ኦሪት ዘፀአት 15
15
የሙሴ መዝሙር
1በዚያ ጊዜም ሙሴና የእስራኤል ልጆች ይህን መዝሙር ለእግዚአብሔር ዘመሩ፤ እንዲህም ብለው ተናገሩ፦
“ለእግዚአብሔር እንዘምራለን፤ በክብር እጅግ ከፍ ከፍ ብሎአልና፤
ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባሕር ጣለ።
2እኔን ለማዳን ረዳትና ሰዋሪ ሆነኝ፤
ይህ አምላኬ ነው፤ አመሰግነውማለሁ፤
የአባቴ አምላክ ነው፤ ከፍ ከፍም አደርገዋለሁ።
3እግዚአብሔር#ዕብ. “እግዚአብሔር ተዋጊ ነው” ይላል። ጦርነትን ያጠፋል፤ ስሙም እግዚአብሔር ነው፤
4የፈርዖንን ሰረገሎች፥ ሠራዊቱንም በባሕር ጣላቸው።
በሦስት የተከፈሉ ፈረሰኞችም በኤርትራ ባሕር ሰጠሙ።
5ማዕበልም ከደናቸው፤
ወደ ባሕር ጥልቀት እንደ ድንጋይ ሰጠሙ።
6አቤቱ፥ ቀኝህ በኀይል ከበረ፤
አቤቱ፥ ቀኝህ ጠላቶችን አደቀቀ።
7በክብርህም ብዛት ጠላቶችህን አጠፋህ፤
ቍጣህን ሰደድህ፤ እንደ ገለባም በላቸው።
8በቍጣህ እስትንፋስ ውኃው ቆመ፤
ውኃዎች እንደ ግደግዳ ቆሙ፤
ሞገዱም በባሕር መካከል ረጋ።
9ጠላትም፦ ‘አሳድጄ እይዛቸዋለሁ፤
ምርኮም እካፈላለሁ፤ ነፍሴንም አጠግባታለሁ፤
በሰይፌም እገድላለሁ፤ በእጄም እገዛለሁ’ አለ።
10ነፋስህን ላክህ፤ ባሕርም ከደናቸው፤
በብዙ ውኆች ውስጥ እንደ አረር ሰጠሙ።
11አቤቱ፦ በአማልክት መካከል አንተን የሚመስል ማን ነው?
በቅዱሳንም ዘንድ እንደ አንተ የከበረ ማን ነው?
በምስጋና የተደነቅህ ነህ፤ ድንቅንም የምታደርግ ነህ፤
12ቀኝህን ዘረጋህ፤ ምድርም ዋጠቻቸው።
13በቸርነትህ የተቤዠሃቸውን ሕዝብህን መራህ፤
በኀይልህ ወደ ቅዱስ ማደሪያህ ጠራሃቸው።
14አሕዛብ ሰሙ፤ ተቈጡም፤
በፍልስጥኤም የሚኖሩትን ምጥ ያዛቸው።
15ያን ጊዜ የኤዶም አለቆች ሸሹ፤
የሞዓብንም አለቆች መንቀጠቀጥ ያዛቸው፤
በከነዓን የሚኖሩ ሁሉ ቀለጡ።
16ፍርሀትና ድንጋጤ ወደቀባቸው፤
የክንድህ ብርታትም ከድንጋይ ይልቅ ጸና፤
አቤቱ፥ ሕዝብህ እስኪያልፉ ድረስ፥
የተቤዠሃቸው እኒህ ሕዝብህ እስኪያልፉ ድረስ፤
17አቤቱ፥ አንተ ታስገባቸዋለህ፤
በመመስገኛህ ተራራም#ግሪክ ሰባ. ሊ. እና ዕብ. “በርስትህ ተራራ” ይላል። ትተክላቸዋለህ፤
አቤቱ፥ ለማደሪያህ ባደረግኸው ስፍራ፥
አቤቱ፥ እጆችህ ባዘጋጁት መቅደስ፤
18እግዚአብሔር ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለምም ይነግሣል።
ማሕሌተ ማርያም እኅተ ሙሴ
19“የፈርዖን ፈረሶች ከሰረገሎቹና ከፈረሰኞቹ ጋር ወደ ባሕር ገቡ፤ እግዚአብሔርም የባሕሩን ውኆች መለሰባቸው፤ የእስራኤል ልጆች ግን በባሕሩ መካከል በየብስ አለፉ፤ ውኃውም ለእነርሱ በቀኝ እንደ ግድግዳ፥ በግራም እንደ ግድግዳ ሆነላቸው።”#“ውኃውም ለእነርሱ በቀኝ እንደ ግድግዳ፥ በግራም እንደ ግድግዳ ሆነላቸው” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. እና በዕብ. የለም። 20የአሮን እኅት ነቢይቱ ማርያምም ከበሮ በእጅዋ ወሰደች፤ ሴቶችም ሁሉ በከበሮና በዝማሬ በኋላዋ ወጡ። 21ማርያምም አስቀድማ ለእግዚአብሔር እንዘምር አለች፥ “ለእግዚአብሔር እንዘምር በክብር እጅግ ከፍ ከፍ ብሎአልና፤ ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባሕር ጥሎአልና።”
መራራው ውኃ እንደ ጣፈጠ
22ሙሴም የእስራኤልን ልጆች ከኤርትራ ባሕር አውጥቶ ወደ ሱር ምድረ በዳ ወሰዳቸው። በምድረ በዳም ሦስት ቀን ተጓዙ፤ ይጠጡም ዘንድ ውኃ አላገኙም። 23ወደ ማራም በመጡ ጊዜ ከማራ ውኃ ሊጠጡ አልቻሉም፤ ውኃው መራራ ነበርና፤ ስለዚህ የዚያ ስፍራ ስም “መሪር” ተብሎ ተጠራ። 24ሕዝቡም፥ “ምን እንጠጣለን?” ብለው በሙሴ ላይ አንጐራጐሩ። 25ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፤ እግዚአብሔርም ዕንጨትን አሳየው፤ በውኃውም ላይ ጣለው፤ ውኃውም ጣፈጠ። በዚያም ሥርዐትንና ፍርድን አደረገላቸው፤ በዚያም ፈተናቸው። 26እርሱም፥ “አንተ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቀህ ብትሰማ፥ በፊቱም መልካምን ብታደርግ፥ ትእዛዙንም ብታደምጥ፥ ሥርዐቱንም ሁሉ ብትጠብቅ፥ በግብፃውያን ላይ ያመጣሁትን በሽታ አላደርስብህም፤ እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝና” አለ።
27እነርሱም ወደ ኤሎም መጡ፤ በዚያም ዐሥራ ሁለት የውኃ ምንጮችና ሰባ የዘንባባ ዛፎች ነበሩባት፤ በዚያም በውኃው አጠገብ ሰፈሩ።
Currently Selected:
ኦሪት ዘፀአት 15: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ