የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘዳ​ግም 33

33
ሙሴ ለመ​ጨ​ረሻ ጊዜ እስ​ራ​ኤ​ልን መባ​ረኩ
1የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ሙሴ ሳይ​ሞት የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች የባ​ረ​ከ​ባት በረ​ከት ይህች ናት። 2እን​ዲ​ህም አለ፦
“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሲና መጣ፤
በሴ​ይ​ርም ተገ​ለ​ጠ​ልን፤
ከፋ​ራን ተራራ፥
ከቃ​ዴስ#ዕብ. “ከእ​እ​ላ​ፋት ቅዱ​ሳኑ ...” ይላል። አእ​ላ​ፋት ጋር ፈጥኖ መጣ፤ መላ​እ​ክ​ቱም ከእ​ርሱ ጋር በቀኙ ነበሩ።
3ለሕ​ዝ​ቡም ራራ​ላ​ቸው፤
ቅዱ​ሳን ሁሉ ከእ​ጅህ በታች ናቸው፤
እነ​ር​ሱም የአ​ንተ ናቸው።
ቃሎ​ች​ህ​ንም ይቀ​በ​ላሉ።
4ሙሴም ለያ​ዕ​ቆብ ማኅ​በር ርስት የሆ​ነ​ውን ሕግ አዘ​ዘን።
5የሕ​ዝቡ አለ​ቆች ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ዶች ሁሉ ጋር በተ​ሰ​በ​ሰቡ ጊዜ፥
አለቃ በተ​ወ​ዳጁ ዘንድ ይሆ​ናል።
6ሮቤ​ልን እፈ​ል​ገ​ዋ​ለሁ፤ አይ​ሙ​ት​ብኝ፤
ቍጥ​ሩም ብዙ ይሁን።
7የይ​ሁ​ዳም በረ​ከት ይህች ናት፤
አቤቱ የይ​ሁ​ዳን ቃል ስማ፤
ወደ ሕዝ​ቡም ይግባ፤
እጆ​ቹም ይግዙ፤
በጠ​ላ​ቶቹ ላይ ረዳት ትሆ​ነ​ዋ​ለህ።
8ስለ ሌዊም እን​ዲህ አለ፥
ለሌዊ ቃሉን፥
በመ​ከ​ራም ለፈ​ተ​ኑት፥
በክ​ር​ክር ውኃም ለሰ​ደ​ቡት፥
ለእ​ው​ነ​ተ​ኛው ሰው ጽድ​ቁን መልስ።
9እና​ቱ​ንና አባ​ቱን አላ​የ​ኋ​ች​ሁም ላለ፥
ወን​ድ​ሞ​ቹ​ንም ላላ​ወቀ፥
ልጆ​ቹ​ንም ላላ​ስ​ተ​ዋለ፤
ቃል​ህን ለጠ​በቀ፥
በቃል ኪዳ​ን​ህም ለተ​ማ​ጠነ።
10ፍር​ድ​ህን ለያ​ዕ​ቆብ፥
ሕግ​ህ​ንም ለእ​ስ​ራ​ኤል ያስ​ተ​ም​ራሉ፤
በማ​ዕ​ጠ​ን​ትህ ዕጣ​ንን፥#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በቍ​ጣህ ጊዜ ዕጣ​ንን” ይላል።
በመ​ሠ​ዊ​ያ​ህም የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትን ሁል​ጊዜ ያቀ​ር​ባሉ።
11አቤቱ ኀይ​ሉን ባርክ፤
የእ​ጁ​ንም ሥራ ተቀ​በል፤
በሚ​ቃ​ወ​ሙት ጠላ​ቶቹ ላይ መከ​ራን አው​ርድ፤#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “የሚ​ነ​ሣ​በ​ትን ወገብ ውጋው” ይላል።
የሚ​ጠ​ሉ​ትም አይ​ነሡ።
12ስለ ብን​ያ​ምም እን​ዲህ አለ፦
በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ወ​ደደ በእ​ርሱ ዘንድ ተማ​ምኖ ይኖ​ራል፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዘ​መኑ ሁሉ ይጋ​ር​ደ​ዋል፤
በት​ከ​ሻ​ውም መካ​ከል ያድ​ራል።
13ስለ ዮሴ​ፍም እን​ዲህ አለ፦
ምድሩ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በረ​ከት፥
ከሰ​ማይ ዝና​ምና ጠል፥
ከታ​ችም ከጥ​ልቁ ምንጭ ናት።
14ከፀ​ሐይ መው​ጣት ከሚ​ገ​ኘው ፍሬ፥
በወ​ራት ቍጥር ከሚ​ገ​ኘው ምርት፥
15ከቀ​ደ​ሙ​ትም ተራ​ሮች ከፍ​ተ​ኛ​ነት፥
ከዘ​ለ​ዓ​ለሙ ኮረ​ብ​ቶች ራሶች፥
16በየ​ወ​ቅ​ቱም ከም​ድ​ሪቱ ምላት፥
በቍ​ጥ​ቋ​ጦው ውስጥ ከነ​በ​ረው በረ​ከት፥
በዮ​ሴፍ ራስ ላይ፥
ከወ​ን​ድ​ሞ​ቹም በከ​በ​ረው በእ​ርሱ ራስ ላይ ይው​ረድ።
17ውበቱ እንደ ላም በኵር ነው፤
ቀን​ዶቹ አንድ ቀንድ እን​ዳ​ለው ናቸው፤
በእ​ነ​ርሱ እስከ ምድር ዳርቻ ያሉ​ትን አሕ​ዛብ ሁሉ ይወ​ጋል፤
የኤ​ፍ​ሬም እልፍ አእ​ላ​ፋት፥
የም​ና​ሴም አእ​ላ​ፋት እነ​ርሱ ናቸው።
18ስለ ዛብ​ሎ​ንም እን​ዲህ አለ፦
ዛብ​ሎን ሆይ፥ በመ​ው​ጣ​ትህ፥
ይሳ​ኮር ሆይ፥ በድ​ን​ኳ​ንህ ውስጥ ደስ ይበ​ላ​ችሁ።
19አሕ​ዛ​ብን ያጠ​ፉ​አ​ቸ​ዋል፤
በዚ​ያም ይጠ​ሩ​አ​ቸ​ዋል፤
የጽ​ድቅ መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም ይሠ​ዋሉ፤
የባ​ሕ​ሩም ሀብት፥
በባ​ሕሩ ዳር የሚ​ኖሩ ሰዎ​ችም ገን​ዘብ ይመ​ግ​ብ​ሃ​ልና፥
20ስለ ጋድም እን​ዲህ አለ፦
ጋድን ሰፊ ያደ​ረገ ቡሩክ ይሁን፤
እንደ አን​በሳ ያለ​ቆ​ችን ክንድ ቀጥ​ቅጦ ያር​ፋል።
21በዚያ ከሕ​ዝቡ ገዦች ጋር የተ​ሰ​በ​ሰቡ የአ​ለ​ቆች ምድር እንደ ተከ​ፈ​ለች፥
የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውን ፍሬ አየ፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጽድ​ቁን፥
ፍር​ዱ​ንም ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር አደ​ረገ።
22ስለ ዳንም እን​ዲህ አለ፦
ዳን የአ​ን​በሳ ደቦል ነው፤
ከባ​ሳን ይበ​ር​ራል።
23ስለ ንፍ​ታ​ሌ​ምም እን​ዲህ አለ፦
ንፍ​ታ​ሌም ከበጎ ነገር ጠግ​ቦ​አል፤
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም በረ​ከት ተሞ​ል​ቶ​አል፤
ባሕ​ር​ንና ሊባን ይወ​ር​ሳል።
24ስለ አሴ​ርም እን​ዲህ አለ፦
አሴር ከል​ጆች የተ​ነሣ የተ​ባ​ረከ ይሁን፤
ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም የተ​መ​ረጠ ይሁን፤
እግ​ሩ​ንም በዘ​ይት ያጥ​ባል።
25ጫማህ ብረ​ትና ናስ ይሆ​ናል፤
እንደ ዕድ​ሜህ እን​ዲሁ ኀይ​ልህ ይሆ​ናል።
26እንደ ፍቁሩ አም​ላክ ማንም የለም፤
በሰ​ማይ የሚ​ኖ​ረው፥ በጠ​ፈ​ርም በታ​ላ​ቅ​ነት ያለው እርሱ ረዳ​ትህ ነው።
27እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ለፊት፥
በዘ​ለ​ዓ​ለም ክን​ዶች ኀይል ይጋ​ር​ድ​ሃል፤
ጠላ​ት​ህን ከፊ​ትህ አው​ጥቶ፦
አጥ​ፋው ይላል።
28እስ​ራ​ኤ​ልም ተማ​ምኖ፥
በያ​ዕ​ቆብ ምድር ብቻ​ውን፥
በስ​ን​ዴና በወ​ይን ምድር ይኖ​ራል፤
ሰማይ ከደ​መ​ናና ከጠል ጋር ለአ​ንተ ነው።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሰማይ ጠልን ለአ​ንተ ይሰ​ጣል” ይላል።
29እስ​ራ​ኤል ሆይ ብፁዕ ነህ፤
በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዳነ ሕዝብ እንደ አንተ ማን​ነው?
እርሱ ያጸ​ን​ሃል፤ ይረ​ዳ​ሃ​ልም፤
ትም​ክ​ሕ​ትህ በሰ​ይ​ፍህ ነው፤
ጠላ​ቶ​ችህ ውሸ​ታ​ሞች ናቸው፤
አን​ተም በአ​ን​ገ​ታ​ቸው ላይ ትጫ​ና​ለህ።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ