረ​ውም ርጉ​ማን ይሆ​ናሉ። 18የሆ​ድህ ፍሬ፥ የም​ድ​ር​ህም ፍሬ፥ የላ​ም​ህም መንጋ፥ የበ​ግ​ህም መንጋ ርጉ​ማን ይሆ​ናሉ። 19አንተ በመ​ግ​ባ​ት​ህና በመ​ው​ጣ​ት​ህም ርጉም ትሆ​ና​ለህ። 20እኔን ስለ​ተ​ው​ኸኝ፥ ስለ ሥራህ ክፋት፥ እስ​ክ​ት​ጠፋ፥ ፈጥ​ነ​ህም እስ​ክ​ታ​ልቅ ድረስ በም​ት​ሠ​ራው ሥራ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ችግ​ርን፥ ረኃ​ብን፦ ቸነ​ፈ​ር​ንም ይል​ክ​ብ​ሃል። 21እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትወ​ር​ሳት ዘንድ ከም​ት​ገ​ባ​ባት ምድር እስ​ኪ​ያ​ጠ​ፋህ ድረስ ሞትን ያመ​ጣ​ብ​ሃል። 22እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በክ​ሳት፥ በን​ዳ​ድም፥ በጥ​ብ​ሳ​ትም፥ በት​ኵ​ሳ​ትም፥ በድ​ር​ቅም፥ በዋ​ግም፥ በአ​ረ​ማ​ሞም ይመ​ታ​ሃል፤ እስ​ክ​ት​ጠ​ፋም ድረስ ያሳ​ድ​ዱ​ሃል። 23በራ​ስ​ህም ላይ ሰማይ ናስ ይሆ​ን​ብ​ሃል፤ ከእ​ግ​ር​ህም በታች ምድ​ሪቱ ብረት ትሆ​ን​ብ​ሃ​ለች። 24እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ድ​ር​ህን ዝናብ ጭጋግ#ዕብ. “የም​ድ​ር​ህን ዝናብ ትቢ​ያና አፈር ያደ​ር​ጋል” ይላል። ያደ​ር​ጋል፤ እስ​ክ​ት​ጠ​ፋም ድረስ ከሰ​ማይ አፈር ይወ​ር​ድ​ብ​ሃል።
25“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከጠ​ላ​ቶ​ችህ ፊት የተ​መ​ታህ ያደ​ር​ግ​ሃል፤ በአ​ንድ መን​ገድ ትወ​ጣ​ባ​ቸ​ዋ​ለህ፤ በሰ​ባት መን​ገ​ድም ከእ​ነ​ርሱ ትሸ​ሻ​ለህ፤ በም​ድ​ርም መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ የተ​በ​ተ​ንህ ትሆ​ና​ለህ። 26ሬሳህ ለሰ​ማይ ወፎች ሁሉ፥ ለም​ድ​ርም አራ​ዊት#“ለም​ድር አራ​ዊት” የሚ​ለው በግ​እዝ የለም። መብል ይሆ​ናል፤ የሚ​ቀ​ብ​ር​ህም አታ​ገ​ኝም።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “የሚ​ያ​ስ​ፈ​ራ​ቸ​ውም የለም” ይላል። 27እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈውስ በሌ​ለው በግ​ብፅ ቍስል፥ በእ​ባ​ጭም፥ በቋ​ቁ​ቻም፥ በች​ፌም ይመ​ታ​ሃል። 28እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዕ​ብ​ደት፥ በዕ​ው​ር​ነት፥ በልብ ድን​ጋ​ጤም ይመ​ታ​ሃል። 29ዕውር በጨ​ለማ እን​ደ​ሚ​ዳ​ብስ በቀ​ትር ጊዜ ትዳ​ብ​ሳ​ለህ፤ መን​ገ​ድ​ህም የቀና አይ​ሆ​ንም፤ በዘ​መ​ን​ህም ሁሉ የተ​ገ​ፋህ፥ የተ​ዘ​ረ​ፍ​ህም ትሆ​ና​ለህ፤ የሚ​ረ​ዳ​ህም የለም። 30ሚስት ታገ​ባ​ለህ፤ ሌላም ሰው ይነ​ጥ​ቅ​ሃል፤ ቤት ትሠ​ራ​ለህ፤ በእ​ር​ሱም አት​ቀ​መ​ጥ​በ​ትም፤ ወይን ትተ​ክ​ላ​ለህ፤ ከእ​ር​ሱም አት​ለ​ቅ​ምም። 31በሬህ በፊ​ትህ ይታ​ረ​ዳል፤ ከእ​ር​ሱም አት​በ​ላም። አህ​ያህ ከእ​ጅህ በግድ ይወ​ሰ​ዳል፤ ወደ አን​ተም አይ​መ​ለ​ስም፤ በጎ​ችህ ለጠ​ላ​ቶ​ችህ ይሰ​ጣሉ፤ የሚ​ረ​ዳ​ህም አታ​ገ​ኝም። 32ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ችህ ለሌላ ሕዝብ ይሰ​ጣሉ፤ ራሳ​ቸ​ው​ንም ሲመ​ቱ​አ​ቸው በዐ​ይ​ኖ​ችህ ታያ​ለህ፤ ልታ​ደ​ር​ገ​ውም የም​ት​ች​ለው የለም። 33የም​ድ​ር​ህን ፍሬ፥ ድካ​ም​ህ​ንም ሁሉ የማ​ታ​ው​ቀው ሕዝብ ይበ​ላ​ዋል፤ አን​ተም ሁል​ጊዜ የተ​ጨ​ነ​ቅህ፥ የተ​ገ​ፋ​ህም ትሆ​ና​ለህ። 34ዐይ​ኖ​ች​ህም ከሚ​ያ​ዩት የተ​ነሣ ዕብድ ትሆ​ና​ለህ። 35እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልት​ድን በማ​ት​ች​ል​በት በክፉ ቍስል ጕል​በ​ት​ህ​ንና ጭን​ህን ከእ​ግ​ርህ ጫማ እስከ አና​ትህ ድረስ ይመ​ታ​ሃል።
36“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አን​ተን፥ በአ​ን​ተም ላይ የም​ት​ሾ​ማ​ቸ​ውን አለ​ቆ​ች​ህን#ዕብ. “የም​ታ​ነ​ግ​ሠ​ውን ንጉሥ” ይላል። አን​ተና አባ​ቶ​ችህ ወዳ​ላ​ወ​ቃ​ች​ኋ​ቸው ሕዝብ ይወ​ስ​ድ​ሃል፤ በዚ​ያም ሌሎ​ችን የእ​ን​ጨ​ትና የድ​ን​ጋይ አማ​ል​ክ​ትን ታመ​ል​ካ​ለህ። 37እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወደ እነ​ርሱ በሚ​ወ​ስ​ድህ አሕ​ዛብ መካ​ከል ሁሉ የደ​ነ​ገ​ጥህ፥ ለም​ሳ​ሌና ለተ​ረ​ትም ትሆ​ና​ለህ። 38ብዙ ዘርም ወደ እርሻ ታወ​ጣ​ለህ፤ አን​በ​ጣም ይበ​ላ​ዋ​ልና ጥቂት ትሰ​በ​ስ​ባ​ለህ። 39ወይን ትተ​ክ​ላ​ለህ፤ ታበ​ጀ​ው​ማ​ለህ፤ ከወ​ይ​ኑም አት​ጠ​ጣም፤ ክፉ ትልም ይበ​ላ​ዋ​ልና በእ​ርሱ ደስ አይ​ል​ህም። 40የወ​ይራ ዛፍ በሀ​ገ​ርህ ሁሉ ይሆ​ን​ል​ሃል፤ ፍሬ​ውም ይረ​ግ​ፋ​ልና ዘይ​ቱን አት​ቀ​ባም። 41ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ችን ትወ​ል​ዳ​ለህ፤ ማር​ከው ይወ​ስ​ዷ​ቸ​ዋ​ልና አይ​ቀ​ሩ​ል​ህም። 42ዛፍ​ህን ሁሉ፤ የም​ድ​ር​ህ​ንም ፍሬ ሁሉ ኩብ​ኩባ ያጠ​ፋ​ዋል። 43በአ​ንተ መካ​ከል ያለ መጻ​ተኛ በአ​ንተ ላይ ከፍ ከፍ ይላል፤ አንተ ግን ዝቅ ዝቅ ትላ​ለህ። 44እርሱ ያበ​ድ​ር​ሃል፤ አንተ ግን አታ​በ​ድ​ረ​ውም፤ እርሱ ራስ ይሆ​ናል፤ አን​ተም ጅራት ትሆ​ና​ለህ። 45የአ​ም​ላ​ክ​ህ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስላ​ል​ሰ​ማህ፥ ያዘ​ዘ​ህ​ንም ትእ​ዛ​ዙ​ንና ሥር​ዐ​ቱን ስላ​ል​ጠ​በ​ቅህ፥ እስ​ክ​ት​ጠፋ ድረስ እነ​ዚህ መር​ገ​ሞች ሁሉ ይወ​ር​ዱ​ብ​ሃል፤ ያሳ​ድ​ዱ​ህ​ማል፤ ያገ​ኙ​ህ​ማል። 46በአ​ን​ተም በልጅ ልጅ​ህም ላይ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ለም​ል​ክ​ትና ለድ​ንቅ ይሆ​ናሉ።
47“ሁሉን አብ​ዝቶ ስለ ሰጠህ#“ሁሉን አብ​ዝቶ ስለ ሰጠህ” የሚ​ለው በግ​እዝ የለም። አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በፍ​ሥ​ሓና በቀና ልብ አላ​መ​ለ​ክ​ኸ​ው​ምና፥ 48በራ​ብና በጥ​ማት፥ በዕ​ራ​ቁ​ት​ነ​ትም፥ ሁሉ​ንም በማ​ጣት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሚ​ል​ክ​ብህ ለጠ​ላ​ቶ​ችህ ትገ​ዛ​ለህ፤ እስ​ኪ​ያ​ጠ​ፋ​ህም ድረስ በአ​ን​ገ​ትህ ላይ የብ​ረት ቀን​በር ይጭ​ናል። 49እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ንስር እን​ደ​ሚ​በ​ርር ከሩቅ ሀገር፥ ከም​ድር ዳር ቋን​ቋ​ቸ​ውን የማ​ት​ሰ​ማ​ውን ሕዝብ፥ 50ፊቱ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ራ​ውን፥ የሽ​ማ​ግ​ሌ​ው​ንም ፊት የማ​ያ​ፍ​ረ​ውን፥ ሕፃ​ኑ​ንም የማ​ይ​ም​ረ​ውን ሕዝብ ያመ​ጣ​ብ​ሃል። 51እስ​ክ​ት​ጠ​ፋም ድረስ የከ​ብ​ት​ህን ፍሬ፥ የም​ድ​ር​ህ​ንም ፍሬ ይበ​ላል፤ እስ​ኪ​ያ​ጠ​ፋ​ህም ድረስ እህ​ል​ህን፥ ወይ​ን​ህ​ንም፥ ዘይ​ት​ህ​ንም፥ የላ​ም​ህ​ንና የበ​ግ​ህ​ንም መንጋ አይ​ተ​ው​ል​ህም። 52በሀ​ገ​ርህ ሁሉ ያሉ፥ ትታ​መ​ን​ባ​ቸው የነ​በሩ፥ የረ​ዘሙ፥ የጸ​ኑም ቅጥ​ሮች እስ​ኪ​ፈ​ርሱ ድረስ፥ በከ​ተ​ሞ​ችህ ሁሉ ያጠ​ፋ​ሃል፤ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ጠህ ምድር ሁሉ፥ በደ​ጆች ሁሉ ያስ​ጨ​ን​ቅ​ሃል። 53ጠላ​ቶ​ች​ህም በሀ​ገ​ርህ ውስጥ ከብ​በው ባስ​ጨ​ነ​ቁ​ህና መከራ ባሳ​ዩህ ጊዜ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሰ​ጥ​ህን የሆ​ድ​ህን ፍሬ፥ የወ​ን​ዶ​ችና የሴ​ቶች ልጆ​ች​ህን ሥጋ ትበ​ላ​ለህ። 54በአ​ንተ ዘንድ የተ​ደ​ላ​ደ​ለና የተ​ቀ​ማ​ጠለ ሰው በወ​ን​ድሙ፥ አብ​ራ​ውም በም​ት​ተኛ በሚ​ስቱ፥ በቀ​ሩ​ትም ልጆቹ ይቀ​ናል፤ 55በከ​ተ​ሞ​ችህ ሁሉ ውስጥ ጠላ​ቶ​ችህ ከብ​በው ባስ​ጨ​ነ​ቁ​ህና መከራ ባሳ​ዩህ ጊዜ ሌላ ነገር የቀ​ረው የለ​ምና ከሚ​በ​ላው ከል​ጆቹ ሥጋ ለአ​ንዱ አይ​ሰ​ጥም። 56በአ​ንተ ዘንድ የተ​ለ​ሳ​ለ​ሰ​ችና የተ​ቀ​ማ​ጠ​ለች፥ ከል​ስ​ላ​ሴና ከቅ​ም​ጥ​ል​ነት የተ​ነሣ የእ​ግር ጫማ​ዋን በም​ድር ላይ ያላ​ደ​ረ​ገ​ችው ሴት፥ አቅፋ በተ​ኛ​ችው ባልዋ፥ በወ​ን​ድና በሴት ልጅ​ዋም ትቀ​ና​ለች፥ 57ከአ​ካ​ልዋ የሚ​ወ​ጣ​ውን የእ​ን​ግዴ ልጅ፥ የም​ት​ወ​ል​ዳ​ቸ​ው​ንም ልጆች፤#ዕብ. “በእ​ግ​ርዋ መካ​ከል በሚ​ወ​ጣው በእ​ን​ግዴ ልጅ​ዋና በም​ት​ወ​ል​ዳ​ቸው ልጆ​ችዋ ትቀ​ና​ለች” ይላል። በደ​ጆ​ችህ ውስጥ ጠላ​ቶ​ችህ፤ ከብ​በው ባስ​ጨ​ነ​ቁ​ህና መከራ ባሳ​ዩህ ጊዜ ሁሉን ስላ​ጣች በስ​ውር ትበ​ላ​ቸ​ዋ​ለች።
58“በዚህ መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፉ​ትን የዚ​ህን ሕግ ቃሎች ሁሉ ታደ​ርግ ዘንድ፥ ይህ​ንም ክቡ​ርና ምስ​ጉን ስም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክ​ህን ትፈራ ዘንድ ባት​ሰማ፥ 59እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ሠ​ፍ​ት​ህን፥ የዘ​ር​ህ​ንም መቅ​ሠ​ፍት፥ ታላ​ቅና የሚ​ያ​ስ​ፈራ መቅ​ሠ​ፍ​ትን፥ ለብዙ ጊዜ የሚ​ኖር ክፉ ደዌና ሕማ​ምን ሁሉ ያመ​ጣ​ብ​ሃል። 60የፈ​ራ​ኸ​ው​ንም የግ​ብፅ ደዌ ሁሉ እን​ደ​ገና ያመ​ጣ​ብ​ሃል፤ ያጣ​ብ​ቅ​ብ​ህ​ማል። 61ደግ​ሞም ይህ ሕግ ባለ​በት መጽ​ሐፍ ውስጥ ያል​ተ​ጻ​ፈ​ውን ደዌ ሁሉ፥ መቅ​ሠ​ፍ​ት​ንም ሁሉ እስ​ክ​ት​ጠፋ ድረስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያመ​ጣ​ብ​ሃል። 62የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ምና ከብ​ዛ​ታ​ችሁ የተ​ነሣ እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብት የነ​በ​ረው ቍጥ​ራ​ችሁ ጥቂት ሆኖ ይቀ​ራል። 63እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጎ ያደ​ር​ግ​ልህ ዘንድ፥ ያበ​ዛ​ህም ዘንድ ደስ ይለው እንደ ነበረ፥ እን​ዲሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሲያ​ጠ​ፋህ፥ ሲያ​ፈ​ር​ስ​ህም ደስ ይለ​ዋል፤ ትወ​ር​ሳ​ትም ዘንድ ከም​ት​ገ​ባ​ባት ምድር ትነ​ቀ​ላ​ለህ ። 64እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከም​ድር ዳር እስከ ዳር​ቻዋ ድረስ ወደ አሉ አሕ​ዛብ ሁሉ ይበ​ት​ን​ሃል፤ በዚ​ያም አን​ተና አባ​ቶ​ችህ ያላ​ወ​ቃ​ች​ኋ​ቸ​ውን ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት፥ እን​ጨ​ት​ንና ድን​ጋ​ይን ታመ​ል​ካ​ለህ። 65በእ​ነ​ዚ​ያም አሕ​ዛብ መካ​ከል ዕረ​ፍት አታ​ገ​ኝም፤ ለእ​ግ​ር​ህም ጫማ ማረ​ፊያ አይ​ሆ​ንም፤ በዚ​ያም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተን​ቀ​ጥ​ቃጭ ልብ ፥ ፈዛዛ ዐይን፥ ደካ​ማም ነፍስ ያመ​ጣ​ብ​ሃል። 66ሕይ​ወ​ትህ በዐ​ይ​ኖ​ችህ ፊት የተ​ሰ​ቀ​ለች ትሆ​ና​ለች፤#ዕብ. “ነፍ​ስ​ህም ታመ​ነ​ታ​ለች” ይላል። ሌሊ​ትና ቀንም ትደ​ነ​ግ​ጣ​ለህ፤ በሕ​ይ​ወ​ት​ህም አት​ታ​መ​ንም፤ 67ከፈ​ራ​ህ​በት ከል​ብህ ፍር​ሀት የተ​ነሣ፥ በዐ​ይ​ን​ህም ካየ​ኸው የተ​ነሣ፥ ሲነጋ እን​ዴት ይመሽ ይሆን? ትላ​ለህ፤ ሲመ​ሽም እን​ዴት ይነጋ ይሆን? ትላ​ለህ። 68ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ተመ​ል​ሰህ አታ​ያ​ትም ባል​ሁህ መን​ገ​ድም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ር​ከብ ወደ ግብፅ ይመ​ል​ስ​ሃል፤ በዚ​ያም ለጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችሁ ወን​ዶ​ችና ሴቶች አገ​ል​ጋ​ዮች ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ የሚ​ራ​ራ​ላ​ች​ሁም አይ​ኖ​ርም።”#ዕብ.“በዚ​ያም ወን​ዶ​ችና ሴቶች ባሪ​ያ​ዎች ትሆ​ኑ​አ​ቸው ዘንድ ለጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችሁ ራሳ​ች​ሁን ትሸ​ጣ​ላ​ችሁ የሚ​ገ​ዛ​ች​ሁም አይ​ገ​ኝም” ይላል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ