ኦሪት ዘፀ​አት 10

10
8፥ የአ​ን​በጣ መንጋ
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፥ “ወደ ፈር​ዖን ግባ፤ እኔ የፈ​ር​ዖ​ን​ንና የሹ​ሞ​ቹን ልብ አጽ​ን​ቼ​አ​ለ​ሁና፥ ተአ​ም​ራቴ በእ​ነ​ርሱ ላይ በት​ክ​ክል ይመጣ ዘንድ፤ 2በግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም ላይ የተ​ዘ​ባ​በ​ት​ሁ​ትን ሁሉ፥ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ባ​ቸ​ው​ንም ተአ​ም​ራ​ቴን በል​ጆ​ቻ​ች​ሁና በልጅ ልጆ​ቻ​ችሁ ጆሮች ትነ​ግሩ ዘንድ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።” 3ሙሴና አሮ​ንም ወደ ፈር​ዖን ገቡ፤ አሉ​ትም፥ “የዕ​ብ​ራ​ው​ያን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እኔን ማፈ​ርን እስከ መቼ እንቢ ትላ​ለህ? ያመ​ል​ኩኝ ዘንድ ሕዝ​ቤን ልቀቅ። 4ሕዝ​ቤን ለመ​ል​ቀቅ እንቢ ብትል ግን፥ እነሆ፥ ነገ በዚህ ጊዜ በተ​ራ​ራ​ዎ​ችህ ሁሉ ላይ አን​በ​ጣን አመ​ጣ​ለሁ፤ 5የም​ድ​ሩ​ንም ፊት ይሸ​ፍ​ናል፤ ምድ​ሩን ለማ​የት አይ​ቻ​ልም፤ ከበ​ረ​ዶ​ውም ተርፎ በም​ድር ላይ የቀ​ረ​ላ​ች​ሁን ትርፍ ሁሉ ይበ​ላል፤ ያደ​ገ​ላ​ች​ሁ​ንም የእ​ር​ሻ​ውን ዛፍ ሁሉ ይበ​ላል፤ 6ቤቶ​ች​ህም የሹ​ሞ​ች​ህም ሁሉ ቤቶች፥ የግ​ብ​ፃ​ው​ያን ሁሉ ቤቶች በእ​ርሱ ይሞ​ላሉ፤ አባ​ቶ​ችህ፥ የአ​ባ​ቶ​ች​ህም አባ​ቶች በም​ድር ላይ ከተ​ቀ​መ​ጡ​በት ቀን ጀምሮ እስ​ከ​ዚህ ቀን ድረስ እንደ እርሱ ያለ ያላ​ዩት ነው።” ሙሴም ተመ​ልሶ ከፈ​ር​ዖን ዘንድ ወጣ። 7የፈ​ር​ዖ​ንም ሹሞች፥ “ይህ ሰው እስከ መቼ እን​ቅ​ፋት ይሆ​ን​ብ​ናል? አም​ላ​ካ​ቸ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ል​ኩት ዘንድ ሰዎ​ችን ልቀቅ፤ ግብ​ፅስ እንደ ጠፋች ገና አታ​ው​ቅ​ምን?” አሉት። 8ሙሴ​ንና አሮ​ን​ንም ወደ ፈር​ዖን ጠሩ​አ​ቸው፤ ፈር​ዖ​ንም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ሂዱ፤ አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አም​ልኩ፤ ነገር ግን ከእ​ና​ንተ ጋር የሚ​ሄ​ዱት እነ​ማን ናቸው?” 9ሙሴም አለው፥ “እኛ ከታ​ና​ና​ሾ​ቻ​ች​ንና ከሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ችን፥ ከወ​ን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ችን ጋር እን​ሄ​ዳ​ለን፤ በጎ​ቻ​ች​ን​ንና ላሞ​ቻ​ች​ን​ንም እን​ወ​ስ​ዳ​ለን። የአ​ም​ላ​ካ​ችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓል ነውና።” 10ፈር​ዖ​ንም አላ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ና​ንተ ጋር ይሁን፤ እነሆ፥ እና​ን​ተን ስለቅ ልጆ​ቻ​ች​ሁ​ንም መል​ቀቅ አለ​ብ​ኝን? ክፉ ነገር እን​ደ​ሚ​ገ​ጥ​ማ​ችሁ ዕወቁ። 11እን​ዲ​ህም አይ​ደ​ለም፤ እና​ንተ ወን​ዶቹ ሂዱ፤ ይህን ፈል​ጋ​ች​ኋ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አም​ልኩ” አላ​ቸው። ሙሴ​ንና አሮ​ን​ንም ከፈ​ር​ዖን ፊት አስ​ወ​ጡ​አ​ቸው።
12እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “በግ​ብፅ ሀገር ላይ እጅ​ህን ዘርጋ፤ አን​በ​ጣም በም​ድር ላይ ይወ​ጣል፤ ከበ​ረ​ዶ​ውም የተ​ረ​ፈ​ውን የም​ድር ቡቃያ ሁሉና የዛ​ፉን ፍሬ ሁሉ ይበ​ላል።” 13ሙሴም በት​ሩን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የደ​ቡ​ብን#ዕብ. “የም​ሥ​ራቅ” ይላል። ነፋስ ያን ቀን ሁሉ ሌሊ​ቱ​ንም ሁሉ አመጣ፤ ማለ​ዳም በሆነ ጊዜ የደ​ቡብ#ዕብ. “የም​ሥ​ራቁ” ይላል ነፋስ አን​በ​ጣን አመጣ። 14አን​በ​ጣም በግ​ብፅ ሀገር ሁሉ ላይ ወጣ፤ በግ​ብ​ፅም ዳርቻ ሁሉ ላይ ተቀ​መጠ፤ እጅ​ግም ብዙና ጠን​ካራ ነበር፤ ይህ​ንም የሚ​ያ​ህል አን​በጣ በፊት አል​ነ​በ​ረም፤ ወደ​ፊ​ትም ደግሞ እንደ እርሱ አይ​ሆ​ንም። 15የም​ድ​ሩ​ንም ፊት ፈጽሞ ሸፈ​ነው፤ ሀገ​ሪ​ቱም ጠፋች፤ የሀ​ገ​ሪ​ቱን ቡቃያ ሁሉ ከበ​ረ​ዶ​ውም የተ​ረ​ፈ​ውን፥ በዛፉ የነ​በ​ረ​ውን ፍሬ ሁሉ በላ፤ ለም​ለም ነገር በዛ​ፎች ላይ፥ በእ​ር​ሻ​ውም ቡቃያ ሁሉ ላይ በግ​ብፅ ሀገር ሁሉ አል​ቀ​ረም። 16ፈር​ዖ​ንም ሙሴ​ንና አሮ​ንን በፍ​ጥ​ነት ጠራ፥ “በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት፥ በእ​ና​ን​ተም ላይ በደ​ልሁ፤ 17አሁን እን​ግ​ዲህ እን​ደ​ገና በዚህ ጊዜ ብቻ ኀጢ​አ​ቴን ይቅር በሉኝ፤ ይህ​ንም ሞት ብቻ ከእኔ ያነ​ሣ​ልኝ ዘንድ ወደ አም​ላ​ካ​ችሁ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸል​ዩ​ልኝ” አላ​ቸው። 18ሙሴም ከፈ​ር​ዖን ፊት ወጣ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጸለየ። 19እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከባ​ሕር#ዕብ. “ከም​ዕ​ራብ” ይላል። ዐውሎ ነፋ​ሱን አስ​ወ​ገደ፤ አን​በ​ጣ​ዎ​ች​ንም ወስዶ በኤ​ር​ትራ ባሕር ውስጥ ጣላ​ቸው፤ አንድ አን​በ​ጣም እን​ኳን በግ​ብፅ ዳርቻ ሁሉ አል​ቀ​ረም። 20እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የፈ​ር​ዖ​ንን ልብ አጸና የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች አል​ል​ቀ​ቀም።
9፥ ጨለማ
21እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “እጅ​ህን ወደ ሰማይ ዘርጋ፤ በግ​ብ​ፅም ሀገር ላይ ጨለማ ይሁን፤ ጨለ​ማ​ውም የሚ​ዳ​ሰስ ነው” አለው። 22ሙሴም እጁን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ በግ​ብ​ፅም ሀገር ሁሉ ላይ ጽኑ ጨለ​ማና ጭጋግ ሦስት ቀን ሆነ፤ 23ማንም ወን​ድ​ሙን አላ​የም፤ ሦስት ቀን ሙሉም ከመ​ኝ​ታው ማንም አል​ተ​ነ​ሣም፤ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ ግን በተ​ቀ​መ​ጡ​በት ስፍራ ሁሉ ብር​ሃን ነበ​ራ​ቸው። 24ፈር​ዖ​ንም ሙሴ​ንና አሮ​ንን ጠርቶ፥ “ሂዱ፤ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አም​ልኩ፤ ነገር ግን በጎ​ቻ​ች​ሁ​ንና ከብ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ብቻ ተዉ፤ ልጆ​ቻ​ች​ሁና ሴቶ​ቻ​ችሁ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ዕቃ​ችሁ” ይላል። ግን ከእ​ና​ንተ ጋር ይሂዱ” አላ​ቸው። 25ሙሴም አለው፥ “አይ​ሆ​ንም! አንተ ደግሞ ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ን​ሠ​ዋው መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንና የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትን ትሰ​ጠ​ና​ለህ።#አን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ “እብ​ነኑ ንገ​ብር” ብሎ ይጨ​ም​ራል። 26ከብ​ቶ​ቻ​ችን ከእኛ ጋር ይሄ​ዳሉ፤ አንድ ሰኰ​ናም አይ​ቀ​ርም፤ አም​ላ​ካ​ች​ንን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለማ​ም​ለክ ከእ​ነ​ርሱ እን​ወ​ስ​ዳ​ለ​ንና፤ አም​ላ​ካ​ች​ንን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ደ​ም​ና​መ​ል​ከው ከዚያ እስ​ክ​ን​ደ​ርስ አና​ው​ቅም።” 27እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የፈ​ር​ዖ​ንን ልብ አጸና፤ ሊለ​ቅ​ቃ​ቸ​ውም አል​ወ​ደ​ደም። 28ፈር​ዖ​ንም ሙሴን፥ “ከእኔ ዘንድ ሂድ፤ በፊቴ በም​ት​ታ​ይ​በት ቀን ትሞ​ታ​ለ​ህና ዳግ​መኛ ፊቴን እን​ዳ​ታይ ተጠ​ን​ቀቅ” አለው። 29ሙሴም፥ “እንደ ተና​ገ​ርህ ይሁን፤ ፊት​ህን እን​ደ​ገና አላ​ይም” አለ።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ