ኦሪት ዘፀ​አት 15:1-3

ኦሪት ዘፀ​አት 15:1-3 አማ2000

በዚያ ጊዜም ሙሴና የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ይህን መዝ​ሙር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘመሩ፤ እን​ዲ​ህም ብለው ተና​ገሩ፦ “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዘ​ም​ራ​ለን፤ በክ​ብር እጅግ ከፍ ከፍ ብሎ​አ​ልና፤ ፈረ​ሱ​ንና ፈረ​ሰ​ኛ​ውን በባ​ሕር ጣለ። እኔን ለማ​ዳን ረዳ​ትና ሰዋሪ ሆነኝ፤ ይህ አም​ላኬ ነው፤ አመ​ሰ​ግ​ነ​ው​ማ​ለሁ፤ የአ​ባቴ አም​ላክ ነው፤ ከፍ ከፍም አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጦር​ነ​ትን ያጠ​ፋል፤ ስሙም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤