የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፀ​አት 14

14
እስ​ራ​ኤል ቀይ ባሕ​ርን መሻ​ገ​ራ​ቸው
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦ 2“ተመ​ል​ሰው በመ​ግ​ደ​ሎና በባ​ሕር መካ​ከል፥ በብ​ኤ​ል​ሴ​ፎን ፊት ለፊት ባለው ገላጣ መን​ደር አን​ጻር እን​ዲ​ሰ​ፍሩ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ተና​ገር፤ ከእ​ር​ሱም አጠ​ገብ በባ​ሕር ዳር ትሰ​ፍ​ራ​ላ​ችሁ። 3ፈር​ዖ​ንም ለሕ​ዝቡ ስለ እስ​ራ​ኤል ልጆች፦ ‘በም​ድር ይቅ​በ​ዘ​በ​ዛሉ፤ ምድረ በዳም ዘጋ​ቻ​ቸው’ ይላል። 4እኔም የፈ​ር​ዖ​ንን ልብ አጸ​ና​ለሁ፤ እር​ሱም ከኋ​ላ​ቸው ይከ​ተ​ላ​ቸ​ዋል፤ እኔም በፈ​ር​ዖ​ንና በሠ​ራ​ዊቱ ሁሉ ላይ እከ​ብ​ራ​ለሁ፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም ሁሉ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።” እነ​ር​ሱም እን​ዲሁ አደ​ረጉ። 5ሕዝ​ቡም እንደ ኰበ​ለሉ ለግ​ብፅ ንጉሥ ነገ​ሩት፤ የፈ​ር​ዖ​ንና የሹ​ሞ​ቹም ልብ በሕ​ዝቡ ላይ ተለ​ወ​ጠና፥ “እን​ዳ​ይ​ገ​ዙ​ልን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች የለ​ቀ​ቅ​ነው ምን ማድ​ረ​ጋ​ችን ነው?” አሉ። 6ፈር​ዖ​ንም ሰረ​ገ​ላ​ውን አሰ​ናዳ፤ ሕዝ​ቡ​ንም ከእ​ርሱ ጋር ሰበ​ሰበ። 7ስድ​ስት መቶ የተ​መ​ረጡ ሰረ​ገ​ሎ​ች​ንም፥ የግ​ብ​ፅ​ንም ፈረ​ሶች ሁሉ ወስዶ ሁሉ​ንም ከሦ​ስት ከፈ​ላ​ቸው። 8እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የግ​ብ​ፅን ንጉሥ የፈ​ር​ዖ​ን​ንና የሹ​ሞ​ቹን ልብ አጸና፤ እር​ሱም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች አሳ​ደደ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከፍ ባለች እጅ ወጡ። 9ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም፥ የፈ​ር​ዖን ፈረ​ሶች፥ ሰረ​ገ​ሎ​ቹም፥ ፈረ​ሰ​ኞ​ቹም፥ ሠራ​ዊ​ቱም ሁሉ አሳ​ደ​ዱ​አ​ቸው፤ በባ​ሕሩ ዳር በብ​ኤ​ል​ሴ​ፎን ፊት ለፊት ባለው ገላጣ መን​ደር አን​ጻ​ርም ሰፍ​ረው አገ​ኙ​አ​ቸው።
10ፈር​ዖ​ንም በቀ​ረበ ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዐይ​ና​ቸ​ውን አነሡ፤ እነ​ሆም፥ ግብ​ፃ​ው​ያን ሲከ​ተ​ሉ​አ​ቸው አዩ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እጅግ ፈሩ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ። 11ሙሴ​ንም አሉት፥ “በግ​ብፅ መቃ​ብር ስላ​ል​ኖረ በም​ድረ በዳ እን​ሞት ዘንድ አወ​ጣ​ኸን? ከግ​ብፅ ታወ​ጣን ዘንድ ይህ ያደ​ረ​ግ​ህ​ብን ምን​ድን ነው? 12በም​ድረ በዳ ከም​ን​ሞት ብን​ገ​ዛ​ላ​ቸው ይሻ​ለ​ና​ልና፦ ‘ተወን፤ ለግ​ብ​ፃ​ው​ያን እን​ገዛ’ ብለን በግ​ብፅ ሳለን ያል​ንህ ቃል ይህ አይ​ደ​ለ​ምን?” 13ሙሴም ለሕ​ዝቡ፥ “አት​ፍሩ፤ ዛሬ የም​ታ​ዩ​አ​ቸ​ውን ግብ​ፃ​ው​ያ​ንን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አታ​ዩ​አ​ቸ​ው​ምና ቁሙ፤ ዛሬ ለእ​ና​ንተ የሚ​ያ​ደ​ር​ጋ​ትን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማዳን እዩ። 14እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እና​ንተ ይዋ​ጋል፤ እና​ን​ተም ዝም ትላ​ላ​ችሁ” አላ​ቸው።
15እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ለምን ትጮ​ኽ​ብ​ኛ​ለህ? ከብ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን እን​ዲ​ነዱ#ዕብ. “እን​ዲ​ጓዙ” ይላል። ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ንገር። 16አን​ተም በት​ር​ህን አንሣ፤ እጅ​ህ​ንም በባ​ሕሩ ላይ ዘርጋ፤ ክፈ​ለ​ውም፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በባ​ሕሩ ውስጥ በየ​ብስ ያል​ፋሉ። 17እነ​ሆም፥ እኔ የፈ​ር​ዖ​ን​ንና የግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንን ልብ አጸ​ና​ለሁ፤ በኋ​ላ​ቸ​ውም ይገ​ባሉ፤ በፈ​ር​ዖ​ንና በሠ​ራ​ዊ​ቱም ሁሉ፥ በሰ​ረ​ገ​ሎ​ቹም፥ በፈ​ረ​ሰ​ኞ​ቹም ላይ እከ​ብ​ራ​ለሁ። 18ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም በፈ​ር​ዖ​ንና በሰ​ረ​ገ​ሎቹ፥ በፈ​ረ​ሰ​ኞ​ቹም ላይ ክብር በአ​ገ​ኘሁ ጊዜ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።” 19በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሠራ​ዊት ፊት ይሄድ የነ​በ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ፈቀቅ ብሎ በኋ​ላ​ቸው ሄደ፤ የደ​መ​ና​ውም ዐምድ ከፊ​ታ​ቸው ፈቀቅ ብሎ በኋ​ላ​ቸው ቆመ፤ 20በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ሰፈ​ርና በእ​ስ​ራ​ኤል ሰፈር መካ​ከ​ልም ገባ፤ በዚ​ያም ጭጋ​ግና ጨለማ ነበረ፤ ሌሊ​ቱም አለፈ፤ ሌሊ​ቱ​ንም ሁሉ እርስ በእ​ር​ሳ​ቸው አል​ተ​ቃ​ረ​ቡም።
21ሙሴም በባ​ሕሩ ላይ እጁን ዘረጋ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሌሊ​ቱን ሁሉ ጽኑ የአ​ዜብ ነፋስ አም​ጥቶ ባሕ​ሩን አስ​ወ​ገ​ደው፤ ባሕ​ሩ​ንም አደ​ረ​ቀው፤ ውኃ​ውም ተከ​ፈለ። 22የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በባ​ሕሩ መካ​ከል በየ​ብስ ገቡ፤ ውኃ​ውም በቀ​ኛ​ቸ​ውና በግ​ራ​ቸው እንደ ግድ​ግዳ ሆነ​ላ​ቸው። 23ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም፥ የፈ​ር​ዖን ፈረ​ሶ​ችና ሰረ​ገ​ሎች፥ ፈረ​ሰ​ኞ​ቹም ሁሉ እያ​ሳ​ደዱ በኋ​ላ​ቸው ወደ ባሕር መካ​ከል ገቡ። 24ንጋ​ትም በሆነ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ሳ​ትና በደ​መና ዐምድ ሆኖ የግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንን ሠራ​ዊት ተመ​ለ​ከተ፤ የግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ን​ንም ሠራ​ዊት አወከ። 25የሰ​ረ​ገ​ሎ​ቹ​ንም መን​ኰ​ራ​ኵር አሰረ፤ ወደ ጭን​ቅም አገ​ባ​ቸው፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እነ​ርሱ ይዋ​ጋ​ላ​ቸ​ዋ​ልና ከእ​ስ​ራ​ኤል ፊት እን​ሽሽ” አሉ።
ግብ​ፃ​ው​ያን እንደ ሰጠሙ
26እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “እጅ​ህን በባ​ሕሩ ላይ ዘርጋ፤ ውኃ​ውም በግ​ብ​ፃ​ው​ያን፥ በሰ​ረ​ገ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም፥ በፈ​ረ​ሰ​ኞ​ቻ​ቸ​ውም ላይ ይመ​ለስ፤ ይሸ​ፍ​ና​ቸ​ውም።” 27ሙሴም እጁን በባ​ሕሩ ላይ ዘረጋ፤ ባሕ​ሩም ማለዳ ወደ መፍ​ሰሱ ተመ​ለሰ፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም ከእ​ርሱ ሸሹ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ግብ​ፃ​ው​ያ​ንን በባ​ሕሩ መካ​ከል ጣላ​ቸው። 28ውኃ​ውም ተመ​ልሶ በኋ​ላ​ቸው ወደ ባሕር የገ​ቡ​ትን ሰረ​ገ​ሎ​ችን፥ ፈረ​ሰ​ኞ​ች​ንም፥ የፈ​ር​ዖ​ን​ንም ሠራ​ዊት ሁሉ ከደነ፤ ከመ​ጡ​ትም ሁሉ አንድ ስንኳ የቀረ የለም። 29የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ግን በባ​ሕሩ ውስጥ በየ​ብስ ሄዱ፤ ውኃ​ውም በቀ​ኛ​ቸ​ውና በግ​ራ​ቸው እንደ ግድ​ግዳ ሆነ​ላ​ቸው። 30እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚያ ቀን እስ​ራ​ኤ​ልን ከግ​ብ​ፃ​ው​ያን እጅ አዳ​ና​ቸው፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ግብ​ፃ​ው​ያን እንደ ሞቱ በባ​ሕር ዳር አዩ። 31እስ​ራ​ኤ​ልም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ላይ ያደ​ረ​ጋ​ትን ታላ​ቂ​ቱን እጅ አዩ፤ ሕዝ​ቡም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈሩ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አመኑ፤ ባሪ​ያ​ው​ንም ሙሴን አከ​በሩ።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንና ባሪ​ያ​ውን ሙሴን አመኑ” ይላል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ