የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፀ​አት 12:12-13

ኦሪት ዘፀ​አት 12:12-13 አማ2000

እኔም በዚ​ያች ሌሊት በግ​ብፅ ሀገር አል​ፋ​ለሁ፤ በግ​ብ​ፅም ሀገር ከሰው እስከ እን​ስሳ ድረስ በኵ​ርን ሁሉ እገ​ድ​ላ​ለሁ፤ በግ​ብ​ፅም አማ​ል​ክት ሁሉ ላይ በቀ​ልን አደ​ር​ግ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ። ደሙም ባላ​ች​ሁ​ባ​ቸው ቤቶች ምል​ክት ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል፤ ደሙ​ንም አያ​ለሁ፤ እና​ን​ተ​ንም እሰ​ው​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔም የግ​ብ​ፅን ሀገር በመ​ታሁ ጊዜ የጥ​ፋት መቅ​ሠ​ፍት አይ​መ​ጣ​ባ​ች​ሁም።