ወደ ኤፌ​ሶን ሰዎች 6:13-17

ወደ ኤፌ​ሶን ሰዎች 6:13-17 አማ2000

ስለ​ዚ​ህም በክፉ ቀን መቃ​ወም እን​ድ​ት​ችሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጋሻ ያዙ፤ እን​ድ​ት​ጸ​ኑም በሁሉ የተ​ዘ​ጋ​ጃ​ችሁ ሁኑ። እን​ግ​ዲህ ወገ​ባ​ች​ሁን በእ​ው​ነት ታጥ​ቃ​ችሁ ቁሙ፤ የጽ​ድ​ቅ​ንም ጥሩር ልበሱ። የሰ​ላም ወን​ጌል ኀይ​ል​ንም ተጫ​ም​ታ​ችሁ ቁሙ። ከዚ​ህም ሁሉ ጋር የሚ​ን​በ​ለ​በሉ የክ​ፉን ፍላ​ፃ​ዎች ሁሉ ማጥ​ፋት እን​ድ​ት​ችሉ የእ​ም​ነ​ትን ጋሻ አንሡ። የመ​ዳ​ን​ንም የራስ ቍር በራ​ሳ​ችሁ ላይ ጫኑ፤ የመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስ​ንም ሰይፍ ያዙ፤ ይኸ​ውም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ነው።