ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4
4
1ወንድሞቻችን ሆይ፥ ለተጠራሁላት አጠራር በሚገባ ትኖሩ ዘንድ በክርስቶስ እስረኛ የሆንሁ እኔ ጳውሎስ እማልዳችኋለሁ። 2#ቈላ. 3፥12-13። በፍጹም የዋህነት ራሳችሁን ዝቅ አድርጋችሁ እየታገሣችሁ፥ ለወንድሞቻችሁም እሺ እያላችሁ፥ በፍቅር እየተጋችሁና እየተባበራችሁ፥ 3በአንድ መንፈስና በሰላም ማሰሪያነት እየተጠበቃችሁ፥ 4ለአንዱ ተስፋችሁ እንደ መጠራታችሁ መጠን፥ አንድ አካልና አንድ መንፈስ ትሆኑ ዘንድ እማልዳችኋለሁ። 5ጌታ አንድ ነው፤ ሃይማኖትም አንዲት ናት፤ ጥምቀትም አንዲት ናት። 6በሁሉ ሙሉ የሚሆን ሁሉም ከእርሱ የተገኘ ከሁሉም በላይ ያለ የሁሉ አባት እግዚአብሔር አንድ ነው። 7ከእኛ ለእያንዳንዱ በክርስቶስ ስጦታ መጠን ጸጋው ተሰጥቶናል። 8#መዝ. 67፥18። “ምርኮን ማርከህ ወደ ሰማይ ወጣህ፤ ጸጋህንም ለሰው ልጅ ሰጠህ” ይላልና። 9ከምድር በታች ካልወረደ መውጣቱ ምንድን ነው? 10የወረደው እርሱ ነው፤ ሁሉንም ይመላ ዘንድ ከሰማያት ሁሉ በላይ የወጣው ደግሞ እርሱ ነው። 11እርሱም ጸጋን ሰጠ፤ ከቤተ ሰቦቹም ሐዋርያትን፥ ከእነርሱም ነቢያትንና የወንጌል ሰባኪዎችን፥ ጠባቂዎችንና መምህራንን ሾመ። 12ቅዱሳን ለአገልግሎቱ ሥራና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ እንዲጸኑ፤ 13ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ አንድ እስክንሆን ድረስ በክርስቶስ ምልዐት መጠን፥ አካለ መጠን እንደ አደረሰ እንደ አንድ ሙሉ ሰው እስክንሆን ድረስ፥ 14እንግዲህ በሽንገላቸው ያስቱ ዘንድ በሚተናኰሉ ሰዎች ተንኰል ምክንያት በትምህርት ነፋስ ሁሉ ወዲያና ወዲህ እየተፍገመገምንና እየተንሳፈፍን ሕፃናት አንሁን። 15ነገር ግን በፍቅር እውነተኞች እንሆን ዘንድ ራስ ወደ ሆነው ወደ እርሱ ወደ ክርስቶስ እንደግ። 16#ቈላ. 2፥19። ከእርሱ የተነሣ አካል ሁሉ እያንዳንዱ ክፍል በልክ እንደሚሠራ፥ በተሰጠው በሥር ሁሉ እየተጋጠመና እየተያያዘ፥ ራሱን በፍቅር ለማነጽ አካሉን ያሳድጋል።
ከአሕዛብ መለየት
17እንግዲህ በልባቸው ከንቱ አሳብ እንደሚኖሩ እንደ አሕዛብ እንዳትኖሩ ይህን እላለሁ፤ በእግዚአብሔርም እመሰክራለሁ። 18ልቡናቸው የተጨፈነ ነው፤ በስንፍናቸውና በድንቍርናቸው እግዚአብሔር ከሚሰጣቸው ሕይወት የተለዩ ናቸው። 19ተስፋ የቈረጡ ናቸው፤ ራሳቸውንም ለጕስቍልና፥ ለርኵሰትና ለመዳራት አሳልፈው ሰጡ። 20እናንተ ግን ክርስቶስን የተማራችሁት እንደዚህ አይደለም። 21በርግጥ ከሰማችሁት፥ እውነት በኢየሱስ ክርስቶስ ነውና እውነትን በእርሱ ዘንድ ትማራላችሁ፤ 22#ቈላ. 3፥9። የቀድሞ ጠባያችሁን ከእናንተ አርቁ፤ ይህንም ስሕተት በሚያመጣው ምኞት ስለሚጠፋው ስለ አሮጌው ሰውነት እላለሁ። 23የልቡናችሁን ዕውቀት አድሱ። 24#ዘፍ. 1፥26፤ ቈላ. 3፥10። እግዚአብሔርም በእውነት፥ በቅንነትና በንጽሕና ያደሰውን አዲሱን ሰውነት ልበሱት።#ግሪኩ “በእውነተኛ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱት” ይላል።
25 #
ዘካ. 8፥16። ስለዚህም ሐሰትን ተዉአት፤ ሁላችሁም ከወንድሞቻችሁ ጋር እውነትን ተነጋገሩ፤ እኛ አንድ አካል ነንና። 26#መዝ. 4፥4። ተቈጡ፤ አትበድሉም፤ ፀሐይ ሳይጠልቅም ቍጣችሁን አብርዱ። 27ለሰይጣንም መንገድን አትስጡት። 28የሚሰርቅም እንግዲህ አይስረቅ፤ ነገር ግን ድሃውን ይረዳ ዘንድ በእጆቹ መልካም እየሠራ ይድከም። 29የሚሰሙአችሁ ሞገስን ያገኙ ዘንድ፥ ግዳጃችሁ እንዲፈጸም መልካም ነገር እንጂ ክፉ ነገር ሁሉ ከአፋችሁ አይውጣ። 30በዳናችሁ ጊዜ የታተማችሁበትን የእግዚአብሔርን ቅዱስ መንፈስ አታሳዝኑት። 31መራራነትንና ቍጣን፥ ብስጭትንና ርግማንን፥ ጥፋትንና ስድብን ሁሉ ከክፉ ነገር ሁሉ ጋር ከእናንተ አርቁ። 32#ቈላ. 3፥13። እርስ በርሳችሁም ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፤ እግዚአብሔርም በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ።
Currently Selected:
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ